Tuesday 15 March 2016

ወርሰን ያንተን ደስታ

                                           
                                                 Please raed in PDF

ያኔ …
ሥላሴ በስድስተኛው ቀን
ፈጥሮ ፤ ፈጽሞ አረፈ እረፍትን ፤

ድካም ዝለት የማያውቀው ጌታ
ለፈጠረው ፍጥረት ዛሬም ነው አለኝታ ፤
ብዙም ሳይቆይ …
ፍጥረቱ በምርጫው የቅን መንገድ መስሎት
ዕረፍት አንተን ትቶ ለመኖር ወደደ በጣዕር በጭንቀት፡፡
ሙሴና ኢያሱ ብዙ አሳራፊዎች ቢመጡም ወደእርሱ
አዳምን ከዝረፍቱ አልቻሉም በፍጹም በምሪት ሊያደርሱ፡፡
የዚያኔ እረፍታችን ልትመልሰን ፈጥነህ
ዝቅ ብለህ መጣህ የሕማም ሰው ሆነህ፡፡
ቅዱሱ ሰንበት ሆይ! ሆነህ ለእረፍታችን ቤዛና አለኝታ

ከቀኖቹ ይልቅ አርፈናል በሥራህ ወርሰን ያንተን ደስታ፡፡

No comments:

Post a Comment