Tuesday 19 February 2019

ኢትዮጲያ በግልጥ ኢየሱስን ለመከተል ከአስቸጋሪ አገራት መካከል ስትመደብ!

Please read in PDF

 ምድራችን ኢትዮጵያ ኢየሱስን በግልጥ ለመከተል አስቸጋሪ ከኾኑት ከዓለማችን አገራት 29ኛ ደረጃ ላይ መገኘቷን ያውቃሉ? አዎን ምድራችን ብዙ ሃይማኖተኛ ሕዝብ ቢኖራትም ነገር ግን ለክርስቶስ ኢየሱስና ለኢየሱስ አማኞች ምቹ ምድር አይደለችም፡፡ ምድራችን ኢየሱሳውያንን፣ በኢየሱስ የሚያምኑትንና ስሙን ወደው የሚጠሩትን ታሳድዳለች፣ ታንገላታለች፣ የመንቀሳቀስ ነጻነታቸውን ትነፍጋለች፣ ትደበድባለች፣ ንብረት የማፍራት መብታቸውን ትነፍጋለች፣ ኢየሱሳውያን[የኢየሱስ ትውልዶች] መከራቸው ዛሬም አለ፡፡


  ጥናቱ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በገዛ ልጆቿ ላይ የምታደርሰው ስም ማጥፋት፣ መከራና ሰቆቃን ቢያካትት ኖሮ የቁጥራች ደረጃ አስፈሪ ደረጃ ላይ አይደርስም ትላላችሁ? ኢየሱስ በዘመናት ልዩነት ያደርጋል፤ ለስሙ በእውነት ዋጋ የምትከፍሉ፤ እጅግ ደስ ይበላችሁ! ጸጋ ይትረፍረፍላችሁ፤ አሜን፡፡

    “እናንተ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በይሁዳ የሚኖሩትን በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉትን የእግዚአብሔርን ማኅበሮች የምትመስሉ ሆናችኋልና፤ እነርሱ ከአይሁድ መከራ እንደ ተቀበሉ፥ እናንተ ደግሞ ያንን መከራ ከአገራችሁ ሰዎች ተቀብላችኋልና። እነዚያም ጌታን ኢየሱስን ደግሞ ገደሉ ነቢያትንም እኛንም አሳደዱ፥ እግዚአብሔርንም ደስ አያሰኙም፥ ሰዎችንም ሁሉ ይቃወማሉ፥ ሁልጊዜ ኃጢአታቸውን ይፈጽሙ ዘንድ አሕዛብ እንዲድኑ እንዳንናገራቸው ይከለክሉናልና። ነገር ግን ቍጣው ወደ እነርሱ ፈጽሞ ደርሶአል።” (1ቆሮ. 2፥14-16) 

1 comment: