Thursday 4 March 2021

አዲሱ የሮዳስ ተረት!

Please read in PDF

መቼም የሐሰት መምህራንን ጠባይ መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር እንዲህ ይላል፣ “ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች፥ እያሳቱና እየሳቱ፥ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ” (2ጢሞ. 3፥13)።  አንድ የስህተት አስተማሪ ፈጥኖ በቅዱስ ፍርሃትና የቅዱሳት መጻሕፍትን ሥልጣን በማክበር በመታዘዝ ካልተመለሰ፣ እየባሰ፣ እየከፋ፣ ኀጢአቱን እየጨመረ፣ አሳሳችነቱን ይበልጥ እየገፋበት ይሄዳል።



ሮዳስ፣ በዲማ ጊዮርጊስ የሚገኝ አንድ የጊዮርጊስ ስእል፣ በየካቲት 23 ቀን ጠዋት ጠፍቶ ማታ እንደ ተገኘና የመቅደሱ ዓቃቢት ስእሉን፣ “ጠዋት አላየኹህም፣ የት ሄደህ ነበር?” ብላ ስትጠይቀው፣ “ቀኑን ሙሉ አጼ ሚኒሊክን ስረዳ ውዬ ነው” ብሎ መለሰላት ይላል።  መቼም ለተረቶቻቸው ወደርና አቻ የላቸውም! ከልባቸው አፍልቀው ሲናገሩ ትንሽ እንኳ አያፍሩም!

ጦርነትንና ሰውን መግደል የሚደግፉ ጭፍን “አማኞችና አገልጋዮችን” እያየን ባለንበት በዚህ ዘመን፣ እነ ሮዳስ ደግሞ እውነት ለማድረግ ተግተው ተረት ሲተርቱ እናያለን። ስተው ከሚያስቱ ተጠንቀቁ፤ በክህደት ዝፍጥ ውስጥ ተዘፍቀው ሌሎችን ለመሳብ ከሚታትሩቱ፣ የመጽሐፍ ቅዱሱን ኢየሱስ ከመጥራት የሚያፍሩ፣ የአሮጊቶችን ተረት ሲተርቱ ግን ከማይሰቀቁ ራቁ፤ ወደ ተወዳጁ መድኀኒትና ቤዛ ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ ፊታችሁን ዘወር ታደርጉ ዘንድ እንማልዳችኋለን፤ ጌታ መንፈስ ቅዱስ የስህተት መምህራንን ልባቸውን በብርቱ ይውቀስ፤ እኛንም በጸጋው ያጎልምስ፤ አሜን። 


11 comments:

  1. GOD bless you for sharing. May the SPIRIT be your guide & strength for days to come.

    ReplyDelete
  2. ስለ እመቤtaችን በፃፍከው መልእክtiሕ ስላንte ማንነt ለማወቅ ጊዜ አልፈጀብኝም ነበር አሑን ደግሞ ለምድ የለበስክ Teኩላ መሖንሕን በደንብ አወኩሕ እንደዚሕ አይነt አካሔድ የtiም አያደርስሕም ወደ ልብሕ Teመለስ ንግግርሕ ማንነtiሕን ይገልጸዋል!!!!!!!!!!☜☜☜

    ReplyDelete
  3. መቼም ዝንብ ትልቅ ትንሽ ሀብታም ወይም ደሃ አትልም ሁሉ ቦታ ትገባ የለ ?? በእውቀት ተበለጥኩ ብሎ ማብኳት አይጠቅምም ለማንኛውም ለዝንብ መልስ መስጠት አስፈላጊ አልነበረም

    ReplyDelete
  4. ጊዮርጊስ ልቦናውን ይስጥህ።

    ReplyDelete
  5. እና ቅዱስ ጊዮርጊስ አልተራዳም እያልከን ነው ። ጰነጰጵክ !!ወይስ አበድክ!አንድም ጴንጤ ስለ ኢትዮጵያ ክብር አሸናፊነት ስለ ሰንደቅ አላማዋ ልዕልና እውነት መናገር አትፈልጉም ። ስለ ኢትዮጵያ እውነተኛ ታሪክ ሲነገርህ እንቅልፍ እንቅልፍ ይልሃል ።ስለ ፈረንጅ እቃ እቃ ተረት ሲሆን አስፓልት ለአስፓልት እያዘለለ ያስለፈልፍሃል ፡አ

    ReplyDelete
  6. ተአምር ማለት ተአምር ነው ማለት ነው እንጂ እነዚ ሊቀ መናፍቆች ማለቂያ የሌለው የትውልድ ታሪክ ተራኪዎች ተረት ተረት ማለት አይደለም ይግባችሁ
    እንቢ እውነት አይገባንም አንፈልግም የምትሉ ከሆነ በመምህር ግርማ መቁጠሪያ ጨርባችሁን አስገርፉና ባላችሁበት ተረት ተረት ወሬ ቀጥሉ ፡፡

    ReplyDelete
  7. ውይ አዘንኩልህ በታሪክ የእንጨች ቅርፊት የሰመጠ ብረት አንሳፈፈ ቢባል
    ተረት ተረት ማለትህ አይቀርም

    ReplyDelete
  8. ሼም የላቸውም እኮ

    ReplyDelete
  9. ኧረ አስተውሉ መጋቢ ዶ/ር ሮዳስ የመናገር አቅሙ የላችሁም

    ReplyDelete
  10. ወፍ ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ አለ
    ኧረ ዝምምምም በል እባክህ አንት ይንን እንቁ ሙህር ለመተቸት አቅሙ አለህ ግን
    ትል እራስ

    ReplyDelete
  11. አንተ በመጄመሪያ የሞትክ ነህ ሲቀጥል መምህራችንን ለመናገር ስልጣን የለህም ምክንያቱም አንተ ክሃዲ ጴጢ ነህ እግዚአብሔርም ዘዳግም 18 ፡20 እንዴተናገረው ነው በመጨረሻ ግን ማቲ.16:27 ትቀበላለህ እግዚአብሔር ልብህን ይመልስልህ እኛ ኦርቶዶክሶች የጠነገርን ነን በማንም ልክስክስ ንፍጥ አስተሳሰብ ሃይማኖታችንን አንክድም ምክንያቱም እግዚአብሔር አምላክ የፊተኛ እምነታችሁን እንዳትሽሩ በፍቅር ተከተሉ ባትከተሉ ግን በገንዘብ ብትሸጧትም እናንተ የዳቢሎስና የይሁዳ ተባባሪ ናችሁ ።

    ReplyDelete