Thursday 6 May 2021

ይድረስ እንደ እኔ ለነበራችሁ ኹሉ!

Please read in PDF

እኔ!

በአጭር ቃል፣ እኔ ትላንትና የክርስቶስን መካከለኝነት ነቅፌ የማርያምን መካከለኝነት አስተምር ነበር፤ የክርስቶስን መካከለኝነት ያስተምሩና ይሰብኩ የነበሩትን ነቅፍ፣ ሰድብ፣ በብርቱ ቃል ተች፣ አዋርድ ነበር። እኔ በማደርገው ንግግርና ድርጊት ሰዎች እስኪሸማቀቁ ድረስ ለብዙዎች የመሰናከልና የመውደቅ ምክንያት ነበርኩ። ማርያምን በዝማሬ አምልኬአለሁ፤ ወደ እርሷ ጸልይ፤ በስሟም እማጠን፣ አማልጂኝ ብዬም እለምናት ነበር። ለስእሏ እሰግድ፣ ለስሟም ስዕለት አስገባ፣ በመላእክት፣ ቅዱሳን ተብለው በሚጠሩ ፍጡራን ሰዎችና ቊሳት ኹሉ ስም አምልኮ እፈጽም፣ እግዚአብሔር ሩቅ እንደ ነበር፣ መዳንን በግል ጥረት ማግኘት እንደሚቻል ለዚህም ገዳም ለገዳም እንከራተትም … ነበር።

ቅዱስ ጳውሎስ፣ “አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምሕረትን አገኘሁ፥” (1ጢሞ. 1፥13) ብሎ እንደ ተናገረው እኔም፣ በቀደመ ዘመኔ ባደረግኹት እጅግ አስቀያሚና አሳዳጅ ሕይወቴ፣ ጌታ ኢየሱስ ምሕረት አድርጐልኝ እነሆ ተመልሼአለሁ። አስቀድሞ በማስተምረው ትምህርትና አደርግ በነበረው ድርጊቶቼ ኹሉ አፍራለሁ፤ እሸማቀቃለሁ፤ ከቶውንም እንደ አገልግሎት ቈጥሬው አልመካበትም። ከዚህም ባለፈ እንዲህ ሳስተምር በነበረበት ዘመን ያሳትኳቸውን ወንድሞችና እህቶች ባገኘኹበት ቦታ ኹሉ ይቅርታ ጠይቄአለሁ፤ ዕድሉን ባገኘኹበትም አጋጣሚ ኹሉ የጌታን የመዳን ወንጌል ሰብኬአለሁ።

ሌሎችስ?

በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ፣ ለማርያም ሲዘምሩ፣ ቅዱሳንን ሲሰብኩ፣ የክርስቶስን መካከለኝነት ሲነቅፉ፣ የሰዎችንና የቊሳትን መካከለኝነት ሲሰብኩ የነበሩ የዚያ ዘመን አገልጋዮች፣ ዛሬ ወንጌል እንሰብካለን፣ ወንጌል እንዘምራለን፣ ወንጌል እንመሰክራለን፣ ወንጌል እናውጃለን … ሲሉ እንሰማቸዋለን። አንዳንዶቹ ደግሞ በኦርቶዶክስ ቤት ያገለገሉት አገልግሎትና አኹን እያገለገሉ ያሉት አገልግሎት ምንም ልዩነት እንደሌለውና አንድ እንደ ኾነ ሲናገሩ እንሰማቸዋለን። እንዲያውም በዚያ ሳለን ያገለገልነው አገልግሎት ተደራሽነቱ ለብዙዎች ነበርና፣ አኹን ካለንበት ይሻላል በማለትም የሚሞግቱ አሉ።

እኒህ ብዙ ቊጥር ያላቸው “አንጋፋና ብዙ ተከታይ ያላቸው አገልጋዮች”፣ በዚያም ቤት ሳሉ ስለ ማርያምና ለፍጡራን ኹሉ ስለ ዘመሩትና ስለ ሰበኩት ስብከትና ትምህርታቸው፣ ይቅርታ ሲሉ ወይም ስህተት መኾኑን አፍረውበት ሲናገሩ ሰምተናቸው አናውቅም። የአገልግሎት መልክና ዘይቤአቸውን ሳይለቁ እዚህም እያገለገሉ መኾናቸውን እያስተዋልን ነው።

እንኪያስ ይህን ጥያቄ እንጠይቅ!

ለመኾኑ ትላንት ለማርያምና ለፍጡራን ኹሉ ለተዘመሩትና ሰዎች ፍጡራንን ላመለኩበት “መዝሙሮች” ተጠያቂው ማን ነው? ንስሐ ሊገባባቸውና ትክክል አይደሉም፣ እውነትን ይቃወማሉ፣ አምልኮተ ፍጡራንን ያበረታታሉ፣ ትላንት በዚህ መንገድ መሥራታችን ትክክል አይደለም፣ … ሊሉ የሚገባቸው እነማን ናቸው፣ የዘመሩቱ፣ ድርሰቱን የጻፉቱ፣ መሣሪያ የተጫወቱቱ፣ ዜማውን የደረሱቱ … ወይስ ማንኛቸው ናቸው?

እኒህ ኹሉ ከተጠያቂነት አይድኑም፤ እውነተኛ መመለስና ንስሐ እንዲኾንልን ከሻትን፣ ትላንት ትውልድ ያሳትንበትን ጠማማ መንገዳችንን፣ ደፍረን ጠማማ መኾኑን በመናገር ይቅርታ ልንጠይቅና እውነተኛነታችንን ልንገልጥ ይገባናል። ትላንት ፍጡራንን በማግነን ያገለገልነው አገልግሎታችንን ልናፍርበት፣ ልንጠየፈው፣ ልንኮንነው ይገባል፤ ዛሬ ደግሞ በእግዚአብሔር ጸጋ በመታመን የምናገለግለውን አገልግሎት ልንወደው፣ ልናከብረው፣ በቅዱስ ቅናትም ልንፈጽመው ይገባናል።

“ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ባለመጥፋት ከሚወዱ ሁሉ ጋር ጸጋ ይሁን፤ አሜን።” (ኤፌ. 6፥24)።


8 comments:

  1. May the SPIRIT be your guide and strength for days to come!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  2. ካለማወቅ ወደ አለማወቅ እኮ ነው የሄድከው ወንድሜ እኛ ኦርቶዶክስ በ40 በ80 ቀና ተቀብለን የምናመልከው እናቱን እንደ እናት የተቀበልን ነንአንተ የምትለው ሃይማኖት ውስጥ ያሉ ካሉ ግን ያው የጨብሲ ሲያጡ መንገድ ታገኛቸዋለህ ብዙ አትጨነቅ

    ReplyDelete
  3. አቶ አቤኔዘር ዲያቆን ያደረገችህ ቤተክርስቲያን ትምህርቷ ስህተት ከሆነ ዲያቆንነቱን ለምን አትተወዉም? ለምን ትጠራበታለህ? ልብሱንስ ለምን አታወልቀውም? ለነገሩ ልብሱን ካወለቃችሁት ተኩላነታችሁ ይገለጣል።እስካሁን ድረስ የመነፈቃችሁ ሰዎችን አንድ የሚያደርጋችሁ ምን እንደሆነ ታውቃለህ? ቤተክርስቲያንዋን ትሳደባላችሁ።መንፈሳዊ ስድብ መሆኑ ነው።

    ReplyDelete
  4. ወንድሞቼ በጣም ታሳዝናላችሁ ስምህን በዳቆን በሌላም የኦርቶዶክስ ስም እየሰየምክ ሰውን ለማሳሳት መሞከርህ ኪሳራህ ነው እንጂ ማትረፍህ አይዴለም እኛ የኦርቶዶክስ አማኞች በ5ቱ መስቀሎች በ12ቁጥር ቢስማር የተቼነከርን የማይነቃነቅ እምነት ያለን ነን ።ወንበዴና ነፋስና ጎርፍ የማይወስዴው እምነት ያለን ነን ።እንዴ መለኩሴው ይሁዳ እንዴ ፓፓሱ ንስጥሮስና አሪዎስ በስም መስሎህ ማታለሉ በእራስህ ላይ ካሪያ ማስቀመጥህ ነው ከብረት እሳት መቀመጥህን አስብ እግዚሃብሔር በቀላሉ እርስቱን አይሰጥም ለምን አንተ ትቢትህ ቀድሞ መላዓክት እንዴነበረው ሳጥናኤል ለእግዚአብሔር አልሰግድም ያልክ ነህ ።ለምን አንተ ዴግሞ በመጄመሪያ ክዴትህ የጄመረው በዩሃንስ ወንጌል 2:3 ላይ ውሃውን ወዴ ወይን ለምና እንድለወጥ ያዴረገችልንን ያማለዴችልልን የለመነችልንን እናታችንን ድንግል ማሪያምን መካድህ ነው ሲቀጥል እንዴ እግዚብሔር ጥምቀት ማቲ 13:3 ያልተጠመክ አንተ እራስህ ነህ ሲቀጥል ዴግሞ
    ማቲዎስ 10:38
    መሰቀሉንምው የማይዝ በኋላየም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም ።
    2ኛ ጴጥሮስ መልዕክት 2:1-4
    ነገር ግን ሀሰተኞች ነብያት ዴግሞ በህዝቡ መካከል ነበሩ እንድሁም በመካከላችሁ ዴግሞ ሀሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክዴው የሚፈጥንንጥፋት በእራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሏቸዋል በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባልገንዘብንም በመመኘትበተፈጠረ ነገር ይረቡባችሗል ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይምጥፋታቸውም አያንቀላፋም እግዚአብሔርም ሀጥያትን ላዴረጉመላዕክት ሳይራራላቸው ወዴ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው አንዱ አንተ ትሆናለህ።

    ReplyDelete
  5. ወንድሜ፡ሁላችንም፡እንደ፡አንተው፡ነበርን፡ኦርቶዶክሥ፡ለሚለው፡የአይማኖት፡መጠሪያ፡ሥምና፡ለማርያም፡ብለን፡እውነትም፡ሕይወትም፡መንገድም፡የሆነውን፡ኢየሱስ፡ክርሥቶሥን፡ሥናሳድደው፡ኖረናል፡አሁን፡ግን፡እውነት፡የሆነው፡እና፡የአይማኖታችን፡ጀማሪና፡ፈጻሚ፡የሆነው፡ኢየሱስ፡ክርሥቶሥ፡አግኝቶኛል፡ለካ፡መቀናት፡ያለበት፡ኢየሱስ፡ክርሥቶሥ፡ለሚለው፡ሥም፡ብቻ፡ነው፡እንኳንም፡የአንተ፡ልጅ፡ሆንኩኝ፡ኢየሱስዬ፡እውነታው፡ይሄው፡ነው

    ReplyDelete
  6. አብ ያልተከለው ይነቀላል .......ይላል ቅዱስ መጽሐፍ ሲኦል ሊቀ ሐጥዓን የለም ብለህ ነው ሣጥናኤል ይሾምሐል ሂድ
    ቤ/ንንም አውከሃት ነበር እኔ ብቻ አዋቂ እያልክ ወደሗላ ሳታይ ሒድ ሆዳም ሆድህ የፈነዳ እለት እንጃ ልህ.....!

    ReplyDelete