Tuesday 18 March 2014

ግብረ ሰዶማዊነት - የዘመናችን መጻጉዕ (የመጨረሻ ክፍል)


Please read in PDF

    አንድ የምወደው ባልንጀራ ወዳጅ ዳኛ አለኝ፡፡ለብርቱ ጉዳይ እንደሚፈልገኝ በስልክ አቻኩሎ ጠራኝ፡፡አላመነታሁም … ከተሰየመው ችሎት ገብቼ አንድ ጉዳይ እንድሰማ ጋበዘኝ፡፡የአርባ ሁለት አመት ጎልማሳ የስድስት አመት ወንድ ህጻን በፈጸመበት ግብረ ሰዶማዊነት መቀመጥ እንደማይችል ብሎም በፊንጢጣ መቀደድ እንደሚሰቃይ ከውሳኔው ስሰማ ረዥም ዝምታ ከችሎቱ በኋላ ወደ ውስጤ ተሰማኝ፡፡(አቤቱ ይህን ሁሉ ለምን ታሳየኛለህ? ... ጥፋትና ርኩሰት መዋረድስ በመካከላችን ስለምን ሆነ?  … አቤቱ ምድሪቱ ለክፉዎች ተሰጥታለችና ጨርሶ ሳይጨልም ድረስልን!!!...የሚያቃጥል እንባ … መንፈስን የሚለበልብ የቁጣ ነበልባል … )
     መንግስት “ከብዙ ነገር አንጻር” ግብረ ሰዶማዊነትን በግልጥ ባይቃወምም በዝምታ ሊደግፍ እንደሚችል ታዝበናል፡፡ ቢያንስ እንደአሸን እየፈሉ የመጡትን እኒህን የሰዶም ሰዎች ሊያስተምር በሚችል መልኩ እንደወንጀል ህጉ ቀጥቶ አለማሳየትና አቀንቃኞቹን አለመግራት በግልጥ ከመደገፍ አይተናነስም፡፡ ከሁሉ በላይ ግን ቤተ ክርስቲያን ለዚህ ነገር ትኩረት ሰጥታ አለመስራቷ ይበልጥ እጅግ የሚያደማ ነገር ነው፡፡ በተለይ በገዳም ባሉ ጥቂት በማይባሉ መነኮሳትና መነኮሳይያት ዘንድ ከሚሰሙ ነውሮች መካከል አንዱ ግብረ ሰዶማዊነት ነው፡፡ምናልባት እንዲህ ደፍሬ የምናገረው የቤተ ክርስቲያንን ነውር መግለጥ የሚያስደስት ሆኖ አይደለም፡፡ነገር ግን ማንቀላፋታችን አለልክ ስለበዛ ፣ይህ ነውር ሩቅ እንጂ እዚህ አፍንጫችን ሥር ያለ ስላልመሰለንና ጣታችንን በሌሎች እየቀሰርን የንስሐ ዘመናችንን በክስና በሽንገላ እየጨረስነው እንደሆነ ስለታየኝ ነው፡፡የማንክደው እውነት ግብረ ሰዶማዊነት በመካከላችን አለ፡፡መኖር ብቻ ሳይሆን ቁጥሩ ቢያንስም እንደሐገሪቱ ህግ የተቀጡና በማረሚያ ቤቶች ያሉ ሰዎችም አሉ፡፡

     በተለይ ዩንቨርሲቲዎቻችን፣ የሁለተኛ  ደረጃ ትምህርት ቤቶቻችን፣ ማረሚያ ቤቶቻችን ፣የቴኳንዶና ካራቴ ማሠልጠኞቻችን፣ የባዝና የማሳጅ ቤቶቻችን ፣ጥቂት ያይደሉ ሰንበት ትምህርት ቤቶቻችን … በአብዛኛው የእነዚህ ሰዎች ትልቅ የትኩረት ሥፍራ ናቸው፡፡ትውልዱ ከትላንት ይልቅ ዛሬ የማያልቁ ብዙ የኃጢአት ቀጠሮዎች በገና ሊፈጽም የተቃጠረ ነው፡፡ “ከሴት እንተኛ አዳሪዎች” ይልቅ በዚህ ነውር ላይ ለተሰማሩ ሰዎች የሚከፈለው ክፍያ መብዛቱ ደግሞ ብዙ ተከታይ ስላለማፍራቱ  ለመከራከር አያስደፍርም፡፡(በእንቅርት ላይ … )
   የምዕራባውያን የዕድገታቸው መሠረት ወንጌል እንደሆነ ይነገራል፡፡በእርግጥም ወንጌል ለሥጋም ለመንፈስም ጤናና ደህንነት መሠረት ነው፡፡ከወንጌል የተወለደ ማህበረሰብ ጠንካራና ኃጢአትን በእውነት ከልቡ መጥላት የሚችል ሥነ ልቦና ያለው ማህበረሰብ ነው፡፡ ወንጌል ለእውነት እስከሞት እንደንጨክን የምታደርገንን ያህል ከኃጢአት ጋር ያለንንም ግንኙነት በቃሉ ጉልበት እንድንቆራርጥ የምታስጨክነን ህያው ስለት ናት፡፡ የሚያድነውን ወንጌል የሰማ ማህበረሰብ ከኃጢአት በተለይም ከዝሙትና ከግብረ ሰዶማዊነት ፊት ይሸሻል እንጂ ቆሞ አይደራደርም፡፡ (ዘፍ.19÷14፤39÷12፤1ቆሮ.6÷18)
    ግብረ ሰዶማዊነት ተፈጥሮን የሚቃወም አፀያፊ ድርጊት ነው፡፡በአንድ ወቅት ተፈጥሮን የሚቃወም ድርጊት መሆኑን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ “እንኳን በእግዚአብሔር አርአያ የተፈጠረ የሰው ልጅ ዕፅዋት እንኳ ወንዴና ሴቴ አላቸው፡፡” ማለታቸው አይዘነጋም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ተፈጥሮንና የሰውን ዘር በቃሉ ከለላነትና ቅጥርነት የመጠበቅ ኃላፊነት አለባት፡፡ምድርና በውስጧ ያሉት ተፈጥሮዎች ሁሉ መባከን የለባቸውም፡፡ደኖቻችንን በሰደድ እሳትና በጦርነት ማባከናችን አሁን ላለው የሙቀት መጠን መጨመርና የአየር መበከል ብሎም ለበረሃማነት መስፋፋት የጎላ ድርሻ ከመውሰዱም በላይ ዛሬ ላይ የነበረውን ለመመለስ ከባድ ዋጋ እያስከፈለን ነው፡፡
   ግብረ ሰዶማዊነት ተፈጥሮን በካይ ድርጊት ነው፡፡እግዚአብሔር ለበሽታና ለደዌ ተላልፈን እንድንሰጥ አልፈጠረንም፡፡ግብረ ሰዶማውያን ከላይ የጠቀስነው እንዳለ ሆኖ ከዕድሜያቸው ማጠር ጋር በኤችአይቪ ኤድስ የመጠቃት ዕድላቸው እጅግ በጣም ሰፊ፣ለኪንታሮትና ለብሽሽት፤ ለአባላዘር አከባቢ ቁስለት እጅግ የተጋለጡ ናቸው፡፡ይህ ደግሞ ከእግዚአብሔር ለመራቃችን ዋና ምልክቱ ነውና፡፡እግዚአብሔር የሚታዘዙትን በደዌና በህመም በሰቆቃም አይቀጣም፡፡(ዘዳ.7÷15) “ … ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ …”(ሮሜ.1÷26-27) የዚህ ውጤት ለማይረባ አዕምሮ ተላልፎ መሰጠት ሆነ፡፡በዚህም ግብረ ሰዶማዊነት የማይረባ አዕምሮ የወለደው አጸያፊ ኃጢአት ነው፡፡
     ግብረ ሰዶም በተመሳሳይ ጾታ መካከል ነውና የሚፈጸመው የሰው ዘር እንዳይቀጥል “ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም … ”(ዘፍ.1÷28) የሚለውን መለኮታዊ ቃል የሚሽር ድርጊት ነው፡፡እስከተቆረጠችው የክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት ቀን የሰው ዘር እንዲቀጥል የመለኮት ቁርጥ ሃሳብ ነው፡፡ግብረ ሰዶማዊነት ግን የዚህ ተቃራኒ ነውር ነው፡፡ተፈጥሮ እንዳይባክንና የሰው ዘር እንዳይበከል የእግዚአብሔር ሃሳብ ሆኖ ሳለ በኃጢአትና በበደል ምድር ስትረክስ ግን ጻድቃን ብቻ “ማራናታ፤አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።” የሚሉ አይደሉም፡፡ፍጥረትም የክርስቶስን መምጣት በናፍቆት የሚጠባበቅ ነው፡፡(ሮሜ.8÷19)መንፈስ ቅዱስም እንኳ ከእኛ ጋር ሆኖ መድኃኒቱን ጌታ ና ይላል፡፡(ራዕ.22÷17፤20)
   እግዚአብሔር የሞተለት ሰው እንዲሞት አይወደድም፡፡ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ከመቼውም ጊዜ በላይ ልትነቃ ይገባታል፡፡ግብረ ሰዶማውያን በደጇ ብቻ የቆሙ አይደሉም፤አንኳኩተው በበሯ በኩል ገብተዋል ፤ተደብቀውም ብዙ ልጆቿን በመርዝ ነውራቸው እየበከሉባት ነው፡፡ትላንት አብረን እናገለግል የነበርን ወንድሞቼና እህቶቼ በዚህ ነውር ተይዘው ሳይ መንፈሴ ይቃጠላል፡፡አዎ! ከዛሬ የተሻለ ቀን ያለ አይመስልም፡፡የሚያድነው ወንጌል ለፍጥረት በችኮላ ሊሰበክ ይገባል፡፡ስብከታችን፣ቅዳሴያችን፣ጾማችን … ልማድ ሆኖብን ኃይል የለውም፡፡ትወልድ እንዲፈወስ የመዳን ወንጌል ይናኝ፡፡በኃይልም ይሰበክ፡፡
     አልያ ግን “አርነታቸውን” ለሥጋ ምክንያት አውለውት “በመቅደሳቸው ውስጥ ግብረ ሰዶማውያንን እንደዳሩት” ምዕራባውያን በእኛም ላለመሆኑ ዋስትና የለንም፡፡ይልቁን እየተደራረበ አንዱን ሳንጨርስ የሚተካውን የኃጢአት የቤት ሥራችንን በንስሐ ልብ  ተመልሰን በክርስቶስ ደም እንቋጨው፡፡ጌታ የመዳኑን ወንጌል ለኃጢአተኞች በመግለጥ ሰዎች ወደልባቸው እንዲመለሱ  የሚያደርገውን ጸጋውን ያብዛልን፡፡አሜን፡፡ 

7 comments:

  1. Berta Geta kante gar yihun.tru tsihuf new mobayil

    ReplyDelete
  2. "ጌታ የመዳኑን ወንጌል ለኃጢአተኞች በመግለጥ ሰዎች ወደልባቸው እንዲመለሱ የሚያደርገውን ጸጋውን ያብዛልን፡፡አሜን፡፡ ".... አሜን ወንድሜ፡፡

    ReplyDelete
  3. ይህ ስድብ ነው::ሌላ የፈለከው በል እንጂ "ገዳሞቻችን/መነኮሳቶቻችንና ሰንበት ት/ቤቶቻችን" በፍፁም የግብረ-ሰዶማውያን መንፈስ ይታይባቸውል ብለህ መፈረጅ አትችልም:: ይህን ያልክበት መስረጃ-መረጃ ማቅረብ ስልማትችል ይቅርታብትጠይቀን ይሻልሃል::

    እንዳውም ቤተ ክርስትያናችን "ግብረ-አውናን" ውጉዝ ነው ብላ ታስተምራለች...አትልም ብለህ ደግም ኮንናት...

    ReplyDelete
  4. ይህ ስድብ ነው::ሌላ የፈለከው በል እንጂ "ገዳሞቻችን/መነኮሳቶቻችንና ሰንበት ት/ቤቶቻችን" በፍፁም የግብረ-ሰዶማውያን መንፈስ ይታይባቸውል ብለህ መፈረጅ አትችልም:: ይህን ያልክበት መስረጃ-መረጃ ማቅረብ ስልማትችል ይቅርታብትጠይቀን ይሻልሃል::

    እንዳውም ቤተ ክርስትያናችን "ግብረ-አውናን" ውጉዝ ነው ብላ ታስተምራለች...አትልም ብለህ ደግም ኮንናት...

    ReplyDelete
  5. የምዕራባውያን የዕድገታቸው መሠረት ወንጌል እንደሆነ ይነገራል፡፡ what it mean? I Conform that you are really stupid.

    ReplyDelete
  6. awo anqelafetenal ende yonas!!!!!!!alaneqlafawem belo kememot yeseweren(nigus abebe qoshashachenene egna kalanesane manem ayanesalenem)abenez....tebarek gerum difek

    ReplyDelete
  7. Anti eferetbes minwe kizeh hayimanot layi betensa anti ewent diyakon nehe ayimselgnem antin belo diakon Betkirestian yihene endemtawgzi tawekale ewent Diakon khonk yihech k MARANATA kimilwe kiprotestat sergogboch yitekorege tsuhufe nwe

    ReplyDelete