Saturday 24 April 2021

ሆሳዕና - አኹን አድን ባክህ!

 Please read in PDF

የመከራው ዘመን አልዋገድ አለ

አድጎ ተመንድጎ ስቃይ ጎለመሰ

ቀንበራችን ሰባ

የሚያጎብጠን በዛ

ቀና ማለት ራቀን

የሞት ጽልመት ዋጠን!

ፊታችን ጠለሸ ጠቆረ ልባችን

መያያዝ ተሳነው አካል ብልታችን

እንኳን መድኀኒቱ ጠፋን በሽታችን

በድቅድቅ ጨለማ ጠፋ መብራታችን!

እባክህ ጌታ ሆይ!

ጆሮን የፈጠርከው ትሰማለህና

ዓይኖችህ በስስት ይጐበኛሉና

ስለ ስምህ ብለህ ስለ መግቦትህ

ቀጠሮ አታውቅም አኹን አድን ባክህ[ሆሳዕና]

የሟች ሞት አትፈቅድም ትቤዣለህና

ምስባክ ዝማሬያችን እንዲል ሆሳዕና

እባክህ!

ጠማማው ልባችን ይቅና ይፈታና!

1 comment:

  1. AMEN!!!! May the SPIRIT be your guide & strength for days
    to come!!!!!

    ReplyDelete