Wednesday 23 March 2016

“ከአሜን ባሻገር”፥ ባንሻገርስ!?




ከእግዜር እያፋቱ
ለዝሙት አዲስ በር እየከፋፈቱ
ዘረኝነት “ጠልቶ”
በሰው ልብ አዲስ ዘር ለማብቀል ኮትኩቶ

የምዕራቡ አለም “የከሠረበትን”
እንደአዲስ መላ ዛሬ የሚነግረን …

በዕውቀቱ “ስዩም”! …
እንደዚህ ከሆነ ያንተ፥ “ከአሜን ባሻገር”
ከእግዜር አስታራቂ “እስኪመጣ” መምህር
“ከአሜኑ ወዲህ” አይሻልም ብንቀር!?

(የበዕውቀቱ ስዩምን አዲሱን መጽሐፍ አንብቤ እንዳስተዋልኩት)

No comments:

Post a Comment