Tuesday 25 December 2018

ለቀን አምላኪዎች!

መጽሐፉ ታጠፈ ተከድኖ ወየበ
የአሮጊቶች ተረት ደምቆ ተነበበ
ቀን ሳለ ለትጋት ለሥራ የተሰጠው

“መሥራት” ስላልቻለ ሰውን ቀን በለጠው፡፡
መሰልጠን ሲገባው በወንጌሉ ሥራ
ሰው ግን ወርዶ ቆመ ከቀንነት ተራ፡፡
ከዚህ የተነሣ …
ሸክላ ሠሪው ጌታ በሸክላው ባይታይ

ገኖ ልቆ ታየ የሸክላው አገልጋይ!

1 comment: