የክብረት ልጅ እይታዎቹን በሚያቀርብበት ብሎጉ፥ “ፓትርያርኩ፦ ለኢትዮጲያ
የደኅንነት ፣ ለምእመናን የድኅነት ሥጋት” በሚል አንድ ጽሁፍ፥ ዛሬ አስነብቦ ድንገት ያየ ሰው ጠቆመኝና ወደጡመራው መድረኩ ገብቼ
አነበብኩት፡፡ ዳንኤል በዚህ ጽሁፉ “100% ማኅበረ ቅዱሳን ሊያዘጋጀው ከጫፍ የደረሰውን ዐውደ ርእይ የከለከሉት ፤ ያስከለከሉት
ፓትርያርኩ ናቸው”፥ ብሎ ደምድሞ አስቀምጦታል፡፡ የዐውደ ርእዩ ባለቤት ማኅበረ ቅዱሳን ደግሞ፥ በዋናው ጸሐፊው አቶ ተስፋዬ ቢኾነኝ
በኩል ትላንት ማምሻውን ለጋዜጠኞች በሰጠው ጋዜጣዊ “መግለጫ”፥ “ለመታገዱ ፓትርያርኩ እንደሌሉበትና በመንግሥት አካላት መመሪያ
መታገዱን”ይፋዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
ዳንኤል ፓትርያርኩን ከሰይጣን እኩል ነበር የሳላቸው ፤ “... ፓትርያርክ
ማለት በግሪክ “ታላቅ አባት” ማለት ነው፡፡ የታላቅ አባት ተግባር የልጆቹን ሥራ ማፍረስ አይደለም ፤ ለዚህማ አባት አያስፈልግም
ሰይጣን እንጂ፤ ...” በማለት፡፡ እንደከዚህ ቀደም ልማዱ ዳንኤል ሌሎች ማስጮኺያዎችንም በዚህ ጽሁፍ ለማካተት ጥሯል፡፡ አዳዲስ
ስድቦችንም ለፓትርያርኩ እንደእጅ መንሻ አቅርቦላቸዋል፡፡
ቅዱስ ቃሉ ግን እንዲህ ይላል፥ “ፈራጆችን አትስደብ፥ የሕዝብህንም
አለቃ አትርገመው።” (ዘጸ.22፥28) የሕዝብ አለቃ ወይም መሪ የሆነ ገዥ በምድር ላይ የእግዚአብሔር ተወካይ ፤ እንደራሴም ነው፡፡
ስለዚህ ልናከብረው ፤ በመውደድም ከሁሉ በፊት ልንጸልይለት ይገባል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ሳያስበው ይህን ቃል በመተላለፉ ምክንያት ወዲያው
ተጸጽቶ ተመለሰ ፤ አለማስተዋሉንም ተናገረ፡፡ (ሐዋ.23፥4-5) ፍትሐ ነገሥቱም “በእነርሱ ላይ የተሾመውን ጳጳስ ... እንደትልቅ
ወንድም ያክብሩት መሪና አስተዳዳሪ እንደመሆኑ መጠን ሊታዘዙለት ይገባል” ይላል፡፡ (አን.4 ቁ.53) ዳኒ! ይህ የሕግ ቃል አንተን
አይመለከትም ይሆን?!
የቤተ ክርስቲያን የቀኖና መጽሐፍ ፍትሐ ነገሥት በአንቀጽ.6 ስለቀሳውስት
ድርሻ ባሰፈረበትና ቀሳውስት ከማዕረገ ክህነታቸው ስለሚሻሩበት ሁኔታ ሲዘረዝር “... ሕግን አውቆ የማይሠራባት ... ቄስ ይሻር፡፡”
በማለት በግልጥ ያስቀምጣል፡፡ ዳኒ! እንኳን መንፈሳዊውን ሥጋዊውን የዚህን አለም ምድራዊ ሕግ መጣስህን አውቀኸዋል? ማኅበሩ ፓትርያርኩ
አልከለከሉኝም እያለ፥ አንተ ግን ለፓትርያርኩ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍተሃል፡፡ እንደቤተ ክርስቲያን ቀኖና ከቅስናህ ትሻር ይሆን?
እውነታው ግን አይመስልም፡፡
ፓትርያርኩ ቢያጠፉ እንኳ የቤተ ክርስቲያን ቀኖና ምን ነበር የሚለው?
ጅል ፣ ሰይጣን ፣ የክፋት አነሳሽ ... እያሉ በአደባባይ ፓትርያርክን መዘርጠጥ አለበት የሚል “ቀኖና” አለን?! ለመሆኑ ስድብ
ከማን ነው? የሕዝብን አለቃ አለማክበርስ? ያንን ሁሉ መጽሐፍ የጻፈው “ደራሲና ተመራማሪ” ምነው ምራቅ እንዳልዋጠ “ፍንዳታ”(የቀድሞው
ጠቅላይ ሚኒስቴራችን ቃል ናት) ደርሶ ቱግ አለ?! እንዴ ይህ ነበር እንዴ በውስጡ የነበረው?!
ውድ ወንድሜ ቀሲስ ዳንኤል፦ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና አላት ፤ በየትኛውም
የቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና ሽቅብ ፓትርያርክን እንዲህ መዘርጠጥ አይደለም ምእመንን መናገር አጸያፊ ነው፡፡ ተግሳጽ ነው ብትለኝ፥
ለመሆኑ ተግሳጽ መቼ ነው የሚመጣው? ደርሰህ ከመገሰጽህ በፊት ስንቴ ይሆን የመከርካቸው? ስንቴ ይሆን የወቀስካቸው? ስንቴ ይሆን
ካሉበት ነቀፌታ እንዲርቁ በሚራራ ልብ አዝነህላቸው እንደእግዚአብሔር ቃል በጸሎት ቃል ወደጌታ የማለድክላቸው? ... ደጋፊ ስላገኙ
ብቻ ብዙ ማለት፥ ከማያዳላ ኅሊና ጋር ያፋጥጣል፡፡ ወንድምን ሰባት ጊዜ ሰባ ይቅር ማለትና መቀበል እኮ ከአባት ባሻገር ወንድም
ለሚሆነን ፓትርያርክንም ያካትታል ፤ ለመሆኑ ይህን ታውቀዋለህን?!
ፓትርያርኩ ቢያጠፉ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና አላት፡፡ “...የአገሩ ሁሉ ኤጲስ
ቆጶሳት ስለእርሱ የሚገባውን ይመረምሩ ዘንድ እርሱንም ለማየት በየዓመቱ ሁለት ጊዜ ከጳጳሳቸው (ፓትርያርካቸው) ዘንድ ይሰብሰቡ፡፡
ስለተሰጣቸው ሥልጣን በምታስፈራዪቱ ቀን መልሳቸው የጸናች ትሆን ዘንድ፡፡” (አን.4 ቁ.55) የሚል፡፡ የሚያዩት ፊቱን ብቻ አይደለም
፤ ሥራውን በማየት ያመሰግኑታል ፤ ነቀፌታም ካለ ይነቅፉታል፡፡ ዳኒ! ይህችን አላነበብካት ይሆን?! ፓትርያርኩን መውቀስና መምከር
፤ መገሰጽም ካለብህ መንገዱን አልሳትከው ይሆን? ይህን ያህል ግን ለምን ይሆን የጠላሃቸው? ዳኒ! ወንድምን ስለመጥላት ቃሉ በትክክል
ይወቅስሃል፡፡
በእርግጥ ዳንኤልና ማኅበሩ መንገድ ሲተላለፉ ይህ የመጀመርያው አይደለም፡፡ ግን እውነት ለመናገር ባልተጣራ ወሬ ፤ በተራ አሉባልታ ያውም ስንት ሽልማት
ያግበሰበሰው ሰው ይቺን ትንሿን ነገር ከማጣራት ቸኩሎ “በሚቆረቆርላት” ቤተ ክርስቲያን መሪ ላይ የስድብ ናዳ ያወርዳል ብሎ ማን
ይጠብቃል?! ከዚህ ስህተቱ ይማር ይሆን ዳንኤል? ወይስ ወደፊትም
ሌላ የስድብና የመዘርጠጥ ጽሁፍ ያስነብበን ይሆን? ወይስ እንደጳውሎስ በግልጥ የይቅርታ ልብ ይዞ “የሕዝብን አለቃ” ስለተሳደበበት
ስድቡ ንስሐ ይገባ ይሆን? የምናየው ይሆናል፡፡ ፈጥነህ ንስሐ ብትገባ ግን ማሰናከያን ታስወግዳለህና እስኪ ቀድመህ ወደራስህ እይ!!!
ጌታ ማስተዋሉን
ያብዛልን፡፡ አሜን፡፡
ባለጌ። አንተን ብሎ መካሪ። አንተ ቤተክርስቲያኗን እና መነኮሳቱን ከፍ ዝቅ አድርገህ እዚሁ መናኛ የጴንጤ ዝባዝንኬህን የምትለቀልቅበት ላይ ስትፅፍ አይደል እንዴ የምትውለው? ቤተክርስቲያኗን ስትዘልፍ የምትውል ሰው ፓትርያርኩ ተሰደቡብኝ ብለህ ነው ወይስ እንዴት ማህበሩ ያልቻለውን አንዱ ግለሰብ ቻለ ብለህ ነው? ማፈሪያ። ይልቅ ለስምህ የከበደውን ድቁና ከሰምህ ላይ አንስተህ የምትሻውን ፓስተርነት ለራስህ ስጥ።
ReplyDelete