Tuesday 9 April 2013

መንፈሱና ሙሽራይቱ


Please read in PDF


ደግ ሰው አልቆ ጉብዝናም ሠሎ
መተማመን ክብርዋ ጎድሎ
ፍቅር ቀዝቅዛ
ጽድቅ አዘቅዝቃ
እውነት ጠንዝቶ
በረከት ጠፍቶ
ስለተፈታ ያ አንድነቱ
ና ትልሃለች ሙሽራይቱ።

በአሳዳጆች ጉልበት
በከሳሾች ጩኸት
በሥጋ ደም ምክር
በጅብ እርሻ ፍቅር
ጀርባችን ጎብጦብን
ልባችን ርዶብን
ሰልችቶናልና ተስፋ የፍጥረቱ
ናልን በምሕረት በቶሎ አቤቱ።

የጨለማ ጮራ
ከጉርሻ ጋር ካራ
የማለዳ ድቅድቅ
ፍትፍትና ምርቅ
አፍቅሮ ከሳሽ
ቀድሶ አርካሽ
የማንጨበጥ ሙልጭልጭ ድንጋይ
ሆነናልና ቅዱስ አዶናይ
ና ና ሰብስበን በየፈርጃችን
መንፈሱ እና ሙሽራይቱ ና ና ይሉሃል ና ናፍቆታችን።

ሙሽራይቱ ና! ትልሃለች
በውብ አጊጣ ደጅ እየጠናች
ና ና ይልሃል መንፈስ ቅዱስም
በብዙ ደስታ የተዋቡትን
             የበጉን ልጆች በክብር እንድትሾም።

1 comment: