Friday 24 July 2015

አይበቃም እኮ!


                               Please read in PDF                                           

ልንበላላ ፣ ልንነካከስ ፤
ልንቋሰል ፣ ልንቦዳደስ ፤
ላንተዛዘን ፣ ልንከፋፋ፤
ተጨካክነን ፣ ልንጠፋፋ፤

   
በህይወት ጽዋ ፣ መርዝ ልንቀምም፤
በኩነኔ ቃል ፣ ልንረጋገም፤
ለዚህ ይቅርና ፣ ይህች የ‘ኛ ዕድሜ፤
አትበቃም እኰ ፣ ለመፈቃቀር  ፣ ያለ ቅያሜ፡፡

በዕድሜ እራፊ ፣ በዘመን ጢቢኛ፤
መች ጠገብነው ፍቅርን ፣ ተሳስበነው እኛ፤
አይበቃምና ፣ የዚህ ዓለም ቀኑ ፤
ከጠብ ተፋቱ ፣ ለፍቅር አንድ ሁኑ፡፡


No comments:

Post a Comment