Wednesday 12 May 2021

ከኦርቶዶክስ ውጭ ያለ መጤ ነው?

Please read in PDF

ከንቱ ትምክህት!

ማኅበረ ቅዱሳንና አንዳንድ የኦርቶዶክስ ሰባክያን፣ ስለ ክርስትና ሲያወሩ፣ ክርስትናን ራሳቸው ጠፍጥፈው የሠሩትና ለዓለም የናኙት ይመስላሉ። እነርሱ በግብዝነት የሚመኩትን ያህል ክርስትና የሰበኩት፣ የመንግሥቱን ወንጌል ለዓለሙ የናኙት የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት እንኳ እንደ እነርሱ ፈጽሞ አይመኩም፤ አይገበዙምም። እጅግ በጣም የሚያስደንቀው ነገር፣ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ አባ ሰላማ፣ ኢትዮጵያዊ  እንዳልኾነ የሚያውቁ እጅግ ጥቂቶች ናቸው። እንዲያውም ከታወቁት የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፍት አንዱ፣ ቅዱስ ማቴዎስ የተገደለው በኢትዮጵያ ምድር እንደ ኾነ ይነግረናል። ክርስትና አገር በቀል ቢኾን፣ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ምድር ባልተገደለ!



እኛን ጨምሮ አሕዛብ ለነበረው ለመላለሙ ክርስትናን የናኙት፣ የተወደዱት የጌታ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት እንደ ኾኑ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ይነግረናል። ታድያ ለምን ይኾን ግን እንዲህ ባልሠራነውና ባላገኘነው፣ ሌላው በነጻ በሰጠንና ቆርሶ ባካፈለን ነገር፣ ልክ እንደ ራሳችን የምንመካበትና የምንገበዝበት?! ያውም ከ1500 በላይ ለኾኑት ዓመታት፣ በግብጽ ሞግዚትነትና በብዙ ዕድፍ ለወየበ ክርስትናችን፣ እንዲህ መገበዝ ያሳፍራል፣ አንገት ያስደፋል፣ ንስሐ ያስመኛል እንጂ ይህን ያህል አያስገብዝም ነበር።

ማኅበረ ቅዱሳንና ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን!

ማኅበረ ቅዱሳን “በምድር ላይ ማንን ትጠላለህ?” ቢባል፣ እንደ ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን የሚጠላው ያለ አይመስለኝም። የማኅበረ ቅዱሳን ዋና አመራር የነበሩትም ይኹኑ አኹን ያሉት[እነ ያረጋል አበጋዝ፣ ኤፍሬም እሸቴ፣ ዳንኤል ክብረት፣ አባይነህ ካሴ]፣ ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንን የሚጠሉትን ያህል፣ ሰይጣንና ኀጢአትን የሚጠሉ አይመስለኝም። ለዚህ ማሳያ ደግሞ አባይነህ ካሴ፣ ከሰሞኑ የተናገረውን ማንሳት በቂ ነው። አባይነህ በግልጥ ቃል፣ በንቀት ንግግር፤ “ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን በንጉሡ ዘርዐ ያዕቆብ ተረትተው፣ የሚገባቸውን ቅጣት ተቀብለው ተሰናብተዋል” በማለት ይናገራል።

ማኅበረ ቅዱሳን ለዓመታት የእስጢፋኖሳውያንን ግድያና አሰቃቂ ዕልቂት ሲቃወሙ እንዳልነበር፣ አኹን አፋቸውን ሞልተው፣ “የሚገባቸውን ቅጣት ተቀብለዋል” በማለት ማመናቸው እጅግ አስደናቂ ነው። በርግጥ ተአምረ ማርያምም የደቂቀ እስጢፋኖሳውያንን አሰቃቂ ግድያና እንግልት፣ “ለማርያም ተአምር የተደረገ ቅንአት ነው” ብሎ ያወራል። እንግዲህ ይታያችሁ፣ ግድያ ትክክል ነው፣ በሌላው አማኝ ላይ ሰቆቃ ማድረስ ኦርቶዶክሳዊ ነው የሚባለውን ክርስትና ነው፤ ክርስትና ብለው የሚሰብኩት።

አማናዊው ክርስትና!

ጠቢቡ፣ “ጻድቅ ሰው ለእንስሳው ነፍስ ይራራል፤ የኀጥኣን ምሕረት ግን ጨካኝ ነው።” (ምሳ. 12፥10) እንዲል፣ ጻድቅ እንኳንስ ለሰው ለእንሰሳ ነፍስ ይራራል፤ ኀጥአን ግን የሰው ሞትና መዋረድ፣ የሰው ጉስቁልናና ሰቆቃ ግድ የማይሰጣቸው እጅግ ጨካኞች ናቸው። የገዛ ነውራቸው ሳይታያቸው፣ ለስህተታቸው አህያ በመደብደብ ነቢይነታቸውን እንደ በለዓም ሊመሰክሩ ይወዳሉ። የእውነተኛ ክርስትና ወጉ ግን፣ “በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፉዎችና በበጐዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።” (ማቴ. 5፥44-45) በሚለው በመሥራቹ በኢየሱስ እውነት ያሸበረቀና የፈካ ነው።

ስግደት ለእግዚአብሔር ብቻ ነው! ያሉት ተገድለው፣ ስግደት ለማርያምና ለእንጨቱ መስቀል የሰገዱቱ እውነተኛ ነን ብለው ሰውን መግደላቸውን ሲናገሩ መስማት ያሸማቅቃል፤ ባያፍሩ እናፍርላቸዋለን። ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እንዲህ ያሉትን ካራ አውርድ አገልዮችን በመካከሏ ይዛ፣ እውነተኛ ወንጌላውያንና አማኞችን ማሳደዷ እጅግ ልብ ሰባሪ ተግባር ነው። ነገር ግን እውነተኛው ክርስትና የሚጠላውን አይጠላም፣ የሚንቀውን አይንቅም፣ አንዱን መጤ ሌላውን ቤተኛ አይልም። ይህ እጅግ ዓመጻና ትዕቢት ነውና!

አጭር ማስታወሻ!

ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ጀርባ፣ እንዲህ ያሉ አሳፋሪ ሰዎች መኖራቸውን ሳስብ፣ የምድሪቱን ጥልቅ ጨለማ አስተውላለሁ፤ ጌታ ኢየሱስ ይራራልን፤ ግብዞችንና ትዕቢተኞችን ያሳፍር ዘንድ፣ የእግዚአብሔር ምሕረት እንደ እኔ ለወደቁትና እጅግ ኀጢአተኞች ለኾኑ፣ በእስር ቤት ለተጣሉ፣ ሰው ኹሉ ፊታቸውን ላዞረባቸው … እንዲበዛ፣ እንዲትረፈረፍ የዘወትር ምልጃና እንባዬ ነው!

ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ባለመጥፋት ከሚወዱ ሁሉ ጋር ጸጋ ይሁን፤ አሜን። (ኤፌ. 6፥24)

 

18 comments:

  1. ለምን የራስህን ኑሮ አርፈህ አትኖርም የማታውቀውን አትዘባርቅ ከአንተም ብሶ ስለ ግብዝነት ታወራለህ ማቴዎስ ኢትዮጵያውስጥ ነው የተገደለው የሚል አንድ ማስረጃ አምጣ ሌላው ደግሞ እግዚአብሔርን ብቻ አምልክ እንጂ ለእርሱ #ብቻ ስገድ የሚል አንድ ማስረጃ ከቅዱስ መጽሐፍ አምጣ ሌላው ደግሞ የራስህን ቤት አጽንተህ ያዝጨየማታውቃትን ኦርቶዶክስ አንስተህ አታቡካ

    ReplyDelete
  2. ለማያቅሽ ታጠኝ አለ

    ReplyDelete
  3. ታሪክን ማጥፋት አይቻልም ካላወክ ዝም በል ።

    ReplyDelete
  4. አንተ አለህ አይደል እንዴ ክብሩን የካድክ መናፍቅ. አንተ ሰይጣን!

    ReplyDelete
  5. ጸረ ኦርቶዶክ ከቤተ ክርስቲያን ጠላቶች አንዱ አንተ ነህ ተወግዘሀል

    ReplyDelete
  6. GOD bless you for sharing Abiny. May the SPIRIT be your guide and strength for days to come!!!!!!

    ReplyDelete
  7. Abenezer Tenkolu Eski Zeme Belelu face book layi eyemetachihu atakershuben kefafayi hula

    ReplyDelete
  8. መናፍቁ ኮመንቴን ለምን ቆረጠክ የልብህን አደረስኩ መሰለኝ???

    ReplyDelete
  9. ርጉማን ስለማታውቁት ማኅበር አታውሩ የቤተክርስቲያናችን ጉዳይ የእኛ የልጆቿ ብቻ ነው ይውጣላችሁ ማኅበረ ቅዱሳን የቤተክርስቲያን ዓይኗ ነው የሚነኩት ሁሉ በስጋና ነፍሳቸው ተወራርደው የሚጠብቁት ልጆች እንዳሉት አትዘንጉ።

    ReplyDelete
  10. መናፍቁ ኮመንቴን ለምን ቆረጠክ የልብህን አደረስኩ መሰለኝ???

    ReplyDelete
  11. ውሸትና ሓሳውያን የሚፅፉልሕ እረጅምና በማስረጄና መረጃ ያልተመሰረተ መሰረተቢስ እንቶፉንቶ የዘመናችን ገንዘብና አፍቅሮነዋይ አምላኪ የቅባት ሐይማኖት የውጮች ብርዝ ነው።
    እጅግ የሚገርመኝ እነዚሕ የገንዘብ ቀበኞች ቅባታውያን ማሕበረ ቅዱሳንን በየትኛውም አድባራት ለማሳደድና ሊቃውንት ኣባቶችን በማግለል የእነሱ አጃቢ እያስገቡ በማደራጀት የአባቶቻችን ጥብቅ ክርስቲያናዊ ስርኣትን እያራከሱና እያኮሰሱ በእነሱው ዘመናዊ ቅባትነት ለመተካት የሚያደርጉት ጥረት መጀመሪያ ማሕበረ ቅዱሳንን እንደ ጠላት ማየታቸው ነው ።

    ReplyDelete
  12. ሲጀምር እንደ አንተ ያለው ቆሮቆንዳ ጸረ ቤ/ክ ፓስተር ምንም ስህተት እንኳን ቢኖር ማውራት አይችልም።

    ReplyDelete
  13. ከፊቱ አይደለም ካለበት ቦታ መቀመጥ በውስጥህ ያለው የውሸት መንፈስ ይጨነቃል!! ሰይጣን ለምን በማያገባው እንደሚገባ ጴንጤን ያየ ይገባዋል

    ReplyDelete
  14. ማህበረ ቅዱሳን ለአንተ አይነቱ መናፍቅ ማርከሻ ስለሆነ ገና ያቃጥለሐል!

    ReplyDelete
  15. እንኳን ልክ ነው

    ReplyDelete
  16. ያንተን ኢየሱስ አናውቀውም

    ReplyDelete
  17. በክደት ከሚጓዙት አይነ ብርሃኖች ልበ ጭፈኖች አንተ ጠብቀን ።

    ReplyDelete