Wednesday 24 March 2021

ቁርጡን ልንገራችሁ!

Please read in PDF

ኹለት ልብ የለኝም

ኹለት ኑሮ አላውቅም

ኹለት ቤት የለኝም

ማመንታት አላውቅም፤

አንድ ነው ኑሮዬ ልቤን የጣልኩበት

አንድ ነው ሕይወቴ ሞቼ ‘ምኖርለት፣

ነፍሴ አቅሏን ስታ የፈዘዘችበት

ልቤ ተርበድብዶ የተሸነፈለት

አንድ እርሱ ብቻ ነው የማምለጫ ዐለቴ

የማልደብልበት ዋናና ንጉሤ

ኢየሱስ ብቻ ነው ኑሮና ሕይወቴ!    

2 comments: