Monday, 10 June 2019

ይድረስ ለውድ እህቴ ዘርፌ ከበደ … !

ይህ ጽሑፍ ዘማሪት ዘርፌ ወደ ስሑት መምህራን ጐራ ባለችበት ወቅት የተጻፈ ነበር፤ ነገር ግን ጽሑፉን ከተመለከቱ ወንድሞች መካከል ጥቂቶች አስተያየቶችን ስለ ሰጡኝ ለጊዜው ከማውጣት አዘግይቼዋለሁ፤ ዘርፌ ግን አኹንም ከፊተኛ ስህተትዋ የሚብስ፣ እንኳን ለመንፈሳዊነት ለአመክንዮ የማይመጥን “ከኦርቶዶክስ የለቀቅሁበት ምክንያቴ” የሚል ርእስ ሊሰጠው የሚችል ምስለ ወድምጽ(Video) ሠርታ ለቅቃለች።

አንዳንድ አገልጋዮች የራሳቸውን አገልግሎት ትክክል ለማድረግ ሲሉ ብቻ፣ አእላፋት በኹለንተናቸው ዋጋ ከፍለው የሚያገለግሉትን ደገኛ አገልግሎት፣ ጥላሸት ለመቀባት ሲዳዱ ማየት እየተለመደ መጥቷል፤ አለመታደል! እንዲህ ከማድረግ ልከኛ የአገልጋይ ጠባይ ይዘን ብናገለግል እጅግ መልካም ነበር፤ ከአገልግሎት በፊት አገልጋይ መኾን ይቀድማልና፤ ሽብርቅና ድምቅ ያሉ አገልግሎቶች ኹሉ አገልግሎት እንዳይደሉ፣ ሰው እንጂ ክርስቶስ እንዳይከብርበት በአጭር ዕድሜዬ አይቻለሁ።
እናም ምንም ሳይለወጥ ጽሑፉን ማውጣት አስፈላጊ መስሎ ስለ ታየኝ ጽሑፉን እንዳለ እንዲህ አውጥቼዋለሁ፤ መልካም ምንባብ …

አንድ የምዕራብ ቤተክርስቲያን አስደናቂና እጅግ አስተማሪ አባባል አለ፤ “በምድር ላይ ፍጽምት ቤተ ክርስቲያን የለችም፣ ብትገኝ እንኳ አንተ የተቀላቀልካት ቀን ፍጽምናዋን ታጣለች” ይላል። እውነት ነው፣ ቤተ ክርስቲያን ሙሉ ለሙሉ ባልተዋጀው ዓለም ስለምትኖር፣ በብዙ ድካም ውስጥ ልታልፍ ትችላለች፤ ምንም እንኳ መያዣው መንፈስ ቅዱስን የተቀበለች ቢኾንም፣ በብዙ ሕማምና ድካም ውስጥ ታልፍ ዘንድ አላት፤ “እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ” ከፊት መጨማደድ ጸድታ ትኖር ዘንድ የምትኖርበት ጊዜ ግን ወደ ፊት እንዲመጣ ፍጹም እናምናለን፤ (ኤፌ. 5፥27)።
ክርስቶስ ኢየሱስን በምታምነው በየትኛዋም ቤተክርስቲያን ውስጥ መንፈስ ቅዱስ እስከ ክርስቶስ ኹለተኛ መምጣት ድረስ፣ ቤተ ክርስቲያንን ይኩላል፣ ያስጌጣልም፣ ያስውባልም። ሸክላ ሠሪው ጌታ እግዚአብሔር (ኢሳ. 18፥6) ሸክላውን [የሰውን ልጅ - በተለይም በክርስቶስ የዳኑትን] ሳይታክት ይሠራቸዋል፤ መንፈስ ቅዱስም ባለመታከት በክርስቶስ መካከለኛነት፣ አዳኝነት፣ ፍጹም ሰውና አምላክነት የምታምነዋን የትኛዋንም ቤተ ክርስቲያን ሳይመረር፣ ሳይታክት፣ ሳይታዘብ ይሠራል፤ ያንጻል፤ ይንከባከባል።
ውድ “እህቴ”! የነበርሽበትን አገልግሎት ተጽዕኖው ምን ያህል ጠንካራና “አይሻሬ” እንደ ነበር ከማንም ፊት የተሠወረ አይደለም። ዛሬም እንኳ የአገልግሎትሽ አሻራው በትክክል ይታያል። በእርግጥ “መዝሙርሽንም” ከሚያደምጡት አንዱ ነኝ!  ምንም እንኳ ወደ አገልግሎት የገባሽው “በፍጥነት” ቢኾንም፣ በሂደት ግን ለመስማትና ለመማር የነበረሽን ቀናነት ሳስተውል በወንጌል ዝማሬ አገልግሎት ረጅም መንገድ ብትሄጂ ብዬ እጅግ ተመኝቼልሻለሁ። አብረውሽ የነበሩት “አገልጋዮች” ከወንጌል ፈቀቅ ብለው “ሲበታተኑ”፣ አንቺም በመጨረሻው መዝሙር ምረቃሽ ዕለት፣ “የእምነት እንቅስቃሴ” አባላት ከኾኑት ሰዎች ጋር በዐውደ ምሕረት ስትገለጪ ፊት ለፊት ከተቃወሙሽ አንዱ ነበርኩ፤ መኾን አልነበረበትም ብዬ!!!
ቅዱስ ቃሉ በአደባባይ የሳቱትን በአደባባይ መውቀስ እንደሚገባ ያስተምረናል፤ አንድ ምሳሌ ብቻ ብናነሣ፣ ቅዱስ ጳውሎስ፣ ቆሮንቶሳዊው ዘማዊና ኬፋ በአደባባይ በተሳሳቱ ጊዜ በአደባባይ ፊት ለፊት ወቅሶአቸዋል፤ (1ቆሮ. 5፥1-5፤ ገላ. 2፥14)። ቅዱስ ጳውሎስ ቅዱስ ጴጥሮስን መቃወሙ ከጥላቻ የፈለቀ ወይም የበላይነቱን ሊያሳይ ያደረገው ተግባር አይደለም፤ የእውነተኛ ወንድምነት ትክክለኛ መገለጫ ነው፤ ተቃውሞውም ኹሉም ሰው ባለበትና ፊት ለፊት መኾኑ በሥራው አፍሮ ንስሐ ይገባ ዘንድ ለማድረግ ብቻ እንጂ አንዳች ኢ መንፈሳዊ ነገር ያለበት አይደለም። እናም እኔም ይህን የምናገርሽና የምጽፍልሽ በወንድማዊና በምክር ቃል በትህትና ዘንበል ብዬ ነው።
ውድ “እህቴ” ዘርፌ፣ በእርግጥ ዛሬ የሄድሽበት የአገልግሎት መስመር ለጊዜው የተደላደለ፣ ኹሉም ነገር ሰላም፣ ኹሉም ነገር ምቹ ሊመስልሽ ይችላል። ዛሬ ፊታቸውን “አብርተው”፣ እጃቸውን “ዘርግተው”፣ ልባቸውን “ከፍተው” የተቀበሉሽ አብዛኛዎቹ የሐሰት መምህራን፤ የክርስቶስ ኢየሱስ ወንጌል ተቃዋሚዎች ናቸው። ዛሬም ስትዘምሪ “ቀናነትሽ በውስጥሽ” አለ፤ የምታደርጊውን በክፋት ልብ እያደረግሽ “እንዳልኾነ” አስተውላለሁ፤ ግና “በራስሽ እንዳልቆምሽ፣ የብዙ ሰው ሃሳብና ድምጽ “ከኋላሽ እየገፋሽ እንዳለ” ጮኸው የሚሰሙ ድምጾች አሉ። እኒህን ድምጾች እንድትረቺ፣ ከጌታ ኢየሱስ ጋር የብቻ ጊዜ ኖሮሽ እንድታሰላስዪ፣ እንድታጉተመትሚ እመክርሻለሁ።
የሐሰት መምህራን አንቺን እንደ ማስታወቂያ “እንደሚጠቀሙብሽ”፣ ከተጠቀሙብሽ በኋላ አሽቅንጥረው እንደሚጥሉሽ አንድ እውነት ልንገርሽ [ከዓመታት በፊት እንዲሁ የሐሠት መምህራን በአዲስ አበባ በባሕል ኢግዚብሺን ያስጨፈሯቸውን መነኮሳት፣ በፍጻሜ እንዴት እንደ ተጫወቱባቸው ካስታወስሽና ጠይቀሽ ከተማርሽባቸው በቂ ምስክሮች ናቸው]።
ሌላው ደግሞ፣ ከአንድ የአገልግሎት ዘርፍ ተገለጠልኝ ወደምትይበት ወደ ሌላ የአገልግሎት በር ለመግባት መጣደፍ የጤና አይደለም፤ አለመስከን፣ የማሰላሰያ ጊዜ አለመኖር … እንዴት አንዲህ ጥዩፍና የተናቀ ነገር ይኾናል? ከፈርዖን ቤት ወደ ቤተ እስራኤል ለመሔድ እግዚአብሔር ሙሴን “ለማሰልጠን” ስንት ዓመት የፈጀበት ይመስልሻል? መጽሐፍ ቅዱስ አርባ ዓመት በምድረ በዳ ለስልጠና እንደ ተቀመጠ ይነግረናል፤ (ሐዋ. 7፥23፤ 30)፣ ዳዊትም ንግሥና ከተቀባ በኋላ ወደ እረኝነት ተመልሶ በታማኝነት ታዝዟል፤ (1ሳሙ. 16፥14-22)፤ “እግዚአብሔር እረኛዬ ነው” ሲል የዘመረው፣ በሕይወቱ ያየውን የእረኝነት ዝማሬ ነው፤ ቅዱስ ጳውሎስ ራእዩን ካየ በኋላ ሦስት ዓመታት ያህል በዓረብ አገር ቆየ (ገላ. 1፥17)፣ ተወዳጁና ድንቁ ኢየሱስ እኛንና አባቱን ሦስት ዓመት ለማገልገል ሰላሳ ዓመት፣ የጌታ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ከጌታ ጋር ስንት ዓመት እንደ ተማሩ አንብበሽ ይኾን? 
ሳይታጠቁ መሮጥ፣ የራስን መንገድ ሽምጥ ለመጋለብ ሲጣደፉ ያለፉበትን መንገድ ሁሉ ጥላሸት መቀባትና ማንጓጠጥ፣ ባልንጀርነትን ሞቶ፣ ተቀብሮ፣ በስብሶ፣ ተልቶ የጠፋ ያህል ሽምጥጥ አድርጐ መካድ፣ በኹሉ መድረክ ኢየሱስን በትምህርታቸውና በኑሮአቸው ከሚያዋርዱ ጋር በአምልኮ አንድ መኾን፣ የሙሽሪት ቤተ ክርስቲያንን አካል ከጋለሞታ ጋር ለማጋባት ብርቱ ጥረት ማድረግ፣ ጨለማና ብርሃንን ለማፋቀር፣ የኢየሱስን ቅዱስ ወንጌልና በኢየሱስ ስም የሚነገረውን ወንጌል ለማስታረቅ በግድ መታገል … የዚህ ዘመን ኹነኛ መልክ ኾኖአል።

አገልግሎት በልጦ ሕይወትና የወንጌል ትምህርት ተንቋል። የትም ከማንም ጋር ማምለክም “በድኛለሁና ነጻ ወጥቻለሁ” ፈሊጥ፣ “ከአጋንንት ማኅበር” ጋር እስከ መሻረክ ብዙዎችን አድርሷል። በርግጥ “ገድል ወይስ ገደል” የሚለውን መጽሐፍ “እንደ ጻፈው” ጌታቸው ፍጹም ጨላጠና ብልጣ ብልጥ ኾነሽ፣ ወደ ሌላ አዘቅትና ገደል ራስሽን ለመጣል የተንደረደርሽ አይደለሽም! ግን የመከሩሽ ሰዎች መልካሙን ነገር አልመከሩሽም፤ እንዲህ ያለ ምክር ልትጠየፊ ሲገባ መቀበልሽ መታለልሽን ያሳያል። ስለዚህም ወደ ጌታ ወንጌል ዘወር ትዪና ከብልጽግና ወንጌል ስሑት መምህራን ትለዪ ዘንድ ይህን ጻፍኩልሽ፤ መንፈስ ቅዱስ በጸጋው ይደግፍሽ፤ በነገር ኹሉ ማስተዋልንም ይስጥሽ፤ አሜን።

18 comments:

  1. መካሪ አያሣጣን ተባረክ ምክርህን ትቀበላለች ብዬ አሥባለው አቤኒ

    ReplyDelete
  2. ስለ ወንድማዊ ምክርህ እግዚአብሔር ይባርክህ።

    ReplyDelete
  3. ewnet new ehtachin yekonferens mastawkiya argatal geta mastawal yadlen

    ReplyDelete
  4. ጌታቸው እውነተኛ ወንጌላዊ ነው ስለሱ መጥፎ ነገር ማውራት አችልም ገደል ወይስ ገድል ብሎ የፃፈው መፅሐፍ በጣም ትክክለኛ ነው። አሁን የሰውን ስተት 1,2, እያልክ ከምቆጥር በራስህን ቤት ያሉትን ገድል (ተረቶች) ከወንጌል ጋር ስለሚጋጩ ሰብስባቹ አቃጥሏቸው

    ReplyDelete
  5. እኔ ሁልጊዜም እህቴ ዘርፌን እደግፋት አበረታታት ነበር ማለቴ በአካል ሳይሆን በሚዲያ መናገር እንኳን የማልችለው እጅግ ጥልቅ ፍቅር አለኝ አሁንም እንኳን ምንም ብትሆንም ምን እጅግ እወዳታለሁ ምክንያቱም ዘርፌ የማይደፈሩ ብዙ መዝሙራትን ደፍራለች ለኢየሱስ ቀናይ እና ፍቅር ያላት ሴት ናት አሁን ግን እንደሚመስለኝ የዋህነቷን አይተው ሊናጠቋትና በእሷ ስም ትልቅና ድብቅ አላማቸውን ለማሳካት እንደሚራኮቱባት ይሰማኛል
    በትልልቆች ውድቀት ብዙዎች ወደ ኃላ ያፈገፍጋሉ ለወንጌል የተጋደሉቱ ክብርና ዝና መፈለግ ሲጀምሩም ቤተክርስቲያን መልኳ ይደበዝዛል ግን የቤተክርስቲያን ባለቤት ሁሉንም ይለያል የዛን ጊዜ ይጠራል
    ሁልጊዜ እጅግ ያሳስበኛል ለምን ከፊት የነበሩ ሁሉ ወደኃላ ሆኑ ብዙዎች የተሻሉ ነበሩ
    እግዚአብሔር ግን ሁሌም አዲስ ነው ተጋድሏቸውን ይረሳ ዘንድ ሰው ስላልሆነ አሁንም በፀጋው ደግፎ ወደ እውነት ሁሉ እንዲመራቸው የዘወትር ፀሎቴ ምኞቴም ነው ።

    ReplyDelete
  6. አጅግ ሲበዛ ደደብ ናችሁ፡፡ ደግሞ ስለ ኢየሱስ ዳግም ምጽአት ስትጽፉ አታፍሩም፡፡ ከ2000 አመት በላይ ጠበቃችሁት፤ ትንሽ አይሰለቻችሁም፡፡ አብርሀማዊ እምነቶች ሁሉ ከኢትዮጵያ ምድር ተወግደው ህዝቡ ከተፈጥሮ ስርአት ጋር ታርቆ በስነስርአት የሚኖርባት ሀገር መፍጠር ሲገባ ክርስትና የመሰለ ቆሻሻ፤ ያውም ኦርቶዶክስ፣ እንዲጸና መታገል ከልክ በላይ ደደብነት ነው፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. Ante weym anchi dedeb ahya borko
      Zara sele menorachu ortodox new
      Hiwotachu dengay chnkelat yezachu
      Ke sew ekule menorachu gematamochuma
      Enanete nachu tubo rase afer batekalay
      Egna nen yatedanachu

      Delete
  7. What? What is that mean Abrhamawi Emnetoch? I never heard before? can you explain? what did you mean?

    ReplyDelete
  8. U said it wrong who are u to judge?

    ReplyDelete
  9. የፈለክሽበት ድረሺ ነገር ግን ሰለኦርቶዶክስ ማስተማር አትቺይም ስለ አዬ ጩፋ ብታወሪ ይሻላል

    ReplyDelete
  10. እባካችሁ እስቲ እርሷት ሁላችንም ትግስት ይስጠን አስመሳዮች እንደሁ በየቦታው ሞልተዋል ምንም ቢዘባርቁ ክርስትና ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች

    ReplyDelete
  11. Do you know why I like the Orthodox church? I have Three reasons: 1) I started learning Amharic Alphabet at church. At that time, they cared about me, but the church didn't try to take over my mind like some other the so_called churches. I was young. I didn't know better. They could, but didn't. I am grateful for that. 2) At the time of difficulty that Ethiopian freedom was endanger, Ethiopian people were fighting everywhere to secure their freedom from the invader Italian forces. The Orthodox church was with soldiers to give them blessings and prayers by carrying the Tselat. Any religious organization that had contributed for freedom of Ethiopia in that tough time is appreciated forever. I value that very much. 3) Orthodox church has become my culture or my identity. I grownup going church with my parents since I was little, so I have developed affection and respect. I am one.

    ReplyDelete
  12. ጠይቆ ለመረዳት ፈጣሪ ልቦናሽን ይክፈትልሽ እላለሁ የኚህን መልካም አባት ምክር መጠቀሙ ፍሬ ያስገኝልሻልና።

    ReplyDelete
  13. "ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።"

    👉1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2:19

    ReplyDelete
  14. እቺኛዋ የዘርፌ አዲስ የገንዘብ ማሠባሠቢያ ዘዴ ነች

    ReplyDelete
  15. አቤቱ የድፍረት ሀጢያት እንዳይገዛኝ እኔ ባርያህን ጠብቃኝ

    ReplyDelete