Monday 21 March 2016

እስኪ አምጡ ዝምታ!!!


የሰባ መሥዋዕት
ለቁጥር ‘ሚታክት
ያማረ እህል ቁርባን
በኵሩ መልከ መልካም ...

ልብ እያባከኑ
ንስሐ ሳይገቡ
እንዲያው በሁካታ
በአጀብ ሞቅታ
መቅደሱ አይሻም የመሥዋዕት ጋጋታ!
መዝሙር መሳይ ጩኸት ሽንገላ ጫጫታ!

ይልቅ...
ዝግ ያለ ዝምታ
የጸሎት ጸጥታ
መቅደሱ ይህን ይሻል
ዝምታ ያወዛዋል...

ሊሠራ እንዲመጣ የሠራዊት ጌታ
መቅደሱ የሚሻውን እስኪ አምጡ ዝምታ!!!


No comments:

Post a Comment