Thursday 20 May 2021

የእውነት ቃል አገልግሎትና የእምነት እንቅስቃሴ ተመሳሳይነት!

 Please read in PDF

የእውነት ቃል አገልግሎት፣ የእምነት እንቅስቃሴ አጋፋሪ ትምህርት ነው። የእምነት እንቅስቃሴ ትምህርቶቹ ኹሉ ሰውንና ራስን ወደ ማላቅ፤ ሰውን አምላክና አንዳች ልዩ ኃይል በውስጡ እንዳለ የሚያሞኙ፣ የሚያጃጅሉ፣ በምኞት የሚያስጎመጁና የሚያነኾልሉ “የከንቱ ከንቱ፤ ከንቱ ከንቱ ስብከቶችና ትምህርቶችን” የታጀለ አስተምህሮ ነው። ትምህርቶቻቸው ማዕከሉ ክርስቶስ መዳረሻውና ፍጻሜው የእግዚአብሔር መንግሥት መስፋት አይደለም።



በተመሳሳይ መንገድ የእውነት ቃል አገልግሎት አማኞችና አገልጋዮች፣ ዋና ማዕከላቸው ኢየሱስ፤ ፍጻሜ መዳረሻቸው ደግሞ የእግዚአብሔር መንግሥት መስፋት አይደለም። ትኵረታቸው፦

·        የጌታ እራት ከሌለ አምልኮ የለም የሚል ብርቱ መፈክር አላቸው። በዚህም የአምልኮ ማዕከል የኾነው ኢየሱስን በግልጽ በመግፋት ይታወቃሉ። ከዚህ ባለፈ ትንሽ ፈገግ የሚያደርገው፣ የጌታ እራት ለመፈጸም ደግሞ “ወይኑ ራሱ ወይን” መኾን አለበት የሚል እምነትም አላቸው[በአንድ ጉባኤ ላይ የእነርሱ ዋና ሰባኪ የነበረ ሰው፣ ባለ ጠርሙሱን ወይን ተሸክሞ መጥቶ በአግራሞት ተመልክተነው ነበር]። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ኢየሱስ ያለበት ጉባኤ ኹሉ፣ አምልኮ እደ ኾነ አጽንቶ ይነግረናል። ለአምልኮ ማዕከሉ ኢየሱስ ብቻ እንደ ኾነም ጭምር።

·        በኢየሱስ የተሰበከችው ወንጉል ኹለት ናት የሚል የማያባራ ከንቱ ክርክርም አላቸው። አንደኛዋ ወንጌል የአሕዛብ ሌላኛዋ ደግሞ የአይሁድ ናት የሚል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ የጸናችው ወንጌል አንዲት ናት ብሎ የምሥራች ይለናል።

·        ከኹሉም የኑፋቄ ኅብረቶች ጋር የሚያመሳስላቸው ሌላኛው አደገኛ ጠባያቸው፣ ወደዳኑት እንጂ ወዳልዳኑት ሲሄዱ አይስተዋልም። ልክ እንደ እምነት እንቅስቃሴ በወገናዊ ኑፋቄያቸው የሚያንዣብቡት (የሚረብቡት) በዳኑትና የጌታ በኾኑት፣ የጌታን አዳኝነትና ቤዛነት በተቀበሉት ወንድሞችና እህቶች፤ እናቶችና አባቶች ላይ ነው።

እኒህንና ሌሎችንም ሰፊ ልዩነቶችና የአስተምኅሮ ዝንፈቶችን “ያለ እውነት፣ የእውነት ቃል አገልግሎት!?” የሚለውን መጽሐፌን ጋበዝኩ!

ከሚመሳሰሉ ወንጌሎችና ኅብረቶች ተጠበቁ፤ ትኵረታችሁንና እይታችሁን ከኢየሱስና ከመንግሥቱ መስፋት አትንቀሉ! በጌታ መጽናትና መበርታት ይኹንላችሁ፤ አሜን።

 

1 comment:

  1. በማን ማልያነው የምትጫወተው መልስ እና ወደ አደራሽህ ግባ

    ReplyDelete