Sunday 17 February 2019

አርባ ምንጭና ተሰሎንቄአዊ ልቧ

በኹለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው፣ ቅዱስ ጳውሎስና ሲላስ ወንጌል በመመስከር ካለፉባቸው ከተሞች አንዷ ተሰሎንቄ ናት፤በአንፊጶልና በአጶሎንያም ካለፉ በኋላ ወደ ተሰሎንቄ መጡ፥ በዚያም የአይሁድ ምኵራብ ነበረ።” (ሐዋ. 171) እንዲል፣ ወደ ተሰሎንቄ እንደ ገቡ ያደረጉት እንደ ልማዳቸው ከቅዱሳት መጻሕፍት እየጠቀሱ ወንጌልን ማስተማር ነበር። የቅዱስ ጳውሎስና ሲላስም የምስክርነታቸው ማዕከልይህ እኔ የምሰብክላችሁ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነውየሚል ነው፤ ምክንያቱምክርስቶስ መከራ እንዲቀበልና ከሙታን እንዲነሣ ይገባው ነበርና

 ወንጌል ማዕከሉኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነውማለት፣ ከቅድስት ድንግል የተወለደው ኢየሱስ እርሱ መሲህ፣ ብቃት ያለው ብቸኛ አዳኝ፣ አብ የረካበትና የተቀበለው ውድ መሥዋዕት፣ ለኃጢአታችን የሞተ ሊያጸድቀን ደግሞ የተነሣ ጌታና አምላክ ነው የሚል ነው፤ እርሱ ኢየሱስ ከድሃ ቤተ ሰብ የተወለደ ድሃ ብቻ አይደለም፤ ቤት ያልነበረው ከርታታ ብቻ አይደለም፤ ኀጢአተኞችን ወዳድ ርኅራኄን ገንዘብ ያደረገ ትሁት ብቻ አይደለም፤ ሲያዩት ምንም የማይወደድ ነገር ያለው የሚመስል ብቻ አይደለም፤ እርሱ ብቻውን አዳኝ፣ ብቻውን ፈዋሽ፣ ብቻውን አስታራቂ፣ ብቻውን መካከለኛ፣ ብቻውን ብቁ ቤዛ፣ የተትረፈረፈ ዋጆአችን ነው።
 ቅዱስ ጳውሎስ ይህን እውነት በተሰሎንቄ ባስተማረበት ወቅት፣ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ብቃት ያለው አዳኝ ነውበማለቱ፣ የግሪክ አሕዛብ ወገኖች ከቅዱስ ጳውሎስና ከሲላስ ጋር ተባበሩ፤ አመኑ። የተሰሎንቄ አይሁድ ግን ለሕጉ ቀንተው በጳውሎስና በሲላስ ላይ ክፉ የኾኑ ሥራ ፈቶችን ሰብስበው ከተማውን በማወክ ወደ ሕዝቡ አውጥተው ለመደብደብ ተነሳሱባቸው። እናም ጳውሎስና ሲላስንባላገኙአቸውም ጊዜ ኢያሶንንና ከወንድሞች አንዳንዶችን ወደ ከተማው አለቆች ጎትተውአወጡአቸው። እናም ከተማውን ሠላም ነስተው ያወኩት እነርሱ ኾነው ሳለ፣ ቅዱሳን ሐዋርያትንና ያመኑትን ኹሉ ግንዓለምን ያወኩ እነዚህ ወደዚህ ደግሞ መጥተዋል፥በማለት ከሰሱአቸው።
  ጠላት ዲያብሎስ ኹል ጊዜ የተሸነፈ መንገድን ይከተላል፤ ቅዱሳንን ሲያሳድድ፣ ስማቸውን ሲያጠፋ፣ በሐሰት ሲከስ፣ ሲደበድብ፣ ሊገድል ሲሞክር፣ ሲገድልየሚያሸንፍ ይመስለዋል፤ በዚህም ድል እንደ ነሣ ሊቈጥር ይቃጣዋል። እናም ከልክ ያለፈ ኃይልን በመጠቀም የወንጌልን ሥራ ለማቆም፣ ለማሰር፣ እንዳይፈጥን ለማድረግ ይጥራል፤ በተቃራኒው ግን ወንጌልን በተቃወመበትና እንዳይሰበክ ባደረገበት ልክ፣ ወንጌሉ ከጫፍ ጫፍ በተቃውሞ ብዛት እንደሚናኝ፤ እንደሚያሸንፍ አያስተውልም። ሰይጣን ለዘመናት የሚወድቅበትና የሚሳሳትበት መንገድ ቢኖር ይህ ነው፤ ወንጌል እየተቃወመ በጥላቻ ወንጌልን ያሰብካል፤ ያስተዋውቃል።
  አርባ ምንጭ የኾነው እንዲህ ነው፤ ወንጌል ለማገልገል የሄዱትን ወንድሞችኦርቶዶክሳውያን ነን ያሉ ሥጋውያን ቀናተኞችአስቀድመው ተዘጋጅተው በመግባት ንብረት ዘረፉ፣ ሰው ደበደቡ፣ ከተማ አወኩ፣ ወንድሞችን አሳሰሩ፣ ጉባኤውን በተኑ። እኒህኦርቶዶክስን እንወክላለንየሚሉ አካላት ለምን መደብደብን ልማድ እንዳደረጉ ይገባናል፤ ለምን ራሳቸው ከተማ አውከውሃይማኖታቻንን ደፈሩብንእንደሚሉ እናውቃለን፤ ለምን ኹል ጊዜ በጥላቻ ቆመው ለማሸነፍ እንደሚጥሩ እንረዳለን፤ ወንጌል እንዲህ ባለ መንገድ እጅግ እንደሚበዛና እንደሚሰፋ ስለማያውቁ ነው። ወንጌል የተዳፈነ እሳት ነው፤ ሲነካኩት ይብስበታል እንጂ፤ ይጋጋማል እንጂ፤ ይንቦገቦጋል እንጂ ፈጽሞ አይጠፋም፤ አይከስምም፤ አይዳፈንም።
 መደብደብ፣ የሰውን ንብረት መንጠቅ፣ ማሳሰር፣ የሰውን አምልኮ መረበሽ፣ ማወክየሽንፈት ውጤት ነው። እውነተኛ አማኝ የክርስቶስ ልብ ስላለው የሞተ ነው፤ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ኹሉን ማድረግ እየቻለ ምንም አላደረገም፤ የአባቱን ፈቃድ ለመፈጸም ፍጹም ታዛዥና እንደሚታረድ በግ ዝም ያለ ነበር። እውነተኛ ክርስቶሳውያን የሚሄዱበት መንገድ ይህ ነው፤ ክርስቶስ እየሞተ ሰይጣንን፣ ሞትን ኀጢአትን ድል ነሣ፤ እውነተኛ አማኝም እየሞተ፣ እየተሰደደ፣ እየተደበደበ፣ እየታሰረ፣ እየተነጠቀ፣ መብቱ እየተገደበወንጌልን ይመሰክር ዘንድ ይገባዋል።
 በክርስቶስ ስም መከራ መቀበል ቅንጣት ታህል ውርደትና ሽንፈት አይደለም፤ አርባ ምንጮች ሆይ! በመደባበባችሁ፣ ንብረት በመዝረፋችሁ፣ ወንድሞችን በማሳሰራችን ያሸነፋችሁ አይደላችሁም፤ ይልቁን በጣም እጅግ በጣም የተሸነፋችሁና የተበለጣችሁ መኾናችሁን እመኑ። ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በእንደ እናንተ አይነቱ ትሰደብ፣ ትወቀስ፣ ትተች፣ ትናቅ፣ ትዘለፍ፣ ትዋረድ፣ እንደኾን እንጂ ፈጽሞ አትከበርም፤ ትከስር እንደኾን እንጂ አንዳችም አታተርፍም።
   ባለፉት ጥቂት አሥርት ዓመታት የቤተ ክርስቲያኒቱ አማኞች ቁጥር ያሽቆለቆለው እንዲህ ባሉ ወራዳ ተግባራት፣ በእውነተኛይቱ ልጆቿ ላይ አጸያፊ ጥቃት ተፈጽሞና ተገፍተው ነው፤ ከመጠጥ፣ ከሲጋራ፣ ከመሸታ ቤት፣ ከዝሙት፣ ከሥጋ ሥራ ሳይለያዩና በክርስቶስ ሕይወት ሳይመላለሱ፣ ድንጋይ ጨብጦ፣ ቁጣ ለብሶ፣ በሥጋዊና በጥላቻ ልብ ታውሮ በወንድም ላይ እንዲህ ያለ አጸያፊ ተግባር መፈጸምኦርቶዶክሳዊነትሳይኾን አላዊነት፣ አረመኔአዊነት፣ ግብዛዊነት፣ ክርስቲያናዊነት ነው። ቤተ ክርስቲያን ነገም በዚህ ተግባሯ የምትቀጥል ከኾነ ከክርስቶስ ጋር ለአንድያው ትለያያለች። የንስሐ ደጇንም በራሷ ላይ ትዘጋለች፡፡
   በእስር ላሉ ለአርባ ምንጭ ወንድሞች፣ እጅግ ተደብድበው ሆስፒታል ለገቡት ወንድሞችና እህቶች የጌታ ጸጋ እንዲበዛላቸው እንማልዳለን፤ በመደብደባቸው፣ በመታሰራቸው፣ በመጠላታቸው፣ በመገፍተራቸውአናዝንም፣ አንሰቀቅም፤ ዋጋቸው በሰማይ ታላቅ ነውና!!! ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲን ሆይ! በተሰሎንቄአዊ ልብ ክርስቶስንና ደቀ መዛሙርቱን፣ ወንጌሉንና ምስክርነቱን መግፋት ፈጽሞ አይረባሽም!!! መሲሑ ኢየሱስ ምሕረት ያደርግልሽ ዘንድ እንማልዳለን፤ መንፈስ ቅዱስም ልብሽን ያብራው፤ አሜን።


13 comments:

  1. ዘርህ ይጥፋና ዘላለም የሚትባል ስለ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ታሪክ ምንታዉቃለህ? መኻይም ኦርቶዶስን ለማጥላላት ነዉ? ልጁስ ብሆን ስለወንጌል ነዉ የደመዉ? ይሄኔ የኦርቶዶክስን ንብረት ያለ አግባብ ይዞ ብገኝ ነዉ እንጅ። ለንዳንተ ላሉት መድኃኒቱ ይሄ ነው ።

    ReplyDelete
  2. ዘርህ ይጥፋና ዘላለም የሚትባል ስለ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ታሪክ ምንታዉቃለህ? መኻይም ኦርቶዶስን ለማጥላላት ነዉ? ልጁስ ብሆን ስለወንጌል ነዉ የደመዉ? ይሄኔ የኦርቶዶክስን ንብረት ያለ አግባብ ይዞ ብገኝ ነዉ እንጅ። ለንዳንተ ላሉት መድኃኒቱ ይሄ ነው ።

    ReplyDelete
  3. ሁሌ ከመክሰስ! ከመቃወም የማትወጡ ውሸታም! ከሀዲ! የውሸት አባቶች! አምላክ ባፍጢማችሁ ይድፋችሁ!

    ReplyDelete
  4. ሁሌ ከመክሰስ! ከመቃወም የማትወጡ ውሸታም! ከሀዲ! የውሸት አባቶች! አምላክ ባፍጢማችሁ ይድፋችሁ!

    ReplyDelete
  5. ወንድሜ ሌባ ተይዞ ዱላ አይጠየቅም የሚባለው ነው የደረሰባቸው፡፡ በጠራራ ፀሐይ መንግሥት ባለበት አገር የታላቂቱን እናት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ገንዘብ መዝረፋችሁ አንሶ ማንነቷ የሆነውን መገለጫዋን ንዋየ ቅድሳትዋን ወደ አዳራሽ ስታግዙ አይቶ መታገስ ኃጢአት ነው፡፡ የእስከ ዛሬው እጅግ የበዛ ትእግስት እዚህ ደረጃ አደረሳችሁ ዛሬ ዝም ብትባሉ ደግሞ ነገ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑንም አስረክቡን ማለታችሁ የማይቀር ነው፡፡ የእናት ጡት ነካሾች ሆይ በቤተ ክርስቲያን ጉያ ተወሽቆ ተመሳስሎ በማሳሳት ከመኖር ይልቅ ሚናችሁን ለይታችሁ ራሳችሁን ሆናችሁ ለምን ያመናችሁትን አትሰብኩም? ያ መብታችሁ ነው፡፡ በዶሮ ማልያ ለአሞራ መጫወት ግን ወንጀል ነው፡፡

    ReplyDelete
  6. አታፍሩም! ይሄኔ ስለ ወንጌሌ ተደበደበ ትሉ ይሆናል።

    ReplyDelete
  7. stupid !
    do whatever the hell u want .
    But stop pretending , u r not orthodox ! so don't use our things !
    I don't recommend attacking people , but u shouldn't provoke violence by pretending to be orthodox !

    ReplyDelete
  8. የራስህን የለህ ማን በሰዉ አጊጥ አለህ:: ዶግማዋና ቀኖናዋን ንቀህ በንዋየ ቅዱሳኑ ማላገጥ ምን የሚሉት ዉንብድና ነዉ? ከፈለክ የኢዩ ጬፋ ዉራጅ ሱፍ አፈላልግና ቀልድ:: የሌባ አይነደረቅ

    ReplyDelete
  9. በአንተ ቤት አሁን ትክክል ነው። በዚያው በአዳራሽህ ጨፈር፡ ሲጀመር ምን የሚሰረቀ ነገር አላችሁና ነው ለማንኛውም እውነተኛው አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ ልቦና ይስጣችሁ።

    ReplyDelete
  10. Hmemachu yebezal gena yketlal because ktatu kelay kesemay new,hahahaha…………… yesetan chifra hula

    ReplyDelete
  11. ከሁሉም ያሳቀኝ " . . . ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ን ሆይ . . . መንፈስ ቅዱስ ልብሽን ያብራው " ያልከው ከወጣችሁ ጠቅልላችሁ መውጣት ነው ድሮም ከእኛ ጋር አልነበራችሁም ከእኛ ዘንድ ወጡ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ኑሮ ከእኛው ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ”ይላል (፩ኛዮሐን፪÷፲፱) እናንተ ለምን የሰው ትቀላውጣላችሁ? ሌባ ደግሞ መቅመሱ አይቀርም ሌቦች!

    ReplyDelete
  12. መዘምር ወንድሜ ፦ከእስጢፋኖስ አይበልጥም ።የኢየሱስ ፍቅር እንዲህ ያደርጋል ። ጌታ ይቅር ይበላቸዉ ። ይችናት ኦርቶዶክስ ።

    ReplyDelete
  13. አንድ ነገርያልገባኝ ነገር ኢትጵያኦርቶዶክ ቤተክርስትያን ድርጊቶች ከተፈጽሙበኃላ እንድሆነብላችሁ የምትነገሩት
    ለምንድነው ድርጊቶ ልፍጽሙሲሉ የማታደጉት ህግ ወጥ የስርግ ስርአት ከተፈጽመበኃላ
    ህግ ወጥ ቀኖና ወይም ዶግማ ብላ የምጠረዋ ቤትክርስቲያ ቀኖነዋም ዶግማዋም ከጠፍበላ እንደዚህማለት ምንይጥቅማል ለአለም መሳቂያ መሳለቂ ከሆነበላይ ለመነፍቃ መተረቻ ከሆነበኃል ለእኛ ምን ይጥቅመናል ሳይሆንና ድርጊቶ ሳይ ፍጽም ነብር ይሄን ማስቆም ራሱ ፎቶአሽው ይሄን ነገር ካውቀ አይሆንም ይሄስርአት አይደለም
    ካሜራም ቀራጩ አይሆንም ይሄ ስራ አተ ቤተክርስቲያን አይደለ ቢል ምነው
    መራጃውን ለማድርስ መፍጥን ሳይሆን መጥፎ ድርጊቶችን ማስቆም መፍጠን አለብን

    ReplyDelete