Thursday 4 April 2013

አለቀሰ አሉኝ


Please read in PDF


ነፍርቆ አለቀሰ አሉ ፣ሐበሻ ተነቅሎ ወጥቶ
አይኑን እያረጠበ ፣እንባ በእንባ ተራጭቶ
አነባ ደረቱን ደቅቶ ፣ተክዞ አመድ ነስንሶ
ማቅ ለብሶ የእዬዬ ሲቃ፣ የሐዘን ግድቡን ጥሶ
ከአልጋው ወረደ አሉ ፣ይህ ህዝቤ ከምንጣፍ ሊውል
ቤቱንም ትቶታል አሉ፣ ከድንኳን ሄዶ ለማደር
ጮኸ አሉ ባ'ደባባዩ፣ ልቅሶውን እያጋጋመ
ስንወድህ ስንናፍቅህ ፣መሪያችን የት ሄድክ? እያለ፡፡

          ግና…
         እውነት ነው ያ ሁሉ ልቅሶ
         እውነት ነው ያ ሁሉ እንባ
         እውነት ነው ያ ሁሉ ፍጅት
         እውነት ነው ያ ሁሉ ዋይታ
         የሼሁ የቄሱ እሪታ
         የፓስተር ሁሉ ጋጋታ
         የዚያ ህዝብ ሁሉ ኡኡታ
         ሽንገላ ማስመሰያ ነው
         ልቅሶውም የአዞ እንባ ነው
         በህይወት እያለ በቁም፣
         በርታልን አንተ የ'ኛ ወንድም፤
         ደጅህን ጌታ ይውረሰው
         ዙፋንህን እርሱ ይቀድሰው
         በትርህ ቅንነት ትፍረድ
         በምድርህ ድኃ እንዳይወድቅ
                    ፊቱንም እርሱ ያብራልህ
                    መንገድህን ያከናውንልህ
                    ሳይለው ሲረግመው ኖሮ
                   አሉ አለቀሰ በሐዘን እንጉርጉሮ
መች እንዲህ ነበር ወጉ፣
ሟች እያከበሩ፣
ቋሚ 'የጠረጠሩ፤
ሲሞት እየተብሰከሰኩ
ከማልቀስ እየነደዱ
ይልቅስ ጠቃሚው ነገር
እንዳይዝል መጸለይ ነበር፤
        እንኪያማ… 
        የመውደድ የፍቅር ጥጉ
        መሆን ነው አብሮ ከጎኑ
        አሁንም አልመሸም ቀኑ
        ዙፋኑ እንዲቆም ለእውነት
        እናስብ ዛሬም በጸሎት፡፡
        አልያ ግን…
        አኩኩሉ የህፃናት ጨዋታ
        ሽንገላ የይምሰል ዋይታ፡፡
ድካሙን በተግሳጽ ቀለም
ነቅሳችሁ ሁሌ በማረም
አብራችሁ ብዙ ደክማችሁ 
በሞቱ የተከዛችሁ
ክብር ይሁን ለትጋታችሁ
ኢትዮጲያን ለመውደዳችሁ!!!

1 comment: