“ለትምህርትና
ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር” (2ጢሞ.3፥16) የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸውን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትንም
ሆነ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን መንፈስ ቅዱስ ለእኛ የሰጠው፥ “ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እናምን ዘንድ፥
አምነንም በስሙ ሕይወት ይሆንልን ዘንድ” ነው፡፡ (ዮሐ.20፥30-31)
የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አንድና አንድ ፤ ግልጽና ግልጽ እንጂ ስውርና
ውስብስብ ፣ ለሰዎች እንዳይገባና እንዳይረዱት ተደርጎ የተጻፈ አይደለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ልጅን የማዳን ተስፋና ተስፋው በኢየሱስ
ክርስቶስ መምጣት ፤ መሞትና መነሳት የተፈጸመ መሆኑን በማስረዳት ይህን መዳን የምሥራች ብለን ለፍጥረት ሁሉ በድፍረት ከመንፈስ
ቅዱስ ጉልበት የተነሳ እንድንናገር እንጂ ሌላ ስውር አጀንዳ የለውም፡፡ ጌታችን የመምጣቱን ምስጢር ራሱ ሲናገር፥ “እኔ ሕይወት
እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ” (ዮሐ.10፥10) ሲል ፤ ደቀ መዛሙርቱም ፤ “ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደዓለም
መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው” (1ጢሞ.1፥15) በማለት መሰከሩ፡፡ ለቤተ ክርስቲያንም የተሰጠው ትልቁ ተልእኮና አደራ “ሂዱና
አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት
አድርጓቸው” የሚል አለም አቀፍ ጥሪና ሰፊ የመከር ሥራ ነው፡፡ (ማቴ.28፥19)
ዛሬ ዛሬ የምንሰማቸው “ሰባክያንና መምህራን” የሚበዙቱ “የሐናን ለወለተ
ሐና” እየሰጡ የሚያገለግሉ ኃላፊነት የጎደላቸው ናቸው፡፡ ለመጽሐፍ ቅዱስ አውዳዊ ትርጉም የማይገዙ ብቻ አይደሉም ፤ ከመጽሐፍ ቅዱስ
ያልሆነውንም ትምህርት ሲናገሩ ከራሳቸው አፍልቀው ወይም አጋንንትን እያደመጡ ይናገራሉ፡፡ (1ጢሞ.4፥1-2) እንዲህ ያሉ “ሰባክያንና መምህራን” ነን ባዮችን ትምህርታቸውንና ስብከቶቻቸውን እየተከታተሉ
መልስ መስጠትና ምላሽ ማዘጋጀት ሁለት ተግዳሮት አለው፡፡
1. ትምህርታቸውን “እንደኢየሱስ” የተቀበሉላቸው
ብዙ ደጋፊዎች አሏቸውና፥ አገልግሎታችንን ሁሉ የተቃውሞና የጥላቻ ያደርጉታል ፤
2. በደጋፊዎቻቸው መጠን ትምህርቶቻቸውም
ብዙና ብዙዎቹም የክርስትና መሠረትና እውነት የሌላቸው ከመሆኑ አንጻር በእያንዳንዱ ላይ መልስ መስጠት እጅግ ሊቸግር ይችላል፡፡
ይሁንና እንዲህ አፈንግጦ የወጣውን ግን መመለስና ሐሰተኝነቱን ማጋለጥ
የተገባና መጽሐፍ ቅዱሳዊም ነው፡፡ እንዲህ የምለው በነገር ለመጠዛጠዝ ከማሰብ አንጻር ሳይሆን “ምነው የቅዱሱን ቃል ሥልጣን ይህን
ያህል ተጋፋን? … ምነው በአገባቡ መተርጎም ባንችል በአገባቡና በሥርዓት ብናነበው? “ከማይረባ” ተርጓሚ ኮልታፋ አንባቢ ይሻላል” ለሚለው ብርቱ ሃሳብ ድጋፍ ለመስጠትና በትርጉም
አስባብ ቃሉን ለማያከብሩት ደግሞ “እግዚአብሔራዊ የቃሉን ሃሳብ” በድፍረት ለመናገር ነው፡፡ በእርግጥም ሕዝብ እልል እያስባሉ እንዲህ
ያለውን አጸያፊ ትምህርት ለማስረጽና እንግዳ ትምህርት፥ መድረኩንና አውደ ምሕረቱን በ“ነጻ” ስላገኘን ብቻ እንደማወጅ የሚከብድ
ነገር ምን አለ!?
(ፊልሙ ለማየት እዚህ ጋ ተጭነው ይመልከቱ …)
እንግዲህ “ምህረተ አብ ወዳስተማረው” ትምህርት ስናመራ በሁለት ዋና ዋና
ርዕሶች ላይ እጅግ ትኩረት ማድረግን መርጫለሁ፡፡ በዋናነት እኒህን የመረጥኩት በእኒህ በሁለቱ ትምህርቶች ምልከታዎች ላይ ስህተቱ
ያፈጠጠና ያገጠጠ መሆኑን ለብዙዎች በማሳየት ሰዎች ሁሉ ፊታቸውን ወደቅዱስ ቃሉና ወደእውነተኛው መምህር ወደመንፈስ ቅዱስ ዘወር
እንዲያደርጉ ለማድረግ ነው፡፡
በእውኑ እኛ የተፈጠርነው ከአባታችን ከአፈርና ከአያታችን ከውኃ ነውን?!
እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ ወንድም ሴትም
ሁለቱም የእግዚአብሔር መልክና አምሳል ናቸው፡፡ መልክና አምሳል እብራይስጡ (ፀሌምና ዳማት) የሚላቸው እኛ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን
ፍጹም ተዛማዶና ትስስር እንዲሁም የእግዚአብሔር ፍጹም እጅ ሥራዎች መሆናችንን ያስረግጣል፡፡ ይህም ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ለማድረግና
ምላሽ ለመስጠት የሚያስችለን ነው፡፡
ስለዚህም በብሉይ ኪዳንም ሆነ በአዲስ ኪዳን መልክና ምሳሌ የሚሉት
ቃላት ተመሳሳይ ፍቺ ያላቸው ብቻ ሳይሆኑ፥ አዳምና ሔዋን መንፈስ ፣ አእምሮ ፣ ስሜት ፣ ምንነትን የማወቅ እንዲሁም የመምረጥ ችሎታ
የነበራቸው ሰብአዊ አካላት ሆነው ሆነው የተፈጠሩ መሆናቸውንም ያሳያል፡፡ ከዚህም ባሻገር ደግሞ አምሳልና መልክ ጽድቅንና ቅድስናን
(ኤፌ.4፥24) እንዲሁም እውቀትንም (ቈላ.3፥1) አካቶ የያዘ መሆኑንም ማስተዋል እንችላለን፡፡
እግዚአብሔር ይህንን መልክና አምሳል ለሰው ልጆች የሰጠው ከራሱ ባሕርይ
እንጂ ከእንሰሳ ወይም ከሌላ ፍጡር በማዛመድ ወይም በመዋስ አይደለም፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ወደፊት ሊገለጥበት ያሰበውን መልክና
አምሳል በሰው እንዲሆን ወዷልና፡፡ (ዘፍጥ.18፥1-2) ክብር ይግባውና ልጁም የሰው ልጅን ሊያድን ሲመጣ የሚይዘው መልክ፥ “የአብርሃምን
ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም።” (ዕብ.2፥16) እንዲል የሰውን እንጂ የሌላውን እንሰሳ ወይም ግዑዝ አካል
ማንነት በመንሳት አይደለምና፡፡ (ሉቃ.1፥35 ፤ ዮሐ.1፥14 ፤ ሮሜ.8፥3 ፤ 2ቆሮ.8፥9 ፤ ፊልጵ.2፥7 ፤ ዕብ.10፥5)
እንዲሁም እግዚአብሔር የሰውን ልጅ እጅግ በፍጥረቱም ማግነኑን የምናየው
“እግዚአብሔርም ፦ ሰውን በመልኩ ፈጠረ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።” (ዘፍጥ.1፥27) በሚለው
ቃሉ ነው፡፡ አስተውሉ! “ፈጠረ” ፣ “ፈጠረው” ፣ “ፈጠራቸው” የሚሉት ቃላት ተራ ድግግሞሽ አይደሉም፡፡ እግዚአብሔር በስድስተኛው
ቀን የሰው ልጅን ሲፈጥር የሠራው ሥራ ትልቅና ልዩ መሆኑን ለማመልከት እንጂ፡፡ ወንድና ሴት ሁለቱም በእግዚአብሔር መልክ ተፈጥረዋል ስንል የመለኮትን ባሕርይ ተካፋይ
ይሆኑ ዘንድ ተወደዋል ማለት ነው፡፡ (2ጴጥ.1፥4) በእርግጥም አማኝ ክርስቲያኖች የክርስቶስን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ እግዚአብሔር
ወስኖአል፡፡ (ሮሜ.8፥29) አንድ ቀንም እርሱን እንድንመስል እናውቃለን፡፡ (1ዮሐ.3፥2) ይህ ሚስጢር እጅግ ውብና ተስፋችንን
በመቃተት እንድንጠብቅ የሚያደርግ ነው!!!
እግዚአብሔር እንዲህ አልቆና አግንኖ የፈጠረውን የሰውን ልጅ መልኩና
አምሳሉ ስላለበት እንዲከበር እንጂ እንዲገደል (ዘፍጥ.9፥6) ፤ እንዲረገምም አልወደደም፡፡ (ያዕ.3፥9) እጅግ የሚመስጠውና የሰውን ልጅ እጅግ ታላቅነት የሚያሳየው ሌላው ድንቅ አባባል፥ “እግዚአብሔር
አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው ፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት ፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ፡፡”
(ዘፍጥ.2፥7) የሚለው ነው፡፡ ይህ ቃል ምንም እንኳ የሰው ልጅ ከእንሰሳት ጋር አካላዊ ተመሳሳይነት እንዳለው ቢናገርም ነገር
ግን ከእግዚአብሔር ጋር ልዩ ግንኙነት የመሠረተበትና በእንሰሳትና በምድር ተንቀሳቃስ ሁሉ ላይ የበላይና ገዥ መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ ስለዚህ በሰውና በእንሰሳት
፤ በግዕዛንም መካከል ከፍ እጅግ ከፍ ያለ ልዩነት አለ፡፡ (መዝ.8፥5-8)
ይህ እውነት “አባታችን መሬት ፣ አያታችን ውኃ” በሚል ዋዘኛና ፌዘኛ ትምህርት የሚቀለድበት አይደለም፡፡ በቀደመው አዳም
የቀደመው መልካችን ሲበላሽ እንኳ እግዚአብሔር ከዚህም በላይ አልቆ ምንም ዳግመኛ “እኛ ፍጥረቱ ነንና ፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር
አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን” (ኤፌ.2፥10) እንደተባለ አዲስና ከአሮጌው ሰው ጋር
ምንም አይነት ግንኙነት የሌለን (2ቆሮ.5፥17 ፤ ኤፌ.4፥22 ፤ ቈላ.3፥2) የእግዚአብሔር የእጁ ምርጥ ሥራዎች ነን እንጂ የውኃና
የአፈር ግኝቶች አይደለንም፡፡ ሕያው የሚያደርግ ቅዱስ መንፈስና ከኃጢአት ሁሉ የሚያጠራ የኢየሱስ ደም (1ዮሐ.1፥7) አለንና ውኃ
፤ ውኃ አንልም ፣ አፈር ፤ አፈርም አንሸትም፡፡
ይቀጥላል …
amen amen!God bless you Brother! I will wait the next part! May the Grace and peace of God be upon You!
ReplyDeleteይህን ጽሁፍ የጻፍክ ወንድም ጌታ ይባርክህ
ReplyDeleteይህን ጽሁፍ ለጻፍክ ወንድም ወንድምህን ለመኮነን አትቸኩል እግዚአብሔር ሁላችሁንንም ይባርክ አሜን
ReplyDeleteያንተንም ጽሁፍ አነበብኩ የወንድምህን video አየሁ ሁለታችሁም ሀሳባችሁ አንድ ነው ግን እኛ ኢትዮጵያኖች ላለመስማማት እንስማማለን አእንደሚባለው ሁሉ የናንተም ጉዳይ እንደዛውነው። ውሀም አፈርም ሰውም ሁላችንም የአባታችን እግዜአብሔር ፍጥረቶች ነን ነገር ግን እኛ ሰዎች ሁልግዜ ስንናገር የእግዜአብሔር ምስሎችነን እያልን እንመፃደቃለን ውሀና አፈር ግን አልተመፃደቁም አባታችን ያዘዛቸውን ግን እየፈፅሙ ነው እኛ ትእዛዙ ላይ የለንበትም አየህ እኛና ውሀና አፈር ልዩነታችንና አንድነታችን ይሄው ነው
ሠላም ለሁላችሁም። አሜን
My brother/sister I sincerely respect your intention of love and unity , but our brother Meheretab's teaching contradicts the very basics of Christianity ,which one we expected to agree with ?what dose it mean orthodox is a religion of Adam??,ወደ ሮሜ ሰዎች
Deleteምዕራፍ 5: 12 ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ፤
13 ሕግ እስከ መጣ ድረስ ኃጢአት በዓለም ነበረና ነገር ግን ሕግ በሌለበት ጊዜ ኃጢአት አይቈጠርም፤
14 ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና። 15 ነገር ግን ስጦታው እንደ በደሉ መጠን እንደዚያው አይደለም፤ በአንድ ሰው( Adam)በደል ብዙዎቹ ሞተዋልና፥ ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋና በአንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የሆነው ስጦታ ከዚያ ይልቅ ለብዙዎች በዛ።
16 አንድ ሰውም ኃጢአትን በማድረጉ እንደ ሆነው መጠን እንደዚያው ስጦታው አይደለም፤ ፍርድ ከአንድ ሰው ለኵነኔ መጥቶአልና፥ ስጦታው ግን በብዙ በደል ለማጽደቅ መጣ።
17 በአንዱም በደል ሞት በአንዱ በኩል ከነገሠ፥ ይልቁን የጸጋን ብዛትና የጽድቅን ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሣሉ።
18 እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኵነኔ ወደ ሰው ሁሉ እንደ መጣ፥ እንዲሁም በአንድ ጽድቅ ምክንያት ስጦታው ሕይወትን ለማጽደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ።
19 በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።
20-21 በደልም እንዲበዛ ሕግ ጭምር ገባ፤ ዳሩ ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ፥ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግሥ ዘንድ፥ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ።
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:17ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።therefore it is not mare proud saying we are created in Gods image( we Jest believe what the Bible says in the Book of Genesis),we can't compromise God's word, stay blessed!!!

ይህን ጽሁፍ ለጻፍክ ወንድም ወንድምህን ለመኮነን አትቸኩል እግዚአብሔር ሁላችሁንንም ይባርክ አሜን
ReplyDeleteያንተንም ጽሁፍ አነበብኩ የወንድምህን video አየሁ ሁለታችሁም ሀሳባችሁ አንድ ነው ግን እኛ ኢትዮጵያኖች ላለመስማማት እንስማማለን አእንደሚባለው ሁሉ የናንተም ጉዳይ እንደዛውነው። ውሀም አፈርም ሰውም ሁላችንም የአባታችን እግዜአብሔር ፍጥረቶች ነን ነገር ግን እኛ ሰዎች ሁልግዜ ስንናገር የእግዜአብሔር ምስሎችነን እያልን እንመፃደቃለን ውሀና አፈር ግን አልተመፃደቁም አባታችን ያዘዛቸውን ግን እየፈፅሙ ነው እኛ ትእዛዙ ላይ የለንበትም አየህ እኛና ውሀና አፈር ልዩነታችንና አንድነታችን ይሄው ነው
ሠላም ለሁላችሁም። አሜን
ende mihereteab yale geleban ende sebaki lemekebele yemetfelegu sewoche tasazenalachu. yihe eko terete teret negari were achawi felefelu neger new.
DeleteIf you desire to improve your familiarity only keep visiting this website and
ReplyDeletebe updated with the most recent gossip posted here.
Here is my web page ... clash of clans hack
የምን ለነገር መችኮል ነው? ትንሽ የመስማት አቅሙ ቢኖርህ እኮ ታገኝው ነበር ፣ አንተ አራሚ ሳትሆን አረም ነህ
ReplyDeleteendegebage kehone aremu ante eremat ya;felekew sew nek sehafiwema emwenetawen tiret adergo askemetowal. min tifelegalehe kezihe weche?
Deletetebarekelen tiru sehif new segawen yabzalehe
ReplyDeleteberta wendme GEta Tsegawun YAbzalh...NEkefetana sidbn bemeshekemk des yibelk enji atkefa. yeWushet agelgayoch bzu degafi silalachew ante satfera wengel meskir....ይሁንና እንዲህ አፈንግጦ የወጣውን ግን መመለስና ሐሰተኝነቱን ማጋለጥ የተገባና መጽሐፍ ቅዱሳዊም ነው፡፡ aydel antes yalkew? berta berta berta...
ReplyDeleteAmen
Deleteየጅብ ችኩል ቀንድን ይነክሳል እንዳሉ ይህን የፃፍከውም የዲያቆን ምህረተአብ ሃሳቡን ሳትረዳ አታጥላላ..
Delete@ሰይፈሚካኤል እስኪ አንተ የተረዳከውን አስረዳን?
DeleteI'm now not sure where you are getting your info, however great topic.
ReplyDeleteI needs to spend some time finding out more or figuring out more.
Thank you for excellent information I was on the lookout for this info for
my mission.
Feel free to visit my web page ... Carly Brooke Avraham Drugs Addicted
ተባረክ ወንድማችን ትልቅ አስተማሪ ፅሁፍ ነው እንዲያውም አልዘገየህም በጊዜው ነው የፃፍክ ይህ የሀሰት ትምህርት ሳይስፋፋ፡፡ ድንግል ማርያም በምልጃዋ ታስብህ፡፡ አገልጋይ በመድረክ ይሳሳታል ስህተትን ዝም ብሎ ማለፍ ደግሞ አብሮ መተባበር ማለት ነው፡፡
ReplyDeleteአገልጋይ በብዙ መልኩ ይሳሳታል እንደማይሳሳት ምታምኑ ሰወች አገልጋዮችን እያመለካችሁ ስለሆነ ተጠንቀቁ፡፡
አገልጋይ ከሚሳሳትባቸዉ በጥቂቱ
ReplyDelete1ኛ. በስህተት የአፍ ወለምታ ሚባለው
2ኛ.ሆን ብሎ አዋቂ ለመባል ለመፅሀፍ ቅዱስ የማይሆን ትርጉም መስጠት
3ኛ.ሌሎችን ለማሳፈር ተሳስታችሗል የኔ ነው ትክክል በማለት የራስን አስተሳሰብ እንደ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ለማቅረብ፡፡(የመምህር ምህረተአብ ስህተት ከዚህ ይመደባል)
4ኛ.የእግዚአብሔርን ቃል ጠንቅቆ ባለማንበብ፡፡
5ኛ. ነገሮችን በመርሳት
6ኛ.በግድ የለሽነት ለደሞዝ ብቻ በመስራት ለመንጋው ግድ የለሽ መሆን፡፡
ሌሎችም ይገኙበታል፡፡
ይገርማል በእርግጥ እኛ እኮ የተፈጠርነዉ ከአፈር አይደለም ወይ!አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ ይላል ቃሉ።ነፍሳችን ግን ዘላለማዊ ናት ምክንያቱም በእግዛብሄር አምሳል ተፈጥራለች ለዚህም ነዉ አባቶቻችን ነፍስ ህያው ናት ማለት immortals ናት የሚሉት።በእርግጥ ነፍስ ደግሞ እንደስጋዊ የሆነ የመበስበስ መብት የላትም ነገር ግን ሞታለች ብለን የምንደመድመዉ በሀጥያት ከእግዛብሄር ከፍጣሪዋ ተጣልታ ያለንስሃ ወደ አምላኳ ለፍርድ ስትቀርብ ነዉ።ወደሲኦል ከተወረወረች በእርግጥም ያቺ ነፍስ ሁለተኛ ሞትን ሞታለች ይላል ቅዱስ የእግዛብሄር ቃል!!!
ReplyDeleteድሮ በሰንበት ት/ቤት ስታስተምረን በእውነቱ እንዴት አይነት ልጅ መጣ ብለን ብዙዎቻችን ተገርመን ነበር። ግን ዛሬ ላይ መጀመርያህን ሳይሆን አሁን የቆምክበትን ሳይ አዘንኩ። በጣም ተስፋ ያለህ ልጅ ነበርክ። ዛሬ ግን አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ሳይሆን ቃልህ መናፍቃንን እጅግ ያስደስታል። ዛሬ ለተነሱበት የተሃድሶ አላማ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ስራና አላማ አስፈጻሚ ብለው ከሚጠቅሷቸው ሰዎች ተርታ ከገባህ ቆየህ። አውቃለው ቃላቴ ላንተ ምንም እንዳልሆኑ ግን እንደው ምን ነካህ ወንድሜ
ReplyDeleteጌታ ማስተዋሉን ይስጥህ
ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባህር መስጠም ይሻለው ነበር፡፡” ማቴ። ፩፰፡፮
Before you comment somebody,you should think what somebody says...please think over!!!
ReplyDeleteየምን ለነገር መችኮል ነው? ትንሽ የመስማት አቅሙ ቢኖርህ እኮ ታገኝው ነበር ፣ አንተ አራሚ ሳትሆን አረም ነህ
ReplyDeleteአዪዪዪዪዪዪዪ---------my brother look who are allover you ለአህያ ማር አይጥማትም እኮ አይገርምም !!! ተማሩ እምቢ እመኑ ብርርርርር ብሎ በየጥፋት ጎሬ ውስጥ መድረክ አዘጋጅቶ መጮህ አተቲቲቲቲ በተቲቲቲቲ ማለት አልፎም የሊቀ መኳሶቻችንን ሥራ ኮርጆ መንጠቅ ይሁን እስኪ!!!!!!!!!
ReplyDelete