ሰርጐ ገቢው ፤
ተመሳስሎ በቀስ አድቢው ፤
የበግ ለምዱን አለስልሶ -
አለሳልሶ
፤
የዝማሬ ድምጸት ገርቶ ፤
የስብከቱን ቃና ለምዶ ፤
የጽሑፉን ዝፍቱን ቀብቶ ፤
በበግ መሐል አንገት ደፍቶ ፤
ተኩላ ክፉ በዚህ ብቻ መቼ ረክቶ?
ጵጵስና ፣ ቅስና ፣
ምርግትናና ድቁና ፤
ከመሪውም እንደአንዱ
መስሎ መኖር ነው ልማዱ!!!
ከበግ መሃል በግ ለመንጠቅ ፤
መሪ መስሎ ለመበጥበጥ ፤
ተኩላው ለምዱን አሳምሯል ፤
የሰባውን በግ ለማረድ - እንደመሪ
ናዞ ያዛል፡፡
እናም …
ከነጣቂ ተኩላ ፣ መራቅን አትዘንጋ ፤
እንዳትርቅ ከእረኛህ ፣ ከበጐቹም መንጋ ፤
ልባም እንደእባብ ፣
የዋሐት እንደርግብ ፣
ገንዝብ አድርግና ፣
ከእረኛህ ጋር ጽና፡፡
No comments:
Post a Comment