Friday 12 April 2013

እንገባ ዘንድ አለን


Please read in PDF

ምድሪቱ ያልተነካች የማርና ወተት
በረከቷ ብዙ የሚያጠግብ ሕብስት
ተስፋው፥ ከግንብ ይልቅ የጸና

ስሙ በጠላት ፊት ሞገስና ግርማ
የአንደበትህ ውበት የእንቆቅልሽህ መልስ
የረሀብህ ጥጋብ የደዌ ሁሉ ፈውስ

ሊያወርስህ ያሰበው ገና ገና ብዙ
የእግዚአብሔር ሕዝብ ሆይ! ሚጠብቅህ ሳይዝል ዓይኖችህ ፈዘዙ፤
ገና በማለዳ ጉልበት በረሰ
ምኑንም ሳታየው ሀሞትህ ፈሰሰ
አረጀህ ሳይነጋ ጮራህ ሳይፈነጥቅ
ጸጋ በዝቶ ሳለ የመንፈስ ቅዱስ ጽድቅ
ንቃ ወገን ንቃ ወንጌሉ ሲዘራ
ወደ እግዚአብሔር መንግስት፥ እንገባ ዘንድ አለን፥ በብዙ መከራ፡፡

No comments:

Post a Comment