Wednesday 7 April 2021

ዳንኤል ክብረት፣ እውን ባንተ ግብር ተከሰሱ?

 Please read in PDF

 “… ኢየሱስ ክርስቶስም ተቃዋሚ ነበረበት፤ ሙሴም ተቃዋሚ ነበረበት፤ … ሌሎች ትልልቅ ሰዎችም ተቃዋሚ ነበረባቸው”

ይህን ቃል የተናገረው ዳንኤል ክብረት(“ቀሲስ”) ነው፤ የተናገረበትም ምክንያት፣ ከፋና ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ፣ “ካንተ ጋር የሚነሡ ክሶችን በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በተዘጋጁ ሰልፎች ላይ ኹሉ፣ ያንተን ፎቶ ኤክስ ምልክት እያደረጉበት ወይም አንተን እያወገዙ የተቃውሞ ድምጾችን እየሰማን ነው … ምንድነው ምላሽህ?” ለሚለው የሰጠው መልስ ነው። በርግጥ ዳንኤል ይህን መልስ አስተውሎ ስለ መመለሱ እርግጠኛ ነኝ።



ኢየሱስና ሙሴ በዳንኤል ግብር ነው የተከሰሱት?

ዳንኤል፣ ራሱን በጽድቅ ወደር ከማይገኝላቸው ኢየሱስና ሙሴ ጋር ማስተካከሉ፣ ምን ያህል ለኢየሱስና ለሙሴ ያለውን ንቀት ያሳያል። ሙሴ የብሉይ ኪዳን መካከለኛ ሲኾን፣ ኢየሱስ ደግሞ ብቸኛው የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው። በአጭር ቃል ነቢዩ ሙሴ፣ “ከግብፅም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለ ጠግነት እንዲኾን አስቦአልና ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ፤ ብድራቱን ትኵር ብሎ ተመልክቶአልና።” (ዕብ. 11፥25-26) የተባለለት ልከኛና ውድ፤ በዘመኑ ኹሉ አምላኩን አስከብሮ ያለፈ ብርቱ ነቢይ ነው!

ጌታችን ኢየሱስ ደግሞ በፍጹም ሰውነቱ አንዳች ነውርና በደል ያልተገኘበት፣ ጻድቅና ቅዱስ አምላክ ነው። ቅዱሳት መጻሕፍት፣ “ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። … ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ፤ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር።” (ኢሳ. 53፥7፡ 9)፣ “እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤” (1ጴጥ. 2፥22-23) በማለት፣ በአንድ ቃል እንከን አልባነቱን የመሰከሩለት፤ በሰማይና በምድር አንዳች ምስያ ያልተገኘለት የአብ የልቡን ፈጻሚ፤ ውድ፤ አንድና የብቻ ልጁ ነው!



የዳንኤል፣ ኢየሱስንና ሙሴን መናቅ!

ሙሴ በአንድም ቦታ ከምድራውያን መንግሥታት አብሮ፣ ዐሳባቸውን ደግፎ፣ ደም አፍሳሽነታቸውን ተስማምቶ አልቆመም፤ እንደ ቀደመው ኪዳን መርህ ከእግዚአብሔር ዓላማ ውጭ የእግዚአብሔርን ጦርነትን ከመዋጋት በቀር … አንዳች ክስ ቀርቦበት አያውቅም፤ የኖረውና ዘመኑን የፈጸመው ለእግዚአብሔርና እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ለማየት ፈጽሞ በመናፈቅና በብርቱ በመጠማት ነው።

ጌታችን ኢየሱስም፣ አንድም ቀን በቄሳር ቤተ መንግሥት መገኘቱን አራቱም ወንጌላት አይነግሩንም፤ ኢየሱስ ቄሳር ቤተ መንግሥት መገኘቱን ወንጌላት የነገሩን፣ በመጨረሻው ቀን ሞት ሊፈረድበት እጅና እግሩን ታስሮ ነው። የኢየሱስ የምድር ኑሮው፣ የቄሳርን፤ የዘመኑን ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍትን፤ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎችን ሕይወት የነቀፈና የተቸ ነበር። ኢየሱስ የተከሰሰውና በሕዝቡ ዘንድ የተጠላው፣ ባደረገው ጽድቅና በጐነት ብቻ ነው። የተከሰሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት በማስፋፋቱ ብቻ ነው። ጴንጤናዊው ጲላጦስና ሌሎችም የኢየሱስ ከሳሾችና ፈራጆች ደጋግመው መርምረውት እንደ ተናገሩት፣ ኢየሱስ በደል አልባ ጻድቅ ነው፤ (ማቴ. 27፥24፤ ዮሐ. 10፥33)።

ዳንኤል በርሱ ግብር ያልተገኙትን፣ ልክ በርሱ ግብር እንደ ተገኙ አድርጎ ማቅረቡ፣ የቅዱሳት መጻሕፍትን ሥልጣን ከመናቁም ባሻገር፣ ኢየሱስና ሙሴ እንደ እርሱ እንዲኾኑለት ይሻል። እንዲህ ያለ ኀጢአት በመዝሙረኛው አንደበት፣ “እኔ እንደ አንተ እሆን ዘንድ ጠረጠርህ፤” (መዝ. 50፥21) በማለት እግዚአብሔር የተናገረውን ጠቅሶ ይናገራል። ደፋር ኀጢአተኞች፣ እግዚአብሔርንና ቅዱሳኑን ወደ ራሳቸው አውርደው በራሳቸው ልክ ለክተው፤ ሊሰፉ ይወዳሉ። ነገር ግን ኢየሱስም፤ ሙሴም ቄሳርን በመወዳጀት አንዳችም ክስ አልቀረበባቸውም። ቀርቦባቸው፣ እኔም እንደ እነርሱ ተከስሻለሁ የሚል እርሱ ግብዝ ብቻ አይደለም፤ በቃሉ ላይ የሚጨምርና ቃሉ የማይለውን የሚል ሐሰተኛ፤ የቅዱሳት መጻሕፍት ባለቤት የመንፈስ ቅዱስ ተቃዋሚ ነው!

ጸጋና ሰላም በክርስቶስ ከማይጠፉት ጋር ይኹን፤ አሜን።

 

 

 

5 comments:

  1. የወረድክ መናፍቅ ዲያቆን ዳንኤል ሞቶም ይበልጥሀል ስም ብቻ የሙጥኝ ብለህ የቀረገህ አጭበርባሪ

    ReplyDelete
  2. አንተ በሽተኛ ፓስተር አቤኔዘር ተኩላው ዝም ብለህ ሆድህን አትሞላም ዘላለም ወደ አንድ አቅጣጫ በአፍህ ከምትጸዳዳ? እንደ አንተ ድንጋይ ገጥሞኝም አያውቅ። በሽታ
    ደግሞ የክርስቶስን ስም በተንኮል የሰከርክ ከርሳም ሰው ስትጠራ አለማፈርህ።

    ReplyDelete
  3. ይሄ ሰው 666 አወሬ ነወ ይሄ ሰው ዲያቆን አይሆንምም ሊሆንም አይችልም

    ReplyDelete
  4. አንተኮ ድፍረትህ የሌለ ነው ፡፡ መንፍቀህም ራስህን ዲያቆን ነኝ ትላለህ፡፡ ዳኒን ግን ለመተቸት ቢያንስ ማንነትህን አታውቅም፡፡ እንዳንተ ትናንሾችን ከመተቸት ተነስ፡፡

    ReplyDelete
  5. May the SPIRIT be your guide and strength for days to come!!!!!!

    ReplyDelete