Wednesday 4 December 2013

ብቻውን እናምልክ

በጸናች ክንዱ
በተዘረጋች እጁ
በድንቅ እየሠራ
ምሪት እየመራ
ያዳናቸውን ቃል የዕሪታቸውን መልስ
ኪዳኑን ሲረሱ ልባቸውም ሲረክስ
የአርባ ቀን ቆይታ ትዕግስት ነስቷቸው
ያወጣን ያዳነን ሙሴ ቀረ ብለው




የሚታዩ አማልክት ሊሰሩ መከሩ
በአመጻ ሰልጥነው ፍጹም ደነቆሩ፡፡
                 ቁልቁል ተንደርዳሪ የለውም መቆሚያ
                 ሙሴንም ጣሉና ሰገዱ ለጥጃ
                 ከግብጽ ባርነት ከሞት ቤት ያወጡን
                 እንዲያ በታ'ምራት ለማዕረግ ያበቁን
                 እኒህ ናቸው አማልክቱ
                 ስለደስታው ብሉ ጠጡ …
               ቀኑ ዛሬ ‹‹የእግዜር›› በዓል ሆኗል
               ደስታ ተድላው ተትረፍርፏል
               ብለው ገና ሳይጨርሱ
               መጣ የአምላክ ጽኑ ፍርዱ፡፡
ከሰገነት መውረድ መቅኖ የለሽ ጉዞ
ደንቁሮ ታውሮ ተዋርዶ ደንዝዞ
ጥቂት በመታገስ ጸንተው ስላልቆሙ
ትልቁን ፈጣሪ በክፉ አማልክት ዝሙት ስላስቀኑ
ከህይወት መጽሐፍ ተደምስሰው ጠፉ፡፡
በሚከፋ ስህተት እኛም እንዳንያዝ
ሰብሮ በሚያቆስለው በሰንበሌጥ ምርኩዝ እንዳንመረኮዝ
አይናችንን ከእርሱ ከትልቁ ጌታ
ነቅለን ወደፍጡር አና'ርግ ለአፍታ እንኳ
አሊያ እንደ እስራኤል ነውና መዋረድ
እርሱን አንዱን ጌታ ብቻውን እናምልክ፡፡

5 comments:

  1. አሊያ እንደ እስራኤል ነውና መዋረድ
    እርሱን አንዱን ጌታ ብቻውን እናምልክ፡፡

    ReplyDelete
  2. Replies
    1. leka befitem esun atamelek ende ?

      Delete
  3. lela tamelek neber ende befit ?

    ReplyDelete