Thursday 26 December 2013

የክብር ፍጻሜው

እስኪ አትቸኩል ኤልያብ አልሆነም
የእግዚአብሔር ሞገስ ዘለግታ አይደለም
ዳዊት ነው በሞገስ ሊቆም የሚቻለው
ጌታ ሊያድርበት ወዶ የፈቀደው
የእንጨት ስራ አይደለም መቅደሱ ልብ ነው።




እሞታለሁ አትበል በቁም ሞተህ ሳለ
መሞትህ ላይፈይድ ዝምን ማን ገደለ
ግና አትቃወም ታዘዝ ለፈቃዱ
የሚበልጠው ነገር መገዛት ነው ለአንዱ፡፡

ከእርሱ የሆነ እንደሁ ፍጹም ነው በእውነቱ
ሞቱ እንኳ የጌታ ጸድቋል በአባቱ
ወዲህ ሲል እግዚአብሔር ወዲያ የምትዞረው
በሰው ሀሳብ ሁሌ 'ምታገለግለው
ለጥቂቷ ዕድሜ ለቀረው ዘመንህ
ከእርሱ የሆነውን ሀብቱን ሀብቴ ብለህ
ያለህን ሁሉንም ተከተለው ጥለህ
ይህ ነው መከበሪያህ ከፍ ብሎ መታያህ
የአንተ ፈቃድ ወድቆ የእርሱ ሲነግስብህ
ልብህን ሀሳብን ተውለት ይያዘው
ከእርሱ የሆነው ነው የክብር ፍጻሜው።

2 comments:

  1. tebarek tebark yesun fekad lemagelegel enederedagn tseleyelegn

    ReplyDelete
  2. fekadun enedagelegel fekuden metal alebegn tebarek behulu neger

    ReplyDelete