Friday 10 June 2016

ባታርግ ኖሮ … (እንኳን አረግህ!)

Please read in PDF


ሞትን ድል ነስተህ
ሲዖልን ረግጠህ
የገሃነምን፥ ደጆች አፍርሰህ
ላመኑህ ልጆች፥ ተስፋውን ሰጥተህ …
ባታርግ ኖሮ …

ባታርግ ኖሮ፥ ወደሰማያት
ማን ይቆም ነበር፥ እንዲህ በሕይወት?
ባታርግ ኖሮ፥ ወደአባትህ ቀኝ
የ‘ኛ አድራሻ፥ ከወዴት ሊገኝ?
ባታርግ ኖሮ፥ በዜማ እልልታ
መች ይሆን ነበር፥ ሕይወት የ‘ኛ ዕጣ?
አዎን!
ቤተ ክርስቲያን፥ ተወልዳ እንድታድግ
ይገባህ ነበር፥ በክብር ማረግ
እንኳን አረግህ፥ እንኳንም ሄድከው
“ስለሄድክ ነው”፥ አጽናኙ ጌታ “ወደእኛ የመጣው”
“ስለሄድክ ነው”፥ የመስቀልህ ሞት -
                ብዙ ነፍሳትን ማርኮ ያስቀረው!!!

No comments:

Post a Comment