Monday 14 April 2014

ሆሼዕና ኢየሱስ


Please read in PDF ; hoshena Eyesus
ምድር ነዳ ከስላ  - ጠቋቁራ ጠልሽታ፤
ዙርያዋን በኃጢአት - ነበልባል ተከባ፤
ትዳር መቅኖ አ’ቶ፤
ሴሰኝነት ክንፉን አርብቦ ዘርግቶ፤
ትውልድ በአመጻ መንፈስ ነፍሱ ጎብጦ፤
              እያየኸው አይሙት የሞትክለት ትውልድ
              ሆሼዕና ኢየሱስ ልቡን መልስለት፡፡
ቃየላዊ ብልጠት - ባ’ቤል ደም መጨቅየት፤
በለዓማዊ ብልሐት - የመረረ ርኩሰት፤
የከንፈር አምልኮ - የሽንገላ ፍቅር፤
ድኃውን ከፍትህ - በገንዘብ መፈንገል፤
         .
         .
         .
የጸሎቱ ቤቱ አውድ - እንደንግድ ተቆጥሮ፤
አገልግሎት “Business” - ወንጌል ችርቻሮ፤
ሲሸመት ሲለወጥ - መዝሙር ተመንዝሮ፤
በመልክና በሀብት - ቃልህ ተሸቃቅጦ፤
       እያየህ እባክህ - ዝም አትበል ጌታ፤
       ሆሼዕና ኢየሱስ - ቤትህን አንተ አጥራ፡፡
አሁኑኑ አድን - አሁኑኑ አቅና፤
ካንተ በቀር ሌላ - አዳኝ የለምና፤
አሁን አድን ‘ባክህ - መድኃኒት ኢየሱስ፤
መዳንህ በዝቶልን - ስምህን እንድንቀድስ፡፡

1 comment:

  1. IT WILL BE WISE TO STOP POSTING ISIS VIDEOS ANYMORE... THEY WANT US TO DO JUST THAT... SPREAD THEIR FEAR N EVIL!!! LETS STOP POSTING IT ALTOGETHER... THEY WONT STOP KILLING UNTIL THEY R DESTROYED............ AND THEY WILL BE DESTROYED

    ReplyDelete