Please read in PDF :- zefagn lebetekiristiyan mnua new?
ከሰሞኑ አንድ ዘፋኝ “ከወንጌላውያን ህብረት አብያተ ክርስቲያናት አባል ነህ” ያሉትን ድህረ ገፆችና መገናኛ ብዙሀን እንደሚከሰና እርሱ “ኦርቶዶክሳዊ” እንደሆነ ማረጋገጫ እንዲሰጡት፤ይቅርታ እንዲጠይቁትም ሊያደርግ እንዳሰበ ከመገናኛ ብዙሀን ሰምተናል፡፡“ተደንቀናልም”፡፡ ለመሆኑ “ዘፋኝ” ለኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ምኗ ነው? አማት ወይስ ምራት? አጎት ወይስ አክስት? “የወንጌላውያን ህብረት አብያተ ክርስቲያናት” ዓለም ያከበረቻቸው ሰዎች ሲመለሱላቸው “የሚደሰቱት”፤ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ዓለም ያከበረቻቸውን እርሷም አብራ በመመቻመች የሚዘልቁት እስከመቼ ነው? (ምነው የትም በጭፈራ እያሳለፉ የዚህ እምነት ተከታይ ነበርኩ ዛሬ ጌታ “ተገለጠልኝ” ማለት አልበዛም እንዴ?)
ከሰሞኑ አንድ ዘፋኝ “ከወንጌላውያን ህብረት አብያተ ክርስቲያናት አባል ነህ” ያሉትን ድህረ ገፆችና መገናኛ ብዙሀን እንደሚከሰና እርሱ “ኦርቶዶክሳዊ” እንደሆነ ማረጋገጫ እንዲሰጡት፤ይቅርታ እንዲጠይቁትም ሊያደርግ እንዳሰበ ከመገናኛ ብዙሀን ሰምተናል፡፡“ተደንቀናልም”፡፡ ለመሆኑ “ዘፋኝ” ለኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ምኗ ነው? አማት ወይስ ምራት? አጎት ወይስ አክስት? “የወንጌላውያን ህብረት አብያተ ክርስቲያናት” ዓለም ያከበረቻቸው ሰዎች ሲመለሱላቸው “የሚደሰቱት”፤ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ዓለም ያከበረቻቸውን እርሷም አብራ በመመቻመች የሚዘልቁት እስከመቼ ነው? (ምነው የትም በጭፈራ እያሳለፉ የዚህ እምነት ተከታይ ነበርኩ ዛሬ ጌታ “ተገለጠልኝ” ማለት አልበዛም እንዴ?)
አንደራደርም ፤“ዘፋኝነት” (አዲሱ “የቤተ-ክርስቲያናችን መጽሐፍ ቅዱስ”
ባይጠቅሰውም) የሥጋ ሥራ ነው፡፡(ገላ.5፥21) የሥጋን ሥራ የሚያደርግ ሁሉ ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርስም፡፡
(1ቆሮ. 6፥11) በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግስትም ርስት የለውም፡፡(ኤፌ.5፥5)፡፡እርግጥ ነው በቀደመው ዘመን ሁላችን የኃጢአት
ባርያዎች፤ የሞትም አገልጋዮች ነበርን፡፡ ነገር ግን ዛሬ ከዚያ ከምናፍርበትና ከምንፀፀትበት ህይወታችን ያተረፍነው ምንም ፍሬ ስለሌለን፤
መጨረሻውም ሞት እንደሆነም ስላመንን፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆነን አሁን ከኩነኔ ነፃ ነን፡፡(ሮሜ 6፥20፤8፥1) ባዕለጠጋው እግዚአብሔር
‹‹ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩም የተነሣ በበደላችን
ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ህይወትን ሰጠን፤ በፀጋውም አዳነን››፡፡(ኤፌ.2፥4-6)
አዎን! በቀደመ ዘመናችን ለሁለት ጌቶች የምንገዛ ብንሆንም (ማቴ.8፥24)ዛሬ
ግን ላንዱና ለሚበልጠው ጌታ በውድና በፍቅር ስለተገዛን ያ ዓለም፤አያምረንም፡፡
(ሮሜ.8፥23) ስለዚህ ያንን ዓለም በሚበልጥ ዓለም ተክተን ንቀን ጠልተነዋል፡፡ “ሰማዕታት የዚህችን ዓለም ጣዕም በእውነት የናቁት፤
ደማቸውንም ስለእግዚአብሔር መንግስት በመታገስ ያፈሰሱት” የዚህን ዓለም ጣዕም በእውነት ስላዩትን ስለናቁት ነውርም እንደሆነ ስለተረዱት ነው፡፡
ሁላችንም
ከልብ የምንወደው አንድ እውነት አለ፡፡አለም “ያገነነቻቸው ብቻ ሳይሆኑ” ሁሉም ኃጢአተኞች ኃጢያታቸውን ጠልተው በንስሐ ቢመለሱ፤
እንኳን እኛ የሰማይ መላዕክትም ደስተኞች ናቸው፡፡ (ሉቃ.15፥10) አንድ ዘፋኝም ሆነ የትኛውም በተገለጠም ሆነ በድብቅ ነውርና
ኃጢአት የሚመላለስ ማናቸውም ሰው “መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ”(1ቆሮ.5፥5) ንስሐ ገብቶ ቢመለስ የሁላችንም መሻት
ነው፡፡ በተለይ የጌታን መንግስት በቶሎና በትጋት ትመጣ ዘንድ ለምንጠባበቅና ለምንናፍቅ “ትሩፋን”፡፡
የእስራኤልን ልጆች ያረከሰው አንዱ ኃጢአት “ሊበሉ ተቀምጠው ሊዘፍኑ
መነሳታቸው” ነበር፡፡ (ዘጸ.32፥6) ጌታን ያጠመቀው ቅዱሱ ነቢይ ዮሐንስ አንገቱ እንደዋዛ በሰይፍ የተመተረው ዘፈን ባመጣው ጣጣ
ነው፡፡(ማቴ.14፥6) ዛሬም የብዙዎች ትዳር የሚፈርሰው፣የብዙ ሚሊየን ወጣቶች ህይወት የሚረክሰውና በአጭር የሚቀጨው ዘፋኞች በሚያቀነቅኑት
“ሰይጣናዊ ዜማ” ነው፡፡የእገሌ ዘፈን “ያስታርቃልና” ተብሎ በቤተ ክርስቲያን አውድ ለመዝፈን የቃጣንና የነሸጠን ጊዜ ላለመኖሩ
ምን ዋስትና አለን? እኒህ ትውልዱን ለዝሙትና ለርኩሰት የሚማግዱ ዘፋኞች ናቸው እንግዲህ “ኦርቶዶክስ እንጂ እኛ የወንጌላውያና
ህብረት አማኞች አይደለንም” እያሉ “በአካኪ ዘራፍ ፉከራ” በየአደባባዩ ጉምቱ ወሬ የሚያወሩት፡፡
ጥቂት ያይደሉ ዘፋኞች ከዓመታት በፊት “መዝሙር ዘምረው” ኦርቶክሳዊ መሆናቸውን
ነገሩን፡፡ከዚያ አንዳቸውንም መመለሳቸውን (በንስሐና እንደኃጢአታቸው በግልጥ ኑዛዜ) ሳንሰማ ወዲያው ዘፈን ማውጣታቸውን አብረን
ሰማን፡፡ (የሎጥ ሚስት ወደኋላ ስትመለስ የጨው ሀውልት እንጂ ሥጋ መልበሷን አልሰማንም፤አላነበብንምም ነበር!!!) ዘፋኝነት የአደባባይ፤
ብዙዎችንንም የሚያሰናክል ኃጢአት ነው፡፡ የአደባባይ ኃጢአት የሠራ ተነሳሒ ኑዛዜውም በአደባባይ ሊሆን ይገባዋል፡፡ዘኬዎስና ከነናዊቷ
ሴት ኃጢአታቸውን በአደባባይ ነበር የተናዘዙትና ያመኑት፡፡(ሉቃ.19፥8፤ማቴ.15፥27) ዘፋኞቻችንና ፖለቲከኞቻችን ግን በአደባባይ
የሠሩትን ነውር በግልጥ ኑዛዜ “ሳያወራርዱ” በጓዲያ ገብተው ጨርሰው በአደባባይ ቀና ቀና እያየን ኖረናል፡፡
እንግዲህ ከሰሞኑ የሰማነው እዚያው የዘፈኑ መንደር ላይ ሆኖ ስለ“ኦርቶዶክሳዊነቱ”
የሚሟገት አንድ ዘፋኝን ነው፡፡ምናልባት ብዙ ባዕለሥልጣናትና የዚህ
አለም ሰዎች የቀብር ሥፍራቸውን ለማስከበር እንደሚያደርጉት ከሆነ “ይቻል ይሆናል”(አማኙም ከሀዲውም በዚህችው ቤተ ክርስቲያን መንግስተ
ሰማያት ወርሳችኋል እየተባለ በደመቀ ሥርዓትና በውሸት ምስክር ሲቀበር ነፍሳችን ተክዞ እያየንም አይደል?) ግና ዘፋኝነትን የክርስትና
ካባ ማልበስ የነውርና የድፍረት ኃጢአት ነው፡፡
በአጭር ቃል የጌታን ቃል ደግሜ እላለሁ “ዘፋኞችና የሥጋን ሥራ የሚያደርጉ
ሁሉ ደመወዛቸው ሞት እንጂ ዘላለማቸው የእግዚአብሔር መንግስት አይደለምና” የበደሉትን ህዝብ፤ በየጭፈራ ቤቱና በየመሸታ ቤቱ ያረከሱትንና
ያፈረሱትን ወጣትና ትዳር በግልጥ ኑዛዜ ይቅርታ ጠይቁና ተመለሱ እንጂ ዘፋኝነትን ኦርቶዶክሳዊ ካባ አታልብሱት፡፡ እውነተኛ ኦርቶክሳዊነት
ዓላማዊነትን መካድ እንጂ ከአለማዊነት ጋር በአንድ መተባበር አይደለምና … ዘፋኞች ሆይ! የግልጥ ኃጢአታችሁን፤ በሁለት ዓለምና
ጌታ ማንከስን ትታችሁ መመለስ ይሁንላችሁ፡፡
አዎ! “ዘፋኝና ዘፋኝነት ለኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ላንቺም” ምንሽም
አይደለምና ለቀብር እንጂ ለህይወት የማይመጡ “ልጆችሽን” ቤተ ክርስቲያን ሆይ! ተነሺና ጎብኚያቸው፤ ባዝነው የሚቅበዘበዙትንም ወደበረቱና
መንጋው ሰብስቢያቸው፡፡
ጌታ በትንሳኤው ብርሐን የዘፋኝነትን
መንፈስ ከምድሪቱ ያርቅልን፡፡አሜን፡፡
እግዚአብሔር አምላክ አገልግሎትህን ይባርክ የእኔ ወንድም
ReplyDeletehulachenem ke endenezi ayinet tekulawoch lentenekek yigebal Diacon nen eyalu sewun wede sehtet wediyabilos menfes kemiwesdu acheberbariwoch andu Abenezer bemil yetekefete ye Protestant blog new
ReplyDeleteare you out of your mind? what is wrong with you? what is wrong with this message? can you atleast try to read the portion of it to get to the point? it is black and white thing. there is no hidding message in it. I really do pray for you. may my God give you a wisdom
Deleteበየጠጅ ቤቱ እየሄድክ ስለምታደገድግ ዘፋኝነት ኦርቶዶክሳዊነት ይመስልሃል። ለመሆኑ አንተ ክርስቲያን ነህ ኦርቶዶክሳዊቷን ቤተክርስቲያን ታውቃታለህ? የት መቼ በምን ሁኔታ ዝፈን ብላህ ነው? ዘፋኝ መወቀሱ ተኩላነት ነው የሚያሰኝህ? አጭበርባሪው እና አሳቹ አንተ ነህ? የዘፈን ዛር የሰፈረብክ። እኛ ግን ያነበብነው ጥርት ያለ የቤተክርሰቲያናችንን መልዕክት ነው። አሁንም ቢሆን ዘፋኝ ለኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ምኗም አይደል።
Deletebased on this article of course this guy is not an orthodox!!!
DeleteAmen! Hiwotin mekeyer yemichil melikt new kale hiwot yasemalin.
ReplyDeleteGod bless you my brother. I was waiting for someone to say something about this. I believe that be a chritian is got to be with being a child of God and live full life of Jesus christ's life and that means whatever you do, do it for the glory to God. it is not about siding with one group or another.
ReplyDeleteTebarek
ReplyDeleteምኗም አይደል
ReplyDeleteየምግባር ጉለትና የሃይማኖት ችግር ፋፅሞ የተለያየ ነው:: የምግባር ጉድለቱ ከተነሳ ሁላችንስ በግልፅም ይሁን በሰውር ሃጥያት የተያዝን አይደለንምን?? ታድያ በስውርም ይሁን በግልፅ ሃጥያት ተይዘን ከዛሬ ነገ ለውጥ እናመጣ ይሆናል ብለን ቤተክርስቲያን የምንመላለስ ሃይማኖታችንን ጠንቅቀን ይዘን ለመቆም የምንውተረተር ሁሉ ስለምግባር ጉለታችን ሃይማኖታችንን እንተው ይሆንን??
ReplyDelete"ዘፋኝ" ለኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ምኗ ነው? ante mane neh???fitsum krstiyanawi tihitina yegodelewu tsihuf!!!!
ReplyDeleteEnter your comment... Enter your comment...እውነቱ እሱ ነው ተባረክ። ቢሆንም እነርሱን መግባባትና ለቸሩ እግዚ አብሔር መማረክ ይሻላል ነገ ማን ያውቃል ይዘምር ይሆናል ስለዚ በተገኘው አጋጣሜ ማስተማር ሁሉም የወንድሙን ሸክም ይሸከም ፡፡ማንም ሀጥያት የለብኝም የሚል ቢኖር እርሱን ውሸታም ያደርጋልና የአንዱ ስለተገለጠ የሌላው ስለተሸፈነ፡፡ ጌታ ስለ አይነስውር ሆኖ የተፈጠረው ሲጠየቅ የእግዚ አብሔር ክብር እንዲገለጥ ይላል።ጌታ ይመስገን
ReplyDelete.......እረ ነዉር ነዉ፣ መጥፎ ቃላት አንወራወር፣ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያን ስነምግባር ይኑረን እባካችሁ፡፡ ከላይ የተነገረን የእግዚአብሄርን ቅዱስ ቃል ነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የምንነጋገርበት ቅዱስ ቃል፣ የማንኛችንም የአኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች የእምነታችን መሰረት መጽሐፍ ቅዱስ ነዉ፣ ስለዚህ ከላይ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ያጨቃጨቀን ቃል( ዘፋኝነት)የሚገኘዉ በግዚአብሄር ቅዱስ ቃል/መጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ነዉ፡፡
ReplyDeleteገላቲያ 5፡ 21.." መለያየት፣ መናፍቅነት፣ ምቀኝነት፣ መግደል፣ ስካር፣ $ዘፋኝነት$፣ ይህንም የሚመስል ነዉ፣ አስቀድሜም እንዳልሁ፣ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ « የእግዚአብሄርን መንግሥት አይወርሱም»" ስለዚህ ዘፋኝ ከሆንን አንወርስም ማለት ነዉ፡፡ ይሄንን የእግዚአብሄርን ቃል ካላከበርን እምነታችንን/ ሃይማኖታችንን ጥያቄ ዉስጥ ያስገባን ይሆን?፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ደግሞ የእግዚአብሄር ቃል እንዲህ ይላል......ዘኅልቁ 15:31 " የእግዚአብሄርን ቃል ስለናቀ ፣ ትእዛዙንም ስለ ሰበረ ፣ ያ ሰዉ ፈጽሞ ፣ ኃጢአቱም በራሱ ላይ ነዉ"፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሄርን ቅዱስ ቃል እንከተል፡፡
እውነት ነው ይህንን የምናስተውልበትን ማስተዋል ጌታ ያድለን በርቱ ፀጋውን ያብዛላችሁ ተባረኩ
ReplyDelete