በመጽሐፍ ቅዱስ በአገባቡ ወይም እንደተጻፈው ከማይነበቡ
ጥቅሶች መካከል አንዱ፦ “ … ከቶ አላወቅኋችሁም ፤ እናንተ ዓመፀኞች ፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።” (ማቴ.7፥23) በማለት
የተጻፈልን ቃል ነው፡፡ ይህ ክፍልና ሌሎችም ከዚሁ ጋር የተያያዙም ንባባት ለአፈጻጸም ከፍ ያለ የሥነ ምግባርና የፍጽምናን መንገድ ይፈልጋሉ፡፡
ከዚህም የተነሳ ብዙዎች የተራራው ትምህርት ተብለው የሚታመኑትን ቃላት ማንም ሰው መፈጸም እንደማይቻለው ያስተምራሉ፡፡ በእርግጥም
የእግዚአብሔርን ማናቸውንም ሥራ በእግዚአብሔር ጉልበት ፤ ራሱ እግዚአብሔርንም መማር የሚቻለን በራሱ በእግዚአብሔር ዕውቀት ገላጭነትና
የጥበብ አስተማሪነት ነው፡፡ ይህ ማለት ግን የተራራውን ትምህርት በራሱ በእግዚአብሔር ጉልበትና መንፈስ መፈጸም ይቻለናል ማለት
እንጂ ፈጽሞ መፈጸም አይቻልም ማለት አይደለም፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተራራው ትምህርቱ ያስተማራቸው ትምህርቶቹ
በብዙዎች ዘንድ እጅግ የተደነቁና የሚያስደምሙ ትምህርቶች ናቸው፡፡ እውነትም! የእግዚአብሔር አምላካችን መንገድና ሕጉ ፤ ሥራውም
ፍጹም ነውና (ዘዳግ.25፥15 ፤ መዝ.18፥30 ፤19፥7) ፤ እኛም በእርሱ ዘንድ (ዘዳግ.18፥13) ፤ እንደእርሱም ፍጹማን እንሆን
ዘንድ ተጠርተናል፡፡ (ዘፍጥ.17፥1 ፤ ማቴ.5፥48 ፤ 19፥21) አዎን! የእግዚአብሔር ቅዱሳንም በፊቱ ያለነውርና ነቀፋ ነበሩ፡፡
(ዘፍጥ.6፥9 ፤ 1ነገ.11፥4 ፤ ኢዮ.1፥1 ፤ ሉቃ.1፥6 ፤ 2፥25) ፍጽምና ወይም በእግዚአብሔር
ፊት የበቃ ሆኖ መገኘት ለሰው የሚቻል ነገር አይደለም (ሮሜ.3፥11 ፤ 2ቆሮ.3፥5) ስለዚህም ስለፍጽምናና ቅድስና
ስናስብ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል በተሰጠን ጸጋ እንጂ (ሮሜ.3፥21-24) በሕግ ወይም በራሳችን የምናደርገውም ፤ እናደርገውም
ዘንድ የሚገባን አንዳችም ነገር የለም፡፡
“በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ከዓለም ርኵሰት
ካመለጥን በኋላ ዳግመኛ በእርስዋ ተጠላልፈን የተሸነፍን እንዳንሆን ፥ ከፊተኛው ኑሮአችን ይልቅ የኋለኛው የባሰ እንዳይሆንብን”
(2ጴጥ.2፥20) በእግዚአብሔርና በሰው ሁሉ ፊት ጨውና ብርሃን ሆነን (ማቴ.5፥13-14) ፤ በምስክርነት ሕይወት
እንመላለስ ዘንድ ይገባናል፡፡ አንድ ክርስቲያን በሁሉ ዘንድ የሚነበብና የሚታይ ልብና ሕይወት ብቻ ነው ሊኖረው የሚችለው (2ቆሮ.3፥2)
፤ ለአንድ ሰውም ሁለት ጌታ በአንድ ሕይወት ማስተናገድ ፈጽሞ አይቻልም፡፡ (ማቴ.6፥24) እንደዳነ የሚያምን ክርስቲያን የዳነ
ሥራና ሕይወት ብቻ ነው ከእርሱና በእርሱ ሊነበብ የሚችለው እንጂ በሁለት ልብ አያነክስም፡፡ (1ነገ.18፥21)
እውነተኛ ክርስቲያኖች ክርስቶስን ሲያገለግሉ የበግ ለምድ አይለብሱም (ማቴ.7፥15)
፤ ወይም በሚያስመስልና በሚያባብል ቃል ክርስቶስን አያገለግሉም (1ቆሮ.2፥4) ፤ በመልካምና በሚያቆላምጥ ንግግርም ተንኮል የሌለባቸውን
ሰዎች ልብ አያታልሉም (ሮሜ.16፥18) ፤ ለሰው ፊት በማድላትም አያመቻምቹም (ሐዋ.4፥19 ፤ 13፥46) ፤ የብርሃን መልአክ
በመምሰልም ራሳቸውን አይለውጡም፡፡ (2ቆሮ.11፥14) ከዚህም የራቁ ናቸው፡፡ (ቈላ.2፥4) ሰይጣንና አገልጋዮቹ ማሳትን አላማቸው
አድርገው የሚኖሩ ፦ “የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸውን እየለወጡ፥ ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞች ሠራተኞች” (2ቆሮ.11፥13)ሆነው
እኒህን ሁሉ “በጥበብና በዘዴ” በሚገባ ይጠቀሙበታል፡፡
ሰይጣንን (ራዕ.13፥5)
፣ ሆዳቸውን (ሮሜ.16፥18 ፤ ፊልጵ.3፥18) ፣ የራሳቸውንም ታላቅነት (ሐዋ.8፥9) የሚሰብኩ ወይም በእነዚህ ነገሮች ፍጹም
ተሸንፈው ወይም ስለነዚህ ነገሮች በመዋደቅ የሚያገለግሉ አገልጋዮች፥ ጌታችን እንደነገረን “… በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥
በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? … ” (ማቴ.7፥22) የሚሉ ብቻ ሳይሆኑ ፦ “እሳትንም
እንኳ ከሰማይ ወደምድር በሰው ፊት እስኪያወርድ ድረስ ታላላቆችን ምልክቶች ማድረግ” (ራዕ.13፥13) ይቻላቸዋል፡፡ በዚህ የበግ
ለምድ አለባበሳቸውና ፤ በብርሃናዊ ፍጹም የገጽ መልካቸው ብዙዎችን ማሳትይ ችላሉ ፤ ያስታሉም፡፡
እኒህ ሰዎች ብዙ ተአምራትን ፤ ውብ የሆኑ መጻሕፍትና ጹሁፎችን ፤ አጋንንትን
ሊያወጡ ፤ ለምጽን ሊያነጹ ፤ እጅግ ግለት ያለውን ስብከትና ትምህርትን ሊያቀርቡ ፤ አፍ የሚያስከፍት ንግግሮችና አስደናቂ ነገሮችን
ሊያደርጉ ይችላሉ ፤ ነገር ግን “ይህም ድንቅ አይደለም” ይለናል ሁነኛው ሐዋርያ፡፡ (2ቆሮ.11፥14) በእርግጥም “ይድኑ ዘንድ
የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉ፥ የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም በዓመፅም መታለል ሁሉ
እንደሰይጣን አሠራር ነው።” (2ተሰ.2፥9-10)
እኒህ ሰዎች አጋንንትን ቢያወጡ ፣ ተአምራትን ቢያደርጉ ፣ ብዙ ብዙ ነገሮችን
ቢያደርጉ ፥ የሚያደርጉትን ሁሉ የሚያደርጉት “በስሙ” ነው፡፡ በስሙ ስለሚያደርጉም ላያቸውና ለሰማቸው ፤ ወይም ጽሁፎቻቸውን ላነበበ
እስኪያስቱና ሥራዎቻቸው ከእውነተኞቹ መለየት እሰኪያስቸግር ድረስ አንድ ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን“…መንሹም በእጁ ነው፥ አውድማውንም
ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።” (ማቴ.3፥12) የተባለለት ጌታ አንዳች
ሳይሳሳት ሥራቸውን ከእውነተኞቹ ይህ ለይቶ ያቃጥለዋል፡፡
እግዚአብሔር በስሙ የሚመጡትን ሐሰተኛ አገልጋዮችን አያውቃቸውም ፤ እነርሱ
እንደታወቀ ሆነው ወይም የታወቅን ነን ብለው ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡ ዛሬ ላይ በእርግጥም እንዲህ አይነት አገልጋዮች ከየትኛውም ጊዜ
ይልቅ እጅግ የበዙበትና እንደአሸን የፈሉበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ በብሉይ ኪዳን እንዲህ አይነት አገልጋዮች እንደነበሩ እናያለን፡፡
እኒህ የሐሰት አገልጋዮች በእውነተኛ አገልጋዮች ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ ቀላል አይደለም፡፡ እኒህ አገልጋዮች በበዙበት ሥፍራ እውነተኛ
አገልጋዮች ሥፍራ የሚያጡ ብቻ ሳይሆኑ የሚናገሩት አንድም ነገራቸው በሕዝብ ዘንድ ሙሉ ለሙሉ ዕውቅና ሊያጣ ይችላል፡፡
ቅዱስ ነቢይ
ኤርምያስ አልቃሻ ነቢይ እስኪባል ዘመኑን ሙሉ ሲያለቅስና ሲያዝን የኖረው፥ እርሱ የተናገረውን እውነተኛ ትንቢት የሐሰት ነቢያት
በመግልበጥ ሕዝቡን በእርሱ ላይ ጠላት አድርገው በማስነሳታቸው ምክንያት ነው፡፡ እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ንስሐ ባልገቡበት ኃጢአታቸው
ምክንያት የተቆረጠ ፍርድ እንዳለ ቢናገርም ፤ የሐሰት ነቢያቱ ግን ለእስራኤል ቅዱስ ላልታመነችው ከዳተኛይቱ እስራኤልና ለዐመጸኛው
ሕዝብ ሰላም ብቻ እንዳለ ይናገሩ ነበር፡፡ ሁልጊዜ የጠላት ማስመሰያ ከባድና ለመለየት አስቸጋሪ እስኪመስል ሊያደናግር ይችላል፡፡
ነገር ግን ዘወትር ቃሉን ለሚመረምርና በጸሎት ለተጋ ብርቱ ሰው፥ በጽድቅ እርሻ ላይ ያለውን እንክርዳድ መለየት አያስቸግረውም፡፡
እስኪ አንድ
እውነተኛ ምሳሌ እናንሳ ፦ በአንድ ወቅት ቅዱስ ጳውሎስና የጌታ ደቀ መዛሙርት ወደጸሎት ሥፍራ ሲሄዱ አንዲት ጠንቋይ እነቅዱስ ጳውሎስን እየተከተለች
፥ “የመዳንን መንገድ የሚነግሩአችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው” እያለች ለብዙ ቀናት ተናገረች፡፡ አስተውሉ!
የተናገረችው ቃል እውነትና ትክክል ነው፡፡ ነገር ግን ምንጩ ፍጹም የተበላሸ ነው፡፡ እንዲህ ያለውን ንግግር በሌላ ስፍራም እናስተውላለን፡፡
(ማር.1፥34 ፤ ሉቃ.4፥41) ምንጩ ካልጠራበት ሥፍራ የሚመጣውን ምስክርነት መንፈስ እጅግ አድርጎ ይቃወመዋል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ ያቺ ሴት ባደረገችው ነገር መንፈሱ እጅግ ነው የታወከው ፤ ለዚህም ነው፥ መንፈሱን እንዲወጣ በጌታ በኢየሱስ ስም
ያዘዘው፡፡
ሰይጣን ሥራው እጅግ ረቂቅ ቢሆንም ለእግዚአብሔር መንፈስ ግን የክፋት አሠራሩ
የተገለጠ ነው፡፡ ስለዚህም የጌታ ኢየሱስ ስሙን በመጥራት ብቻ አማኝ ወይም አገልጋይ መሆን አይቻልም፡፡ ሊያስትበት ስሙን ሰይጣንም
ይጠቀመዋልና፡፡ ራሳቸውን በክርስቶስ በኩል ለእውነት የሚያበቃና በክርስቶስ የሆነ እውነተኛ እምነት የሌላቸው እንዲህ ያሉ አገልጋዮችን
እግዚአብሔር ፈጽሞ አያውቃቸውም ፤ በዳግም ምጽአቱ የሚላቸው፥ እኛ እንደምናነበው “አላውቃችሁም” ሳይሆን፥ “ከቶ አላወቅኋችሁም” ብሎ ነው፡፡
የማያውቃቸው ያኔ በፍርዱ ጊዜ ሳይሆን ቀድሞ በዚህ ምድር ባሉበት ጊዜ ማለትም ያገለግሉ በነበረበት አያውቃቸውም፡፡
ወገኖቼ! ማን እንደሚያውቀን እየኖርን ሆን?! ሰው እንደሚያውቃቸው የሚያገለግሉ
የእግዚአብሔር መሳይ እልፍ ባለቀሚስና ባለካባ ፤ ባለአስኬማና ባለወይባ ካህንና ዲያቆን ፤ ጳጳስና ዘማርያን አሉ፡፡ እናንተ ግን
ማን እንደሚያያችሁ ይሆን ያመናችሁትን እያገለገላችሁ ያላችሁት? ብዙ ደክሞ በጌታ አለመታወቅ ትልቅ ኪሳራ ፤ ጥቂት እጅግ በጣም
ጥቂት አገልግሎ ግን በጌታ መታወቅ ከመቶ እጥፍ የሚበልጥ ትልቅ ትርፍ ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ለባርያዎችህ እንዲህ ያለውን ማስተዋል
አብዛልን፡፡ አሜን፡፡
amen amen! God bless you brother!
ReplyDeleteI never seen in the bible that Satan do miracle or cast out demons in Jesus's name, Please brother en test every miracle in the light of the Bible.calling the work of the holy spirit as Satan's work is unforgivable sin!!!
ReplyDeleteየማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 3:22 ከኢየሩሳሌም የወረዱ ጻፎችም። ብዔል ዜቡል አለበት፤ ደግሞ። በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል ብለው ተናገሩ።
23 እነርሱንም ወደ እርሱ ጠርቶ በምሳሌ አላቸው። ሰይጣን ሰይጣንን ሊያወጣው እንዴት ይችላል?
24 መንግሥትም እርስ በርስዋ ከተለያየች ያች መንግሥት ልትቆም አትችልም፤
25 ቤትም እርስ በርሱ ከተለያየ ያ ቤት ሊቆም አይችልም።
26 ሰይጣንም ራሱን ተቃውሞ ከተለያየ፥ መጨረሻ ይሆንበታል እንጂ ሊቆም አይችልም።
27 ነገር ግን አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ ዕቃውን ሊበዘብዝ የሚችል የለም፥ ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል።
28 እውነት እላችኋለሁ፥ ለሰው ልጆች ኃጢአት ሁሉ የሚሳደቡትም ስድብ ሁሉ ይሰረይላቸዋል፤
*29 በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚሳደብ ሁሉ ግን የዘላለም ኃጢአት ዕዳ ይሆንበታል እንጂ ለዘላለም አይሰረይለትም።*!!
የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 11:18 እኔ አጋንንትን በብዔል ዜቡል እንዳወጣ ትላላችሁና ሰይጣን ደግሞ እርስ በርሱ ከተለያየ መንግሥቱ እንዴት ትቆማለች?
*19 እኔስ በብዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ ልጆቻችሁ በማን ያወጡአቸዋል?* ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል።
Therefore Satan never Glorify Jesus by doing miracle in Jesus name, even can't call his name ,1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
ምዕራፍ 12:1 ስለ መንፈሳዊ ነገርም፥ ወንድሞች ሆይ፥ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ።
2 አሕዛብ ሳላችሁ በማናቸውም ጊዜ እንደምትመሩ ድምፅ ወደሌላቸው ወደ ጣዖታት እንደ ተወሰዳችሁ ታውቃላችሁ።
3 ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር። ኢየሱስ የተረገመ ነው የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር። *ኢየሱስ ጌታ ነው* ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።
4 የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው፤
5 አገልግሎትም ልዩ ልዩ ነው ጌታም አንድ ነው፤
6 አሠራርም ልዩ ልዩ ነው፥ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።
7 ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሰጠዋል።
8 ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና፥ ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል፥
9 ለአንዱም በዚያው መንፈስ እምነት፥ ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ስጦታ፥ ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ፥
10 ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱም *መናፍስትን መለየት፥* ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤
11 ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል። therefore we have to be patience like Apostle Paul until the holy spirit expose it.
የሐዋርያት ሥራ
ምዕራፍ 16:16ወደ ጸሎት ስፍራም ስንሄድ፥ የምዋርተኝነት መንፈስ የነበረባት ለጌቶችዋም እየጠነቈለች ብዙ ትርፍ ታመጣ የነበረች አንዲት ገረድ አገኘችን።
17 እርስዋ ጳውሎስንና እኛን እየተከተለች። የመዳንን መንገድ የሚነግሩአችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው ብላ ትጮኽ ነበር።
18 *ይህንም እጅግ ቀን አደረገች*። ጳውሎስ ግን ተቸገረና ዘወር ብሎ መንፈሱን። ከእርስዋ እንድትወጣ *በኢየሱስ ክርስቶስ ስም* አዝሃለሁ አለው፤ በዚያም ሰዓት ወጣ።
Finally “ … ከቶ አላወቅኋችሁም ፤ እናንተ ዓመፀኞች ፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።” (ማቴ.7፥23)dose not applies for every servant of God,only for those who have seen the Glory and power of God done in Jesus name,and gone back to their sin Like Iscariot Judah(remember he cast out demons in Jesus name by the power of God with all Apostles).Jesus said "I never new you" since their names has been wiped off from the book of life,not because their miracle was from Satan.Satan never do a miracle to Glorify Jesus's name!!
God bless you all in the mighty name of Jesus Christ, the name above all names !!!!
I never seen in the bible that Satan do miracle or cast out demons in Jesus's name, Please brother en test every miracle in the light of the Bible.calling the work of the holy spirit as Satan's work is unforgivable sin!!!