Wednesday 27 February 2019

ነይ ይልሻል ቶሎ

ሩቅ አስበሽ ቅርብ አዳሪ
አንቺ “ሴት እንተኛ አዳሪ” …
ተኝቼ ካልጋዬ ጐኔን ወጋኝ ድንገት
ሳስብ ስቃይሽን በሰመመን ቅጽበት
እንዴት ነው መቻሉ ምኑን ከምን አርገሽ?!
ያንን የስቃይ ጣ’ር ኹሌ ማቃሰትሽ …
ኅሊናሽ ተጨንቆ
አካልሽ ተሳቆ
ለማይጥም እንጀራ አፍሽ በጥም ደርቆ …
ምነዋ እህቴ ተይ እንጂ ተይ እንጂ - ፍጻሜሽ ይከፋል፣
ከምክንያትሽ በላይ ኢየሱስ ይበልጣል፡፡
ደግሞም …
የአካልሽ ጌታ ብዙ ይታገሳል
ነይ ይልሻል ቶሎ እጁ ተዘርግቷል
የንስሐ በሩን ስላ’ንቹ አስፍቷል፡፡




2 comments:

  1. የንስሐ በሩን ስላንቺ አስፍቷል አሜን

    ReplyDelete