Thursday 28 April 2016

ትዝታዬ ሁነኝ


                                         Please read in PDF

ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት መታሰቢያ በዓል እንኳን አደረሳችሁ፡፡


ሁሌ እራገማለሁ የአይሁድን ጥላቻ
ጌታ ኢየሱስን …
ለምን ጠሉት? ብዬ ሙግት ማንሳት ብቻ
ለምን ነው ይሁዳ? ለምን ነው ጲላጦስ?

እንጀራ የበሉ እኒያ ሁሉ አይሁድ፥
                    ደግሞም፥ ያ ፌዘኛው ሄሮድስ
ለምን አደረጉ ንጹሕ ሰው ሊገድሉ?
በቀንም በማታ በሸንጐ መከሩ?
እያልኩ በልቤ ሙግት አቀርባለሁ ፤
ዓመጸኞች እያልኩ ሁሉን እነቅፋለሁ፡፡
አሳዛኙ ነገር …
ከዚህ ሁሉ ድርጊት ነፍሴ ግን ሳትማር ፤
ከገዳዮች ጋራ ቆማለች እሳት ዳር፡፡
አቤቱ ኢየሱስ ሆይ!
ትዝታዬ ሁነኝ ስጠፋ እንድመለስ ፤
በኰነንኩት ኃጢአት እኔው ደግሞ እንዳልረክስ፡፡


No comments:

Post a Comment