Monday 13 July 2015

መሞቱ ጥቅም ነው!


                      Please read in PDF   

የ“እኔ አልክድህም” ፣ ስሜታዊ ግለት ፤
ቀደም ቀደም የሚል ፣ የእዩኝ ማንነት ፤
አንተ ደግ መምህር !
አትሞትም ይቅር ! …

“አማኑኤል ሁነኝ” ፣ አትራቅ ካ'ጠገቤ ፤
እያለ 'ሚሞግት ፣ ቅን መሳይ እሳቤ ፤
ከእግዚአብሔር አይደለም ፣ ከሰማያት ዕቅዱ ፤
አብ ተስማምቷልና ፣ በኢየሱስ ሞቱ፡፡
በለዘበ ንግር ፣ በለሰለሰ ቃል ፤
አዛኝ ነኝ እያለ ፣ መንፈስን በማዛል ፤
ቀርቦ 'ሚያለቅሰውን ፣ መልካም ቃልን መርጦ ፤
ላ’ንተ እየሳሳ ፣ ከራሱ አብልጦ ፤
ሲመጣ ገስጸው ፣ የጴጥሮስን ምላስ ፤
ከመኖሩ ይልቅ ፣ መሞቱ ጥቅም ነው ፣ ጌታችን ኢየሱስ፡፡


No comments:

Post a Comment