ይህንን ፎቶ ሳይ፥ ደንግጬ ክው ብዬ ነው የቀረሁት!!! ማን ያምናል ኢትዮጲያውያን “ግብረ ሰዶም በመጽደቁ ደስ ብሏቸው ሰልፍ ወጡ
፤ ወይም እንዲጸድቅላቸው እነርሱም ሰልፍ ወጡ” ቢባል?! ግን ይኸው ሆኖ አየን፡፡
ኢትዮጲያ
ገና ዳቦ ያልተዳረሰባት አገር ናት ፤ ኢትዮጲያ ገና የፍትሕ ጥያቄ በሚገባ መልስ ያላገኘች አገር ናት ፤ ኢትዮጲያ ገና ከሙስና
ለመላቀቅ የምትታትር አገር ናት ፤ ኢትዮጲያ ገና ለዕድገት ከህልም እንደሚባንን ጎልማሳ የነቃችበት ወራት ላይ ናት፡፡ ይህንን ብቻ
ያይደለ ህዝባችን ገና ከተጣባው የመንፈሳዊነት ዝለት ቀና ማለት የጀመረበትና ቤተ ክህነትም ድካሙን አይቶ ቀና እንዲልና በመንቃት
ለምዕመናን እንዲያስብ ደወል እየተደወለበት ያለበት ወራት ላይ ነን፡፡ ይህን ያለብንን ድካም የሚያግዝ የኢትዮጲያዊ ዲያስፓራ ዕርዳት
ኢትዮጲያ ትሻለች፡፡
እንዴት ሁሉ ጠግቦ እንዲያድር ለዜጎቿ ዳቦ መዳረስ እንዳለበት ፣ ፍትህ
በማጣት የሚቅበዘበዘውና እንባው ያልታበሰው ህዝቧ እንዴት ፍትህ ማግኘት
እንዳለበት ፣ የሚበዛው ስግብግብ ባእለ ሥልጣን ከተቀመጠበት የሙስና ዙፋን ላይ ወርዶ ግብረ ገቡ እንዲቀመጥ የሚሠራ የዲያስፖራ
ዕውቀት ፣ ገንዘብ ፣ ጥበብ ፣ ልግስና … ኢትዮጲያ በእውነት ትሻለች፡፡ አዎ! በመንፈሳዊ ማንነቷም እንደንስር በሮ በማይደክም
ክንፍ እንድትበርር ኃይሏን በማደስም እንድትሮጥ የሚያደርጋት አቅምና መንፈሳዊ ጥበብ ከኢትዮጲያውያን ዲያስፖራዎች ትሻለች፡፡
ያየነውና የሰማነው ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ኃይል
ያጣና የተሰበረ ይሁን!!! አስደንግጦናል ፤ ጆሮዋችንን ጭው አድርጎታል፡፡ አዎ! እጅጉን በሚሰብር ሃዘን ልባችን ተመቷል፡፡ ግብረ
ሰዶም እንዲጸድቅ ሰልፍ ከወጡ አሜሪካውን ጋር “የእኛም ኢትዮጲያውያን” ዜጎች ባንዲራችንን ይዘው ደግፈው መውጣቻው ሰብሮናል ፤
በእውነት ልባችንን አድምቶታል ፡፡ አዎ! እኛ ኢትዮጲያውያን የተራበ ሆዳችንን እያከክንም ሆነ ጠግበንም ስለ ርኩሰት ፤ ግብረ ሰዶም
ከእናንተ መስማትም ማየትም አንሻም፡፡ ሁሉን ዲያስፖራ ማለቴ አይደለም ፤ ነገር ግን ርኩሰትን ባለማፈር በአደባባይ ስለሚያስፋፉ
ዲያስፖራውያን እላለሁ፦ ሕያው እግዚአብሔርን በሕያው ነፍሴ እምላለሁ፦ ለኢትዮጲያ የሚያስፈልጋት “ግብረ ሰዶማዊነትን የሚያጸድቅ ሰላማዊ ሰልፍን መሳተፍና ማሳተፍ አይደለም”፡፡
ምነው! ያ ትምክህት ወዴት ሄደ? ምነው “ግብረ ሰዶማዊ ሁን ካለኝ ኦባማ
፤ መጀመርያ እኔ እሱን ነው የማገባው” ካለው ዚምባቤያዊ ፕረዘዳንት “የቅድስትና የክርስቲያን ደሴት ላይ ነው የምንኖረው” ብለን
የምንሸልለው አንሰን ተገኘን? ምነው ቅዱስ ጋብቻ እንዲህ ረከሰብን? ምነው ዘር መተካት እንዲህ አሳፈረን? ምነው በርኩሰት ነዶ
ለመኖር ብቻ እንዲህ አመጽን? በእውኑ ኃጢአት አምነናል ፤ “ከእኛም ወዲያ እምነትና ክርስትና” ለምንል ለእኛ መብት ነበረንን?
በእርግጥም ጊዜው ረፍዶብን ይሆንን ብዬ እሰጋለሁ? ያደፈጡ ግብረ ሰዶማውያን
በመካከላችን ኦቀጥቁጠው አደባባይ ለመውጣት ሰባራ ቀን ብቻ እየጠበቁ ይሆንን? ዲያስፖራዎቻችንን ካለማመን ባንደርስ እውነት አይሆንን?
ትላንት ሴት ልጃቻችንን ከባለጌ ወንዶች ለመጠበቅ ነበር ድካማችን ፤ ዛሬ ግን ወንዶች ህጻናቶቻችንን ከወንዶች መጠበቅ እጅግ ሊያደክመን
ነውን? አዎን! የራቀው ምነው እንዲህ ገስግሶ ከደጃችን ደረሰ? ዲያስፖራዎቻችን በውጪ ያደረጉትን ግብረሰዶማዊ ሰላማዊ ሰልፍ በእኛም
አገር ሊያደርጉ አይነሳኑም ብለን ተሞኝተን አንቀመጥም፡፡ አዎን አናምናቸውም!!! አዎን! በብዙ መጸለይ ፤ እንደገና በብሔራዊ ንስሐ
ራሳችንን ማየት ያለብን ጊዜ ከመቼውም ጊዜ አሁን ነው እላለሁ፡፡
ጌታ ሆይ! የሚቸኩለውን ርኩሰት አየኸውን? አቤቱ የተጀመረው የነውርና
የኃጢአት ፤ የርኩሰትም መንገድ ሳይጨረስ ድረስልን? አቤቱ ለአለሙ ሁሉ የክፋት ምሳሌ የሆኑትን አገሮች አንደገና አስባቸው፡፡ የእንደገና
ጌታ አቤቱ እንደገና ወደልባችን መልሰን፡፡ አሜን፡፡
be blessed brother. you are doing great
ReplyDelete