Saturday 8 December 2018

አባይነህ ካሴ ጠቡ ከኢየሱስ እንጂ ከአቡኑ አይደለም!

Please read in PDF

  “ … በግድ በብዙ ስም የሚጠራውን ልዑለ ባሕርይ ጌታ በአንዱ ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ ኢየሱስ ብቻ ብላችሁ ካልጠራችሁ ብሎ ሙግት ሌላ የተሰወረ ዓላማን ከሚያሳብቅ በቀር ሌላ ትርፍ የለውም። ወይ እኛ ኢየሱስ ማለት ትክክል አይደለም አላልን፤ ይህ ባልተካደበት ሁኔታ ከስሞች መርጦ ለአንዱ ያጋደለ ስሜት እንዲፈጠር ለማድረግ መሞከር አደገኛነትን ያሳያል። …”[1]

   በቀን 27/3/2011 በቦሌ መድኀኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ብጹዕ አቡነ በርናባስ የሰበኩትን ስብከት ከዩቲዩብ አውርጄ አደመጥኹት፤ ከዚያም በዚህ ስብከት ላይ ጥላቻውን ጮኾ በሚያሰማ መንገድ [ለኑፋቄ ግብር የገቡ ልማደኛ … ሐራጥቃዊመምህር ሰውዬው … እያለ “አዋርዶ” በመጥራት] አባይነህ ካሴ የተባለ የማኅበረ ቅዱሳን ቀኝ እጅ የኾነ ሰው፣ ስብከታቸውን በመተቸት የጻፈውንም አነበብኹ፤ እናም “ጉዳዩ ኢየሱስ ኾነና” አንድ ነገር እናገር ዘንድ ተገደድሁ።



አቡነ በርናባስ ስብከት
   አቡነ በርናባስ አኹንም መንፈሳዊ ድፍረታቸው፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ላይ ያላቸው የማያወላውል አቋማቸው አብሮአቸው አለ፤ በጸጋ ያስተምራሉ፤ ይመሰክራሉ፤ ወንጌሉን ይናኛሉ፤ ወንጌልን ሲመሰክሩ ቅንጣት ታህል በውስጣቸው ፍርሃት የለም፤ ጸጋ ይብዛልዎት ልል ወደድኹ፤ [በትውፊቱ ዲያቆን ጳጳስን እንዲል ባይደገፍም!]። በአገራችን ካሉት ጳጳሳት ኹሉ ክርስቶስን በመስበክ የሚተካከላቸው ያለም አይመስልም። እስካሁንም አልገጠመኝምና! በዚህ ነፍሴ አብዝታ ትባርካቸዋለች፤ ደስም ትሰኝባቸዋለች፤ እንዲህ ያሉ ጳጳሳትና አማንያን እንዲበዙ የዕድሜ ዘመን ምልጃዬና ጥማቴም ነው! አባታችን መንፈስ ቅዱስ ይርዳዎት፤ ክንድዎትንም ያበርታልዎ! አሜን።
አባይነህ ካሴ “ነቀፋ”
   አባይነህ ካሴ “ነቀፋውን” የመሠረተው፣ ስምን ከሥላሴ ባሕርይ ጋር በማዛመድ ክርስቶስና አማኑኤል የተባሉት ስሞች ከትስጉቱ በፊት መጠሪያው እንደ ኾኑ በመሞገት ነው። ጳጳሱን ለመንቀፍ ለምን የሥላሴ ስምንና ባሕርይን ማገናዘብ እንደ ፈለገ ግልጥ አይደለም፤ በእርግጥ ዋና ዓላማው ጳጳሱን ማዋረድና ማንኳሰስ እስከ ኾነ ድረስ፣ የትኛውንም መንገድ ከመከተል ይመለሳል ብዬ አላምንም፤ እንዲህ ማድረግ የማኅበረ ቅዱሳን አመራር ዋና መገለጫ ነውና። አባይነህ ደግሞ የማኅበሩ ዋና ሎሌ ነው።

   ጳጳሱ ያስተማሩበትን ዓውድ ጥሷል፣ ጳጳሱ ያተኰሩት ስመ ትስጉቱ ላይ ነው፤ በትክክልም የክርስቶስ ስመ ትስብእቱ ኢየሱስ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ፦ “ … ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ።” (ሉቃ. 2፥21፤ ማቴ. 1፥25) ይላል። ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን ሲጠሩት ወይም ለሌሎች ሲናገሩት፣ “ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል” (ዮሐ. 1፥46) በማለት ነው፣ ኢየሱስን ከሌሎች ለመለየትም የናዝሬቱ ተብሏል።
   ድንግል ማርያምም የተጠራችው “የኢየሱስ እናት” (ዮሐ. 2፥1፤ 19፥26፤ ሐዋ. 1፥14) ተብላ ነው፤ አይሁድ ኢየሱስን በክርስቶስነቱ አያውቁትም፣ ለዚህም ነው ሐዋርያት የስብከታቸው ዋና ርዕስ፦ “ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው” የሚል ነው፤ “ዕለት ዕለትም በመቅደስና በቤታቸው ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አይተዉም ነበር” (ሐዋ. 5፥42)፣ “ሲተረጉምም ክርስቶስ መከራ እንዲቀበልና ከሙታን እንዲነሣ ይገባው ዘንድ እያስረዳ፦ ይህ እኔ የምሰብክላችሁ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው ይል ነበር” (ሐዋ. 17፥3)፣ “ጳውሎስ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለአይሁድ እየመሰከረ ለቃሉ ይተጋ ነበር።” (ሐዋ. 18፥5)፣ “ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ከመጻሕፍት እየገለጠ ለአይሁድ በሁሉ ፊት በጽኑ ያስረዳቸው ነበርና።” (ሐዋ. 18፥28) … የሚል የኾነው። እኒህና እጅግ አያሌ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ኢየሱስ [በትስጉት የተገለጠው ጌታ] እርሱ ክርስቶስ እንደ ኾነ ደቀ መዛሙርቱ ገልጠው መናገራቸውን ያሳየናል።
   ኢየሱስ ስመ ትስብእቱ ብቻ መኾኑን አይሁድ ያውቁ ነበር፣ ይጠብቁት የነበረው መሲህ እርሱ በስመ ትስብእቱ የሚያውቁት ኢየሱስ እንደ ኾነ ገልጠው ደቀ መዛሙርቱ መስክረዋል፤ እኛም ያመንንበትና የዳንንበት እውነት ይህ ብቻ ነው፤ “ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።” (ዮሐ. 20፥31) የሚል። እንኪያስ ጳጳሱና እኛ ስመ ትስጉቱ ኢየሱስ የተባለውን፣ መሲህ ክርስቶስ እንሰብካለን እንጂ ሌላ ምን ርዕስ ሊኖረን? ጳጳሱ ስመ ትስጉቱ ኢየሱስ ነው ቢሉ፣ ዳሩ ግን ስመ ትስጉቱ ኢየሱስ የተባለው እርሱ ክርስቶስ እንደ ኾነ፣ ሞትና ኀጢአት ድል እንደ ተነሡበት ቢናገሩ ስህተቱ ምኑ ላይ ነው?! አባይነህ ሆይ! ይልቅ የሚመርረውን መርዶ ድጋሚ ስማው! በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በድፍረት ከማይጠሩ ስሞች አንዱ እኮ ኢየሱስ የሚለው ስም እንደኾነ የጠራራ እውነት፣ አንተም በልብህ የምታውቀው ነው! ኢየሱስ የሚለውን ስም ደጋግመው ስለጠሩ ብቻ “ተሐድሶ፣ ኦርቶጴንጤ፣ ሐራጥቃ፣ መናፍቅ … እየተባሉ የተባረሩ፣ የተሰደዱትን የሚያውቅ ከእናንተ በላይ ምስክር ማን አለ? ይህን ሁሉ ስም እንደ ታርጋ ለጥፋችሁ እንኳ መች ረካችሁ? ኢየሱስን ኢየሱስ ብላችሁ ላለመጥራት ዛሬም ሌላ የክስና የስድብ ስም ፍለጋ ትንከራተታላችሁ እንጂ።
   እናም የኢየሱስን መካከለኝነትና ብቻውን አዳኝነት ለሚክዱ ለአባይነህና ተከታዮቹ እንዲህ ያለ ትምህርት ተሰውሮባቸዋል፣ ተጋርዶባቸዋል፣ ረቆባቸዋል፣ መጥቆባቸዋል እንጂ አልተገለጠላቸውም። በውኑ ኢየሱስ የሚለው ስምና የስሙ ኃይል ከገባንና አሰምተን ከጠራነው፣ በመጥራታችን “ምን የተሰወረ ዓላማ፣ ምን አደገኛ ነገርስ ይኖረን ይኾን?”፤ ሞት ለተሳለቀብን፣ ሰይጣን ለዘበተብን፣ ኀጢአት ድሩን ላደራብን፣ መርገም በክንዱ ላደቀቀን … አለኝታና መከታ፣ ጋሻና ከለላ፣ ሕይወትና ሞገስ፣ ተድላና ዕረፍት የኾነን ስም ኢየሱስ፣ ኢየሱስ፣ ኢየሱስ፣ ኢየሱስ፣ ኢየሱስ፣ ኢየሱስ፣ ኢየሱስ … ብቻ ነው!
  የካሴ ልጅ ሆይ! ኢየሱስ ማለት አይታፈርበትም፣ አላፈረብንምና፤ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ኾነ መናገርም ሴራ የለበትም ሕያው ዘላለማዊ እውነት ነውና፤ ወንድሜ ኢየሱስን ደስ እያለህ ደጋግመህ እንድትጠራው መንፈስ ቅዱስ ልብህን ያቅናልህ፣ ይመልስልህም … ምናልባት ይህን የኮብት ቤተ ክርስቲያን ኢየሱስን ደጋግመው ሲጠሩ ብትሠማ ልብህ ይቃናልህ ይኾንን? እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሆይ! አባይነህ ኢየሱስን ኢየሱስ ብሎ በልጅነት መንፈስ መጥራት ይቻለው ዘንድ እርዳው፤ አሜን።



ባታችን ቢያስተካክሉት ብዬ በልጅነት የምናገረው
 ጳጳሱ በስብከታቸው በጥቂቱም ቢኾን ከፖለቲካው ተጽዕኖ የወጡ አይመስሉም፤ በእርግጥ በምዕራቡ ዓለም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ተተግኖ፣ “ሠላሳ ደቂቃ መንፈሳዊ መርሃ ግብር አካሂዶ” ሦስት ሰዓት ለፖለቲካ ስብሰባ በሚሰበሰብ የዲያስፖራ ማኅበረ ሰብ ውስጥ፣ ወንጌልን ያለ ተጽዕኖ መስበክ እጅግ አዳጋች እንደኾነ ባውቅም፣ አሁንም ከዚያ ባለ መራቃቸው ነፍሴ አትወደውም! ከዚህ ባሻገር እንደ ማቴ. 5፥17 ያለውን የአተረጓጎም ስልታቸው ከወንጌል ያፈነገጠ ነው። “እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም።” የሚለው ቅዱስ ቃል ሕጉን ላጠብቅ፣ ላጸና … መጣሁ የሚል ትርጉም የለውም፤ የሰው ልጅ ሕጉን ከኀጢአት የተነሣ ይፈጽመው ዘንድ አልቻለም፣ ክርስቶስ ኢየሱስ ሰውን ተገብቶ ሊፈጽም፣ ሊተገብር፣ ሊያደርግ … መምጣቱን አመልካች ነውና፤ “የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና” (ሮሜ 10፥4)፣ እንዲል። አባታችን ጸጋ ይብዛልዎት፣ አባይነህ መንፈስ ቅዱስ ክርስቶስን በትክክል እንድታውቀው ይርዳህ፤ አሜን።




[1] ከአባይነህ ካሴ የፊት ገጽ የተወሰደ፣ https://www.facebook.com/abayneh.kassie.5/posts/1913324775453657

11 comments:

  1. አይ ጼንጤ ክክክክክክክክክክክክክ አትነግሩንም አዲስ ጌታ የልምምምምም

    ReplyDelete
  2. ይች ናት ጭዋታ!ስለ ኢየሱስ ልትሰብኩን? ጌታችንና አምላካችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አይደል የምንለው:: በውኑ ኢየሱስ የሚለው የስጋው ብቻ መጠሪያ ነውን?

    ReplyDelete
  3. 1000,ጊዜ ትክክል ነው ። !!!

    ReplyDelete
  4. ኢየሱስ በእርግጫ ፈውሱ ብሎ አስተምሯል እንዴ??

    የት ቦታ

    ኢየሱሰ አይን ጨፍናችሁ ተደናበሩ ብሎ አስተምሯል እንዴ???

    የት ቦታ

    እጉርን እጉር ሊመራው አይችልም ይላል የጌታ ቃል

    ታድያ ከየት ያመጣችሁት ነው
    የያዛችሁት ምግብ ፀለይን ብላችሁ
    በሰውነታችሁ እሰኪደፍ ድረሰ አይን ጨፍናችሁ የሚፀልዩ
    የሰይጣን ተገዥወች
    እናንተ

    ጌታ ያአለም ብርሀን ነውውውውውው

    ReplyDelete
  5. በኢየሱስ ሰም አትነግዱ

    ReplyDelete
  6. ኢየሱሰ ያሰተማረን እሱን እድንመሰል ነው
    አይደል ሁሉን አሰረግጦበት
    አስምሮበት ሄዷል
    ክብር ምሰጋና ለሰመአጠራሩ ይሁን አሜን አሜን አሜን ♥♥♥

    ReplyDelete
  7. ከእኛ ዘንድ ወጡ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም ከእኛ ወገንሰ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ፀንተው በኖሩ ነበር

    1ዮሐ 2÷19

    ReplyDelete
  8. ከላይ ኢሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ ከገለፅህ ብሁዋላ መጨረሻ ላይ ለምን ነጥለህ ኢየሱስ ኢየሱስ አልክ? ደግሞ ኢየሱስ ኢየሱስ በማለት ብቻ መዳን የለም! "ጌታሆይ ጌታሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግስተሰማያትን አይወርስም"ብሏል!ለኦር

    ReplyDelete
  9. ወግቼሀለው በጌታ ስም ሄሎ ሊያ ማታ ስላትተ ነገረኝ

    ReplyDelete
  10. www.cmasnakugbyhu

    ReplyDelete
  11. weyi ant sijemer semek tesefay nw abenzer mn aderegew ahun ateferagexi zmmm Belk yemetamelkwen sehitetik amelk defar nk aqalew demo atebel betaweqema zmmm enji afek erat ayetefam nbr demo birr yelatim atesexim kkkkkkkkkk

    ReplyDelete