Saturday 2 August 2014

ብትሮጥም አክሊል የማትደፋው …


Please read in PDF

ፍቅርና ርህራሄ፣ ደስታና ቸርነት፤
የውሃት፣ ቅንነት፣ የበዛ ምህረት፤
ለማድረግ ምክንያቶች የምትደረድረው፤
እኔ በሚል ብቃት ለማድረግ ‘ም‘ጥረው፤
እንዳይመስልህ ፍጹም አንተ የምትችለው፡፡


መልካሙን በጎውን ባ‘ንተ የሚሠራው፤
ደሙና መንፈሱ፤ ያ‘ንተ መታዘዝ ነው፡፡

ከ‘ኒህ ተለይተህ በራስህ ካሰብከው፤
ክብር አልባ ፍትጊያ የራስህ ጽድቅ ነው፤

ለዚህ ነው ብትሮጥም አክሊል የማትደፋው!!!

6 comments:

  1. No doubt about it.Well done ,what a wonderful thought .Be blessed.

    ReplyDelete
  2. ከተሃድሶ መናፍቃን ተጠበቁ
    የክህደት መካነ ድር- “የዲ/ን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ” -
    ብዙ ጊዜ ለማየት እስኪያስጠላኝ ድረስ በተለያዩ ገጾች ላይ እራሱን ሲያስተዋውቅ ገርሞኝ ነበር፡፡
    ነገሩ ያላማረኝ ከመነሻው ነው፡፡ “ገጼን ካላነበባችሁ” የሚል ኦርቶዶክሳዊ “ዲያቆን” ስለ መኖሩ እየገረመኝ፡፡
    በህይወቴ ከምጠየፋቸው ሰዎች ውስጥ አንደኛዎቹ “ተሃድሶ “ተብዬዎቹ ያልታደሱ ገለባዎች ናቸው፡፡ በየድህረ ገጾቹ የሚዘሩትን እርክንዳድ ላለመልቀም እነሱን ከነምንፍቅናቸው ለመራቅ የዘወትር ጸሎቴ ነው፡፡
    በቅርቡ ይህን “የዲ/ን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ” የሚለውን ገጽ ክፉ ደጉን ለመለየት ከፈትኩና አንዱን ርዕስና ዝርዝሩን አነበብኩ፡፡
    ያው እንደ ጠረጠርኩት ነው፡፡
    ___በዓለ ጰራቅሊጦስ የተጻፈ ነው ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ግን ለምን ተረሳ ይላል ርእሱ፡፡
    +++ማነው መንፈስ ቅዱስን የረሳ; ቤተክርስቲያን ወይስ የእርሱ ጠማማ ልብ;
    የአገልግሎቷ መሰረት የስርዓቷ ሁሉ መሪ የጉባኤዎቿ መሪ ማን ሆነና;
    ቤተክርስቲያን ይህን ጥያቄ ልትጠየቅ ይገባል;
    ___በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በቅዱሳን መታሰቢያነት የተነሰሩትን አብያተ ክርስቲያናት “ብዙ ሺዎች…” ካለ በኋላ
    ከእነዚህ እልፍ ሺህ “አብያተ ክርስቲያናት” መካከል የመንፈስ ቅዱስን “መታሰቢያ ህንጻ” ማግኘት በምድረ በዳ መልካም ጥላ የመፈለግ ያህል እጅግ ይከብዳል፡፡-
    +++እንግዲህ “ምድረ በዳ” ተብለው የተጠቀሱት በሌሎች መታሰቢያነት የተሰሩ አብያተክርስቲያን ናቸው፡፡ እነዚያ “የሚያቃጥሉ ምድረ በዳዎች” ስለሆኑ (አብያተክርስቲያንነታቸውእንኳ በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ መግባቱ ልብ ይሏል) መልካም ጥላነት የማይገኝባቸው ይላል፡፡
    ___”ቤተ-ክርስቲያን የምትባለው … በመንፈስ ቅዱስ ስትጠመቅ ብቻ ነው”፡፡
    +++ጌታ እንኳ ለማታ ተማሪው ለኒቆዲሞስ ሲያስተምር ከወሃና ከመንፈስ ቅዱስ መወለድ አስፈላጊ መሆኑ ሲናገር አንተ ደግሞ የወሃ ጥምቀትን ዋጋ ለምን ቆርጠህ ጣልከው? ቢቻ ብሎ ያስተማረን ሀዋርያስ አለ? ፡፡ ዘመዶችህ ተኩላዎቹ ካልነገሩህ በስተቀር የክርስቲናን አስተምህሮ “ቢቻ” በማለት ማን ነገረህ?
    ___”የናዝሬቱ ኢየሱስ ሠላሣ አመት ወላጆቹንና ዘመዶቹን፤ ሦስት ዓመቱን ደግሞ ቅዱስ አባቱንና እኛን በገዛ ዘመኑ አገልግሎ በገዛ ደሙም ዋጅቶ፤ የመለኮቱ ተካፋይ እንሆን ዘንድ ቃሉን አሰምቶ ጮኾ ጠራን” ትላለህ፡፡
    +++ክብር ይግባውና ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር የመጣው አባቱ አብን ሊያገለግል አይደለም፡፡ በቅድምና እኩል የሆኑ፣ ስልጣናቸው ትክክል የሆነ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንዱ አገልጋይ አንዱ ተገልጋይ አይባሉም፡፡ እግዚብሔር ወልድ በራሱ ፈቃድ በአባቱና በህይወቱ በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ክብሩን አዋርዶ የደካማውን ሰው ስጋ በለበሰ ጊዜ በትህትና ትዕቢተኛውን ሰው አገልግሎ ህይወት ሰጥቶትና አብነቱ ሆኖት ወደ አባቱ ከማረጉ ባሻገር የተሰወረብን የስላሴን ምስጢር በገሃድ ገልጦልናል፡፡ የአብን አባትነት፣ የእርሱንም የባህርይ ልጅነት የመንፈስ ቅዱስንም ሰራጺነት አስረዳን እንጂ አገለግላለሁ አላለም፡፡
    ___”ደግሜ እላለሁ፥ በጣም ልብ የሚነካውና በሐዘን የሚሰብረው ነገር ደግሞ ለቅዱሳን ÷ ጻድቃን ÷ ሰማዕታት … አዕላፍ "መታሰቢያ" ተሰርቶ ለአንዱ ጌታ ለመንፈስ ቅዱስ በ"መታሰቢያነት" እንኳ አንድ "ቤተ-ክርስቲያን" በስሙ ተሰይሞ ለማግኘት ጭንቅ መሆኑ ምን እየሆን ነው? ያስብላል ÷ ምነው "ትንሹን" ስናከብር ትልቁ አኗሪው ተዘነጋን? ያሰኛል ÷ ምነው “ከዚያ ሁሉ” መዝሙር አንድ መዝሙር ስለመንፈስ ቅዱስ ጠፋ?” ---ትላለህ
    የገረመኝ ነገር እጅጉን የከነከነህ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በቅዱሳን ስም መታነጻቸው መሆኑ ቢቻ አይደለም፡፡ ምን ያህል ያለማወቅ ባዶነት ውስጥህን እየፈጀ መሆኑን አለማወቅህም ጭምር እንጂ፡፡ ለመረጃ ያህል ለመንፈስ ቅዱስ ያልዘመረ የቤተክርስቲያን ዲያቆን የለም፡፡ ከሰንበት ተማሪ እስከ ፓትሪያርኩ ዘምረዋል፡፡ ያልዘመርክ ሰው በመሆንህ በራስህ ላይ ልታፍር ይገባሃል፡፡ አንድም ቤተክርስቲያን አለመኖሩንም ቁጥብነት በሌለው አንደበትህ ደምድመወሃል፡፡ እኔ እንኳ በምገኝበት ግቢ አቅራቢያ ባለው ቤ/ክ ስላለመኖሩ ጠይቀሃልን? ከጥቁር አንበሳ በስተቀኝ የሚገኘው ጽርሃ ጽዮን ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ እንኳ የታነጸውና በየዓመቱም በበዓለ ጰራቅሊጦስ ታቦተ ህጉ ወጥቶ የሚከብረው ለዚሁ ነው፡፡ ይህንን በዓል ካከበርን ገና አንድ ሳምንት እንኳ ሳይሆነን የለም ለማለት የሚቸኩለውን አንደበትህን ታገስ በለው፡፡
    ___ ይህ ሰው ቤተክርስቲያን መንፈስ ቅዱስን” በመርሳቷ” “የለችም” ካለና እራሱን ጀሌዎቹን “ከጻድቃንና ሰማእታት ልክ” አሰልፎ “አለን” ካለ በኋላ ትንሽም ፍርሃት በሌለው ድፍረት እንዲህ ይላል፡፡” ቤተ-ክርስቲያን ሆይ ከወዴት እንደወደቅሽ አስቢ! … የቆምሽበትንም መርምሪ!!! ከሙሽራሽ ከኢየሱስ ስለመጋባትሽ ማጫ ሆኖ የተሰጠሽን መንፈስ ቅዱስን ገለል ብለሽ ካለፍሽበት ጎዳና ዳግም በንስሐ ፈልጊው፡፡”
    የወደቁትን የምትጠራ ቤ/ክ እንዲህ ተባለች!! የገሃነም ደጆች የማይችሏት እናት በመናፍቅ እንክዳድ “ወድቀሻል ነይ እኔ ላድስሽና ላንሳሽ” ተባለች; ፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በጉዞዋ ሁሉ ተለይቷት የሚያውቅ ይመስል “እኔ ጋ አለና ነይና ፈልጊ” ትባል?
    ድሮም ከባዶነት ምን ሊገኝ? ከክህደት ምን ሃይማኖት ሊኖር? ከትዕቢት ምላስ ምን ትህትና ሊገኝ?፡፡
    ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፡- ይህንን ጽሁፍ ስጽፍ ለዚህና መሰሎቹ የእናት ጡት ነካሾች ማስታወቂያ ለመሆን አይደለም፡፡ ጥቂት የማይባሉት የዋህ ክርስቲያኖች ባለማወቅ የእነሱን ድህረ ገጽ ላይክ በማደርግና የምንፍቅና እንክርዳድ ጽሁፎቻቸውን እያነበቡ ስለሆነ በስመ ኦርቶዶክስ ስለተጻፈ ቢቻ አሜን ከማለት እንዲመረምሩ ለማሳሳብ ነው፡፡
    እግዚእብሔር አጽራረ-ቤተክርስቲያንን ያስታግስልን፡፡
    ወስብሃት ለእግዚአብሔር

    ReplyDelete
    Replies
    1. Anonymous August 4, 2014 at 9:33 PM,
      So, Why is that the Church you mentioned had a name change from Tserha Ariam MENFES KIDUS to golla Michael?
      I need an honest answer, Please?

      Delete
  3. በአጭሩ እኔ ልመልስልክ ወንድሜ ከታሪኩ የሰማሁትን መንፈስ ቅዱስን ለማሰብ የተሰራው ቤተክርስቲያን ሆድ አምላኪዎች በሆኑ አንዳንድ ክርስቲያን ነኝ ባዮች ሙዳይ ምፅዋት አልሞላ ሲላቸው ህዝቡን ከማስተማር ይልቅ የሚያውቀውን የህዝቡን ጆሮ ጣቢያ ከመንፈስ ቅዱስ ወደ ሚካኤል ቀየሩት በአጭር ጊዜም ሙዳይ ምፅዋቱም ሞላ ከዚያም በሚያሳፍር ሁኔታ ስሙን ጎላ ሚካኤል ብለው ጠሩት ይህም ማለት ከጰራቅሊጦስ ይልቅ ሚካኤል ታወቀ ማለት ነው ።ለሁላችንም እግዚአብሔር ይቅር ይበለን።ከመተቸት በፊት ቅዱስ መፅሐፍ ምን ይላል ብለን እንደቃሉ ልንመረምር ይገባል።ክርስቲያን ዐይኑ በጌታ ቃል የተወለወለ ንፁህ ነው።
    ወንድሜ ዲ/ን አቤኔዘር ተክሉ እና ዲ/ን አሸናፊ መኮንን እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛላችሁ።እግዚአብሔር በእናንተ ላይ አላማ አለው የእርሱን ድምፅ ብቻ በመስማት አላማውንና ራዕዩን አሳኩ በብዙ ተባረኩ የሚፅፈው እጃቹ የሚያስብ አእምሮአችሁ ይባረክ አይንጠፍ።ስለእናንተ ደግሞ አምላኬን እግዚአብሔርን አመሰግነዋለው ክብሩ ሁሉ ተጠቅልሎ ለእርሱ ይሁን አሜን።

    ReplyDelete
  4. በአጭሩ እኔ ልመልስልክ ወንድሜ ከታሪኩ የሰማሁትን መንፈስ ቅዱስን ለማሰብ የተሰራው ቤተክርስቲያን ሆድ አምላኪዎች በሆኑ አንዳንድ ክርስቲያን ነኝ ባዮች ሙዳይ ምፅዋት አልሞላ ሲላቸው ህዝቡን ከማስተማር ይልቅ የሚያውቀውን የህዝቡን ጆሮ ጣቢያ ከመንፈስ ቅዱስ ወደ ሚካኤል ቀየሩት በአጭር ጊዜም ሙዳይ ምፅዋቱም ሞላ ከዚያም በሚያሳፍር ሁኔታ ስሙን ጎላ ሚካኤል ብለው ጠሩት ይህም ማለት ከጰራቅሊጦስ ይልቅ ሚካኤል ታወቀ ማለት ነው ።ለሁላችንም እግዚአብሔር ይቅር ይበለን።ከመተቸት በፊት ቅዱስ መፅሐፍ ምን ይላል ብለን እንደቃሉ ልንመረምር ይገባል።ክርስቲያን ዐይኑ በጌታ ቃል የተወለወለ ንፁህ ነው።
    ወንድሜ ዲ/ን አቤኔዘር ተክሉ እና ዲ/ን አሸናፊ መኮንን እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛላችሁ።እግዚአብሔር በእናንተ ላይ አላማ አለው የእርሱን ድምፅ ብቻ በመስማት አላማውንና ራዕዩን አሳኩ በብዙ ተባረኩ የሚፅፈው እጃቹ የሚያስብ አእምሮአችሁ ይባረክ አይንጠፍ።ስለእናንተ ደግሞ አምላኬን እግዚአብሔርን አመሰግነዋለው ክብሩ ሁሉ ተጠቅልሎ ለእርሱ ይሁን አሜን።

    ReplyDelete
  5. በአጭሩ እኔ ልመልስልክ ወንድሜ ከታሪኩ የሰማሁትን መንፈስ ቅዱስን ለማሰብ የተሰራው ቤተክርስቲያን ሆድ አምላኪዎች በሆኑ አንዳንድ ክርስቲያን ነኝ ባዮች ሙዳይ ምፅዋት አልሞላ ሲላቸው ህዝቡን ከማስተማር ይልቅ የሚያውቀውን የህዝቡን ጆሮ ጣቢያ ከመንፈስ ቅዱስ ወደ ሚካኤል ቀየሩት በአጭር ጊዜም ሙዳይ ምፅዋቱም ሞላ ከዚያም በሚያሳፍር ሁኔታ ስሙን ጎላ ሚካኤል ብለው ጠሩት ይህም ማለት ከጰራቅሊጦስ ይልቅ ሚካኤል ታወቀ ማለት ነው ።ለሁላችንም እግዚአብሔር ይቅር ይበለን።ከመተቸት በፊት ቅዱስ መፅሐፍ ምን ይላል ብለን እንደቃሉ ልንመረምር ይገባል።ክርስቲያን ዐይኑ በጌታ ቃል የተወለወለ ንፁህ ነው። ወንድሜ ዲ/ን አቤኔዘር ተክሉ እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልህ። እግዚአብሔር በአንተ ላይ አላማ አለው የእርሱን ድምፅ ብቻ በመስማት አላማውንና ራዕዩን አሳካ በብዙ ተባረክ የሚፅፈው እጃቹ የሚያስብ አእምሮህ ይባረክ አይንጠፍ።ስለ አንተ ደግሞ አምላኬን እግዚአብሔርን አመሰግነዋለው ክብሩ ሁሉ ተጠቅልሎ ለእርሱ ይሁን አሜን።

    ReplyDelete