Please read in PDF
በአጭር ቃል በእኛ መካከል ዝሙት እንዳለ ይታወቃል፡፡ኃጢአት ከእግዚአብሔር መንግስት እንደሚያወጣ ለድርድር በማይቀርብበት በሐዲሱ ኪዳን ዘመን እንደነውር እንኳ ሳይቆጠር ዝሙት በመካከላችን አብቦ ፈክቷል፡፤መናፍቅነትን ሊያወግዝ ደቦ የሚጠራ ህብረታችን ዝሙትን ለማውገዝና እንደመናፍቅነት ያለ ኃጢአት ነው ለማለት ድፍረቱ የተሰለበብን ይመስላል፡፡
ቤተ ክርስቲያንን በጥፋታቸውና በአሰቃቂነታቸው ወደር ያልተገኘላቸው አላውያን ነገስታት ፈጽሞ ከክርስቶስ ሊለይዋት አልቻሉም፤ነገር ግን የገዛ ኃጢአቷ ፈጽሞ ከጌታዋና ከሙሽራዋ ኢየሱስ ይለያታል፡፡ የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን በከባድ ተግሳጽ ከተወቀሰችበት ኃጢአት አንዱና ትልቁ ባላመኑ አህዛብ ዘንድ እንኳ ያልተሰማ አዲስ ነውር በክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መሰማቱና መታየቱ ነው፡፡ፍጥረታዊውና እንሰሳዊ ማንነታችን ውስጣችንን ሲገዛ በአደባባይ ለመፈጸም ከማናፍርባቸው ኃጢአቶች አንዱ ዝሙት ነው፡፡
ፍጥረታዊ ሰው ለነውሩ ዳርና ድንበር የለውም፡፡በእግዚአብሔር አደባባይ ከመናገር እስከማድረግ እንኳ ፊቱን አይመልስም፡፡የተገለጠ ኃጢአቱን ሲናገረው እንደጀብዱነትና ዕውቀትም ያወራዋል፡፡ዝሙቱ በግልጥ ታውቆ በቤተ ክርስቲያን መካከል ይመላለስ ለነበረው ቆሮንቶሳዊ ታላቁ ልከኛ ሐዋርያ ፦ ከቅድስቲቱ ህብረትና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያስተላለፈው ውሳኔ የዛሬዎቹን አብያተ ክርስቲያናት በግልጥ የሚዘልፍ ነው፡፡በማናኛውም ሰው ላይ አብያተ ክርስቲያናት የሚያስተላልፉት የውግዘት (ከማህበረ ምዕመናን መለየት)ውሳኔ እንደቅዱስ ጳውሎስ ካልሆነ ውግዘታቸው ከቡድንና ከግለሰብ ሐሳብ የመነጨ ጥላቻ እንጂ የመንፈስ ቅዱስ ሐሳብ አይሆንም፡፡እንኳን በበደለ በአንድ ምዕመን በአገልጋዮች ላይ እየተወሰደ ያለው የዛሬው “ውግዘት” ግን እጅጉን የሚያሳዝን ነው፡፡
ወደቀደመ ነገር ስንመለስ በሐገራችን በደቡብ ባለ አንድ “ታላቅ” ገዳም ውስጥ በኮሚቴነት በሚያገለግል አንድ ሰው “ሆቴል” ቤት ውስጥ ዕድሜያቸው አስራ ስምንት አመት የማይመሉ እህቶች ለዝሙት ከመማገዳቸው ባለፈ እርቃን ጭፈራና የህብረት ዝሙት እንደሚፈጸም ጠራራ ፀሐይ ያስተዋለው እውነት ነው፡፡ግና ዛሬም ይኸው ሰው ለቤተ ክርስቲያን “ቆሜያለው” ከሚል ማህበር ጋር “በቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያንን እየመሩ” አሉ፡፡
ሌላ የነውር ምሳሌ፦በምስራቅ ሐገራችን “በታወቀ” አንድ ገዳም “ድንግልናን ማስወሰድ” እንደታላቅ ስዕለት ይቆጠራል፡፡በአይኔ በቦታው ተገኝቼ እንዳየሁት ስዕለቱን ለማስፈጸም የሚቆሙ አመንዝራ ወንዶች በአከባቢው የክብረ በዓሉ ዕለት ጥግ ጥግ ይዘው “ባዕለስዕለትን” ሲጠይቁ የማፈር እንግዳ ጠባይ ፈጽሞ አይታይባቸውም፡፡ ይህ እየሆነ ያለው በአውሮፓ ወይም በአሜሪካ በሚገኝ አንድ ቤተ እምነት ውስጥ አይደለም፤እዚሁ “ቅድስት የክርስቲያን ደሴት” ብለን በምንሸልልባት ኢትዮጲያ ውስጥ ነው፡፡ምናልባት ይህን በአዋጅ ቤተ ክርስቲያን አልፈቀደችም ብለው የሚሟገቱ እንዳሉ አምናለሁ፤እውነት ነው ቤተ ክርስቲያን አልፈቀደችም፣አትፈቅድም፡፡
ዳሩ ግን ፈጻሚዎቹና አስፈጻሚዎቹ የራሷ የቤተ ክርስቲያን አካላት አይደሉምን? የሚፈጸመውስ እርሷ ባዘጋጀችው ክብረ በዓልና ሥፍራ አይደለምን? በጉያዋስ ይዛ የእኔ አማኞች ናቸው ብላስ የምትጠራቸው አይደለምን? ስለምንስ በግልጥ መክራ ፣ዘክራ፣ አስታማ ፣አገላብጣ አልመለስ ካሉ ለይታ አታወግዝም? ከነውራቸውስ እስኪመለሱ ለምን ከምዕመናን አንድነት “ከቅድስቲቱ ህብረት” አትለይም? እውነት ዝሙት ከመናፍቅነት አንሶ ነውን? የየትኛው ትንሽ እባብ መርዝ ነው ነድፎ የማይጎዳ? የትኛውስ ትንሽ ኃጢአት ነው የቤተ ክርስቲያንን ቅድስና የማያረክስ?
አዎ! አለቅጥ እንደቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ታብየናል(1ቆሮ.5÷2)፡፡የእግዚአብሔርን ጸጋ በአገባብ በእውነት መረዳትና ማስተዋል ካለመቻላችን የተነሳ አርነታችንን ለኃጢአት ተጠቅመንበታል፡፡በክርስቶስ የተሰጠንን ከኃጢአት ነጻ የመውጣት አርነት ለሥጋ ኑሮአችን ምክንያት እንዲሆነን አልነበረም፡፡
ዳኛው ቀን ካፋታት ሴት ጋር ማታ ያመነዝራል፣ካህኑ ከንስሐ ልጁ ጋር ሚስቱን ተደብቆ ይማግጣል፣ ወጣቱ ዝሙትን እንደአንድ የ“ማደግ ምልክት” ቆጥሮታል፣አሮጊቶቹ በፌዛቸው የጥንት “አተራማሽነታቸውን” እንደደህና ወግ ያወሩታል፣ፊልሞቻችን ዝሙትን በፍትፍት ፊት የዝሙት መርዝ ሰንገው ያቀርቡታል ፣ሆቴሎቻችን የደሩትና የደመቁት በዝሙት ወዝ ነው… በዝሙት ምክንያት የሚመጡ በሽታዎች ፈውስ አልባ መሆናቸውን እያየን እንኳ ተጠይፈን ለመሸሽ አቅም አጥተናል፡፡
በጥንት የሮማ ከተማ ጎዳናዎቿ የደመቁት ለዝሙትና ለጣዖት አንገዛም ያሉ ውድና ውብ የክርስቶስ ሰማዕታት ሰውነታቸው በሰም እየተነከረ በሚለኮስባቸው እሳት ነበር፡፡ዛሬ ግን የሀገራችን ታላላቅ ከተሞች በሌሊት “የሚደምቁት” እንደዝንጀሮ ለዝሙት በሚጓተቱ አመንዝሮችና ጋለሞታዎች ነው፡፡ ቀን ቢሮና ከትዳር አጋራቸው ጋር የሚውሉት ማታ መሸታ ቤት አድረው ማለዳ ኪዳንና ቅዳሴ፣ ጸሎትና ስዕለት ይዘው ሲመጡ ላየ ወይ ፍጻሜያችን ያስብላል፡፡አዎ! የከተሞቻችንና “የታላላቅ” ሆቴሎቻችን ሌሊት መዓትና መቅሰፍትን የሚጣራ ነው፡፡ሐገሬ ከእንቅልፍሽ ማን ባነቃሽ!!!
ቤተ ክርስቲያን ከተሰጣት ሥልጣን ትልቁ አንድ አስነዋሪ ተግባር የፈጸመ ሰው በመካከልዋ ቢገኝ በጌታችን በኢየሱስ ኃይል፣በቃሉና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በድርጊቱ ተጸጽቶ ንስሐ በመግባት እንዲመለስ ከምዕመናን አንድነት ልትለየው እንደምትችል ነው፡፡የምትለየው የኃጢአተኛው መንፈሱ በጌታ ቀን በተባለችው ዳግም ምጽአት ትድን ዘንድ ከእግዚአብሔር ህዝብ ለይታ ክፉኛ እንዲቀጣ ወደሰይጣን ግዛት በመስደድ ነው፡፡ ምክንያቱም ጥቂት እርሾ ብዙውን ሊጥ ያበላሻልና፡፡በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ሆኖ እርሾ ክፉ ኃጢአት የማያውቅ ንጹህ ሊጥ አለ፡፡(2ቆሮ.5÷17)፡፡
ይህ ሐሳብ የመንፈስ ቅዱስ ሐሳብ ነው፡፡ጥቂቱ እርሾ ብዙውን ንጹህ ሊጥ ያቦካዋል፡፡ጥቂቱም የኃጢአት እርሾ ንጹሑን የአማኞች ህብረት ያረክሰዋል፡፡በዚህም ያለእድፈት ልትኖር የተጠራችው ቤተ ክርስቲያን በእድፈት ትያዛለች፡፡እግዚአብሔር አብ ስለኃጢአት ዋጋ ውድና ተካካይ የሌለው ልጁን ጨክኖ በቀራንዮ ላይ እንደበግ አርዶታል፡፡በውኑ በልጁ እንዲህ የጨከነ ጌታ አብ ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ስለምትሰራው ኃጢአት የማይጨክን የማይፈርድ ይመስላችኋልን? እንደልቤ ያለውን(ሐዋ. 13÷22)ዳዊትን ዝሙት በፈጸመ ጊዜ እንዴት ባለ ቅጣት ነው የቀጣው?(2ሳሙ.12÷9-12)፡፡
ለምን ነው እንዲህ ያለ ነውር በመካከላችን እያለ ዝምታው? ስለምንስ ነው ኃጢአትን ኃጢአት ነው ማለት የተሳነን? ከእንደነዚህ አይነት ሰዎች ጋር ምግብ እንኳ እንዳንበላ ታዘናል(1ቆሮ.5÷11) ምክንያቱም እውነተኛ አማኝ ከእነዚህ ሰዎች ግንኙነቱን ባጠበቀ ቁጥር አምላኩን ያስነቅፋል፤ሌሎችም ደግሞ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ያለውን ርኩሰት የምትቀበል ሊመስላቸው ይችላልና፡፡
ቤተ ክርስቲያን እንደጌታ ትምህርት በግልጥ የመቆጣት፣ የመገሰጽና የማስተካከል ኃላፊነት አለባት፡፡ (ማቴ.18÷15)፡፡እገሌ፣እገሊት፣እነእገሌ … “መናፍቅ” ናቸው የሚለው ድፍረታችን በቅድስና ስፍራና አከባቢ አይን ያወጣ አመንዝራነታችንንም ለመገሰጽ አይናችን ይገለጥ፤ከንፈራችንም ይከፈት፡፡ይህም ከመናፍቅነት የማይተናነስ ከባድ የሥጋ ሥራ ነውና፡፡(ገላ.5÷21)
ጌታ ሆይ ቤተ ክርስቲያንን ዳግም በጸጋህ በሚበዛ ቅድስና አጎልምሳት፡፡አሜን፡፡
Be blessed,thanks ,most of the time u touch alot of things how Christians being Christian,it's really it makes sense this is how it be teaching I agree
ReplyDeleteall what you saying awesome article.
God bless you.
እኔ እኮ የምለው ታዲያ እዚህ ምንፍቅና የሞላበት ቤት ዲያቆን የሚል ተቀጥላ አንጠልጥለህ ምን ትሰራለህ? ለዝሙትማ አንተን ጨምሮ የተወገዙት መናፍቃን መቼ ነው ጋብ ያላችሁት? ልክ እንደ ፆታዊ ዝሙት ሁሉ ወደ ሌላ ሃይማኖት እያዩ መመኘትም ዝሙት ነው:: ስንቱስ የምታደንቀው "መናፍቅ" ያለሆነው ፓስተሮች የምሰሩትንስ አትነግረንም ታዲያ:: አሁንስ የምታወሩት ሁሉ እጅ እጅ አለ:: ቢያንስ ራስህን ዲያቆን አትበል::
ReplyDeleteአብዛኛዎቻችን እኛ ኦርቶዶክሳውያን የተሻለና መልካም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አመለካከት ያለውን ሰው ማክበርና ነገርን በመመርመር ከስድብና ከጥላቻ የጸዳ የሚያንጽና ልብ የሚያቀና ምክር መለገስ የምንጀምረው መቼ ነው?በእውነት ለኃይማኖታችን የምንቀናው በመሳደብ፣በማውገዝ፣በመደብደብ ነው? እግዚአብሔር ግን በአመጽ አይከብርም፡፡ስለዚህ ወንድሜ ወንድምህን ከምትጠላውና ከምታሽሟጥጥበት በፍቅር ምከረው በፍቅር ውቀሰው፡፡ፍቅር ከጥላቻ ይልቅ የሚገዛ ጉልበት አለውና፡፡
Deleteወንድም አይተሃዋል አሱ የፃፈውን ለመሆኑ? የሚያንፅ ነገር እንደፃፈ አላወኩም:: ለኔ ዲያቆን የሚል ማአረግ የሰጠችውን ቤተክርስቲያን ሲዘልፍ ነው ያየሁት:: ሰውን ስም መጥራት እስኪቀረው ሲሰድብና ሲኮንን ነው ያነበብኩት ይህን መቼም " የተሻለና መልካም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አመለካከት ያለውን ሰው ማክበር" (ሰው ማክበር) ነው ካልክ አንተ ታውቃለህ:: በፍቅር ስለመምከርም ቢሆን መቼም ይህን ፅሁፍ ያመጣው ፀሐፊው ነውና መቼም ያማቸውን (የገሰፃቸውን) ሰዎች በፍቅር ቢመክር ኖሮ እዚህ ባልፃፈው እኔም ባልፃፍኩ አንተም ባልከፋህ:: ስለዚህ ለሌላው ያዘዝነውን መድሃኒት ራሳችንም ብንጠቀምበት መልካም መሰለኝ:: ካለበለዚያ ግብዝነት ነው የሚሆነው::
Deleteእንዳለመታደል ተግሳጽ አንወድም ኬክ ብቻ መምረጣችን ለጎመዘዘው ብዙም ቦታ የለንም ዘለፋ ለመዝለፍ ይህን ያህል የሚደከም አይመስለኝም፡፡የሚታየኝ ነገር ቢኖር ስለዝሙት ዝም በተባለበት በዚህ ጊዜ የእርሱ መናገር ሲያንስ እንጂ የበዛ አይመስለኝም፡፡ኤርምያስ ስለእስራኤል
Deleteትንቢተ ኤርምያስ 3
1 በሰው ዘንድ። ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ ከእርሱም ዘንድ ሄዳ ሌላ ወንድ ብታገባ፥ በውኑ ደግሞ ወደ እርሱ ትመለሳለችን? ያች ሴት እጅግ የረከሰች አይደለችምን? ይባላል። አንቺ ከብዙ ውሽሞች ጋር አመንዝረሻል፥ ወደ እኔም ትመለሻለሽን? ይላል እግዚአብሔር፦
2 ዓይንሽን አንሥተሽ ወደ ወናዎች ኮረብቶች ተመልከቺ ያልተጋደምሽበት ስፍራ ወዴት አለ? ዓረባዊ በምድረ በዳ እንደሚቀመጥ አንቺ በመንገድ ላይ ተቀምጠሽ ትጠብቂያቸው ነበር በግልሙትናሽና በኃጢአትሽ ምድሪቱን አረከስሽ።
3 ስለዚህ ካፊያ ተከለከለ፥ የኋለኛውም ዝናብ ጠፋ የጋለሞታም ሴት ፊት ነበረብሽ፥ ታፍሪም ዘንድ እንቢ ብለሻል።
ማለቱ ዘለፋ ነው?ወይስ ያሳደገውን የጌታ ህዝብ መናቁ ነው? ሌላ ልጨምርልህ ይኸው ነቢይ ስለጽዮን እንዲህ ያለው ስድብ ነውን?
ትንቢተ ኤርምያስ 6
1 እናንተ የብንያም ልጆች፥ ክፉ ነገር ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ይጐበኛልና ከኢየሩሳሌም ውስጥ ሽሹ፥ በቴቁሔ መለከቱን ንፉ፥ በቤትሐካሪም ላይ ምልክት አንሡ።
2 የተዋበችውንና የተሰባቀለችውን የጽዮንን ልጅ አጐሰቍላለሁ።
3 እረኞችና መንጐቻቸው ወደ እርስዋ ይመጣሉ፥ በዙሪያዋም ድንኳኖቻቸውን ይተክሉባታል፥ እያንዳንዱም በስፍራው መንጋውን ያሰማራል።
4 በእርስዋ ላይ ሰልፍ አዘጋጁ ተነሡ፥ በቀትርም እንውጣ። ቀኑ መሽቶአልና፥ የማታውም ጥላ ረዝሞአልና ወዮልን።
5 ተነሡ በሌሊትም እንውጣ፥ አዳራሾችዋንም እናፍርስ።
6 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። ዛፎችዋን ቍረጡ፥ በኢየሩሳሌምም ላይ አፈርን ደልድሉ ይህች ከተማ የምትቀሠፍ ናት መካከልዋ ሁሉ ግፍ ብቻ ነው።
7 በጕድጓድ ውኃ እንደሚፈልቅ፥ እንዲሁ ክፋትዋ ከእርስዋ ዘንድ ይፈልቃል ግፍና ቅሚያ በእርስዋ ዘንድ ይሰማል፥ ደዌና ቍስልም ሁልጊዜ በፊቴ አለ።
8 ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነፍሴ ከአንቺ እንዳትለይ፥ አንቺንም ባድማና ወና እንዳላደርግሽ፥ ተግሣጽን ተቀበዪ።
9 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰው ወይኑን እንደሚቃርም፥ እንዲሁ ከእስራኤል የቀሩትን ፈጽሞ ይቃርሙአቸዋል እጅህንም እንደ ለቃሚ ወደ እንቅብ ዘርጋ።
10 ይሰሙኝስ ዘንድ ለማን እናገራለሁ? ለማንስ አስጠነቅቃለሁ? እነሆ፥ ጆሮአቸው ያልተገረዘች ናት ለመስማትም አይችሉም እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቃል ለስድብ ሆኖባቸዋል፥ ደስም አያሰኛቸውም።
11 ስለዚህ በእግዚአብሔር ቍጣ ተሞልቻለሁ ከመታገሥ ደክሜአለሁ በሜዳ በሕፃናት ላይ በጕልማሶችም ጉባዔ ላይ በአንድነት አፍስሰው ባል ከሚስቱ ጋር ሽማግሌውም ከጎበዙ ጋር ይያያዛልና።
12 እጄን በምድር በሚኖሩ ላይ እዘረጋለሁና ቤቶቻቸው እርሻዎቻቸውም ሴቶቻቸውም በአንድነት ለሌሎች ይሆናሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፦
13 ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስትን ያስባሉና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ በተንኰል ያደርጋሉና።
14 የሕዝቤንም ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ ሰላም ሳይሆን፦ ሰላም ሰላም ይላሉ።
15 ርኩስን ነገር ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፦
ወንድሜ ቃሉለስድብ አይሁንብህ?የገሰጸ እንደቃሉ የተቆጣ ሁሉ የተሳደበ የዘለፈ አይደለም በመካከላችን ስላለው ዝሙት ማስተባበያ ሳይሆን ንስሐ ነው የሚያዋጣው
እግዚአብሔር ዛሬ ቢመጣ እንዲህ የማይል ይመስልሀል?
ትንቢተ ኤርምያስ 9
1 ተወግተው ስለ ሞቱ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ራሴ ውኃ፥ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ!
2 ሁሉም አመንዝሮች፥ የአታላዮች ጉባኤ ናቸውና ሕዝቤን እተዋቸው ዘንድ ከእነርሱም እለይ ዘንድ በምድረ በዳ የመንገደኞች ማደሪያን ማን በሰጠኝ?
3 ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና እኔንም አላወቁምና፥ ይላል እግዚአብሔር፦
4 ወንድምም ሁሉ ያሰናክላልና፥ ባልንጀራም ሁሉ ያማልና እናንተ ሁሉ ከባልንጀሮቻችሁ ተጠንቀቁ፥ በወንድሞቻችሁም አትታመኑ።
ስለዚህ ወዳጄ አስተውልና ተናገር እንጂ በከንቱ አትቆጣ
ከምርህ ነው ግን? ለዛ ነዋ አንድ ሙሉ ጥቅስ የፃፍኩት:: ስለምንፍቅና ስለማስመሰልስ ጥቅስ አታውቅም? ዝሙት ብቻ አይደለም ሙስና ምንፍቅና በድቁና ስም ማስመስል ሁሉ ቤተ ክርስቲያኗን ወሯታል:: እሱ ዝሙትን ለይቶ አነሳ እኔ ምንፍቅናና የሃይማኖት ዝሙትን አነሳሁ:: ስለዚህ በራስህ ምክር መሰረት ወዳጄ አስተውልና ተናገር እንጂ በከንቱ አትቆጣ:: ምአራፍ መጥቀስም አያስፈልግህም::
Deleteabenezer ewnet endesemeh ante yebetekerestian lej neh?????bemesraq yemetelew ene teweleje yadeghut mesrak new yalew and gedam new endieh eyalk yemetaweraw keyet amteteh new antebecha neh yehe yetegeleteleh weyes nte kemiderederut west alehebet? enem beyeametu 2x kemehed albozenkum leante yemigeletsew gen betam yemideneq keaemro belay yehone new EWNET ANTE YEBETEKERESTIAN LEJ KEHONK YETEDEREGE NEGER ENQWAN BIHON MANEM ENATUN ASALEFO AYSETEM!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! YABESACHEHEM WEGZETU KEHONE endalhonachehu besera masayet techlalachehu, ketelo degmo betsom betselot mebertat, beterefe gen LEMEN SERACHEN TAWEKE BELEH ENDETENADEDK YASTAWEKAL betewedem betetelam TEWAHEDON YESOL DEJOCH AYCHLWATEMMMMMMMMMMMMMMMM:
ReplyDeleteyegeremal anetem mesadeb jemerek ?gen sedeb kemanew ?tawekwalek ?mechem sedeb K E/R aydelem ketelat enji
Deleteselezih temehereteh keyet endehon asetwel
xian afu lemesegan new eneji lesedeb ayekefetem
bedeneb selemakeh geremogn new wedaje
weye teamer anetem mesadeb jemerek ?
ReplyDeletebalen eweket erasachen enanets mejemeria sedeb k EGEZIABEHER ayedelem ketelat enji
ReplyDelete