Saturday 10 April 2021

ማነው ታማኝ ባሪያ?

 Please read in PDF

ለንዋይ ለክብር ያልተንበረከከ

እዩኝ እዩኝ ማይል ምራቁን የዋጠ

ማለዳ ለወንጌል ሰርክ ለስብከቱ

ቃሉ እንደ ተዋበ በሕይወቱም ርቱ’[ዕ] …

ማነው ታማኝ ባሪያ ለኢየሱስ የቆመ

ራሱን የካደ በጌታ የታመነ?!

ለግሳንግስ ዓለም ጀርባውን የሰጠ

እርሱ ዝቅ ብሎ ጌታውን ያላቀ

ዓይኑ ፈዞ የቀረ ከመስቀሉ ችንካር

ሞት የማይበግረው የጌታ ባለሟል

እኮ እርሱ ማነው እንደ ጸና የቀረ

በሞት ላይ ተራምዶ ጽዮን ያማተረ?! …

እርሱ ነው ልከኛ እውነተኛ ባሪያ

በኢየሱስ እጅ ወድቆ በርሱ የተሠማራ!

2 comments:

  1. ጌታ አብዝቶ ይባርክህ ፀጋውን ያብዛልህ በርታ

    ReplyDelete
  2. እኛ የምናመልከው ከሰማየ ሰማያት የወረደውን ከድንግል ማርያም የተወለደውን በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ ያዳነንን፡ነው።
    አንተ የምታመልከው የአሜሪካ ባለሃብቶች ና አውቆ አበዶች የመሰረቱትን እየሱስ ።

    ReplyDelete