Thursday 19 December 2013

ቀን ሳለ ተመለስ

መቅረዝ ዕድሜህ ፈክቶ
እንደበር ተከፍቶ
ህመምህ ርቆ
መቆምህም ፀድቆ
ዳፍንት ሳይመጣ
ቀኑ ሳይሆን ማታ፤




ድንገት ሳይጨላልም
ኑሮህ ሳይገደም
ብርሃንህ ሳይያዝ
ጉልበት ሳይደነዝዝ
ቀን ሳለ ተመለስ
ተንደህ ሳትፈርስ፡፡

ታግለህ በምትጥለው
ሮጠህ በምትቀድመው
በጉብዝና ወራት
በዘር መዝሪያህ ሰዓት
በደመ ክርስቶስ
የታነጽኽው መቅደስ
ቀን ሳለህ የመዳን
ይኽው በእውነት አሁን
ዛሬ ይሁን ልደትህ
ከፈጠረህ ጌታ መታረቂያ ቀንህ፤

የዛገው ቀለበት ያደፉት ልብሶችህ
የራስህ ባርኔጣ መጫሚያ የእግሮችህ
የተሰባበረው መመርኮዣ ዘንጉ
ይለወጡ ዛሬ ፍፁም ይታደሱ
የጠፋው ይህ ልጄ ተገኘልኝ ዛሬ
ሙቱ ህያው ሆነ የሚለው ዝማሬ
ይሰማ ስላ'ንተ በብርሐን ቀኑ
ቀን ሳለ ተመለስ ከዛሬም አሁኑ፡፡

1 comment: