Friday 8 November 2019

አቤንኤዘር

Please read in PDF

አቤንኤዘር አቤንኤዘር መዝሙራችን
ድል አይተናል ተዋግቶልን ረዳታችን
ቅኔ አምጡ ተንጓደዱ በምስጋና
ከሳሽ ወድቋል ጌታ ቀኙን ልኳልና


ረዳታችን ሰማይና ምድርን ሠሪ
ክፉ ሌʻትን ሞገድንም አሻጋሪ
ምን ጎደለን ከʻርሱ ጋራ ወጥተን ገብተን
አቤንኤዘር ላከበረን ለወደደን

መዝሙር ቅኔ በገናችን አቤንኤዘር
ወድቋልና የአስጨናቂው ጽኑ ቀንበር
ይገባሃል ተቀበለን የእኛ ጌታ
አምልጠናል ከወጥመዱ ባʻንተ እርዳታ

አንፈራም ቀስተኛውን ሠባሪያችን ካለህልን
በስምህ ኃይል እንወጣለን ተመክተን
ሰልፍ ያʻንተ ነው ጎመድና ጭሬ የለም
ድልን አይተን አቤንኤዘር እንላለን ዝም አንልም፡፡

ጥር 2009 ዓ.ም ተጻፈ፡፡

No comments:

Post a Comment