አልማዝ ወርቅ እንቁውን፣ በኲራቱ ያደበሰ፤
ዘረ አዳምን አስጎንብሶ ፣ ብርታት አቅሉን ያፈረሰ፤
ትልቁን ቁጥር በራሱ ምጥ፤
በማጣደፍ በማሯሯጥ፤
የሚነዳ፤
የሚገዛ፤
ጥቂቶቹን ወደክብረት ፣የሚያጓጉዝ ወደእረፍት፤
ሞት ገበሬ ፣ ሲያበራይ ፣ መች ይዝላል?
ጠይም አፈር፣
ዳማ አፈር፣
ጥቁር አፈር፣
ወዛምና አመዳሙን፣
ህጻንና ሸበቶውን፣
ሲያመላልስ ፣ መች ይዝላል?
ሞት ደግ ነው፤ በየደጁ በር ያንኳኳል፤
ወርቅ ፣ ጠጠር
ፍህም ፣ አመድ
ሳር ፣ ገለባ
ፍሬ ፣ እንክርዳድ
ሲያመላልስ መች ይዝላል?
… ይታክታል?
እንኪያ እናስተውላ …
ፊተኛው ሞት፣ መሰልጠኑ በሁላችን ቢቆጠርም፤
በኋላው ሞት እንዳንዋጥ ፣ የዋጠውን እንመነው ለዘላለም፤
አሜን፦ ጌታ ኢየሱስን እናምልከው፡፡
No comments:
Post a Comment