ስለ “አጥማቂ” ግርማ ወንድሙ፣ በተደጋጋሚ ጠንቋ ይነቱን፣ በመቍጠሪያ ላይ
ባስደገመው ድግምት እንደሚሠራና ሰዎችን ማሳበድ እስከሚያደርስ በሽታ ላይ እንደሚጥል በተደጋጋሚ ጽፈናል፤ አስጠንቅቀናል። ነገር
ግን የዚያኔ አሰምተን ጮኸን ስንናገር እኛን እንደ መና ፍቅና ሐሰተኛ እንጂ ማንም “አሜን” ብሎ ሊቀበለን የወደደ አልነበረም።
ነገር ግን ጉዳቱ በየቤቱና በየአብያተ ክርስቲያናቱ ሲደርስ ግን፣ ከቀዳሚ ተቃዋሚዎች
መካከል አንዱ ራሱ ማኅበረ ቅዱሳን፣ የ“አጥማቂ” ግርማ ወንድሙንና ኢንቨስተሩ አጥማቂ አባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም ስለ ተባሉት በግል
ጠባቂያቸው ስለሚጠበቁት ኹለት ድግም ተኛ አጥማቂያንን ገመና አጋልጦአል። የተሐድሶ ትልቁ ጥያቄና በዚህ ረገድ እናሰማቸው የነበሩ
ሙግቶች ከዚያው መካከል መነሣቱ ደስ ብሎናል። በዚህ ረገድ ከተነሡት ጭብጦች መካከል ጥቂቶቹ፣
·
አጥማቂያኑ ራሳቸውን ብቻ ነው የሚያስተዋውቁትና የሚሰብኩት፤ ጌታን ግን አይደለም፤
·
አጥማቅያኑ አንዳችም የቅድስና ሕይወት የላቸውም፤ ፍጹም ሥጋውያንና ገንዘብ ወዳድ
ናቸው፤
·
አጥማቅያኑ ከሰይጣን ምስክርነትን እየተቀበሉ፣ ባልና ሚስትን ያፋታሉ፤ ጐረቤታሞችን
ያጣላሉ፤
·
የተለያዩ ሰዎች ምስክር እንዲኾኑላቸው ያታልላሉ፣ የታወቁ አርቲስቶችንና የታወቁ
ሰዎችን ከፍለው እንዲሠሩላቸው ይቀጥራሉ፤
·
አጥማቅያኑ አጭበርባሪዎችና አታላዮች፤ ምትሐተኞችና የጥንቁልና ልምምድ ያላቸው
ናቸው፤
·
አጥማቅያኑ በአንደበት ሊነገሩ የማይችሉ እጅግ ብዙ አጸያፊ ነገሮችን ያደርጉ
ነበር፤ … እና ሌሎችንም አስነዋሪ ተግባሮችን ይፈጽሙ ነበር።
በርግጥም አጥማቅያኑ ጠን ቋዮች ስለ መኾናቸውና የአጋንንት ልምምድ ውስጥ ስለ
መኖራቸው አንዳችም ጥርጥር አልነበረንም። ማኅበረ ቅዱሳን ይህን ዘግይቶ ቢኾንም መረዳቱ፣ እጅግ መልካም ነው፤ ነገር ግን ደግመን
እንላለን፣ የሚያድነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስምና ደም ብቻ ነው፤ ከኢየሱስ ስምና ደም በቀር ሌላ የሚያድን አንዳችም ኃይልና
መድኃኒት የለም።
ዛሬም በጨለማ ውስጥ ላሉት የምንለው ይህን ነው፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለውን
መዳንና ሕይወት ይቀበሉ ዘንድ እንማልዳለን። መጽሐፍ እንዲህ እንደሚል፤ “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች
የተሰጠ ስም[ከኢየሱስ በቀር] ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” (የሐ. ሥ. 4፥12)።
“ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር ለሚወዱ ኹሉ
ጸጋ ይኹን፤ አሜን” (ኤፌ. 6፥24)።
No comments:
Post a Comment