Sunday 6 December 2015

ጌታ ካላለበት



ከመድረኩ ቆመህ ከአውደ ምህረቱ፤
ተፋተህ ተራቁተህ ከእግዚአብሔር ፍርሃቱ፤
“በʻኔ የሚናገር ጌታ ነው” በማለት፤
ለምን ትጮኻለህ? የውስጥህን ክህደት፤

ልጠይቅህ? …
ሸቃቅጠህ ቀላቅለህ እንክርዳድ ከስንዴ፤
ዘፈንና መጠጥ ተፈቅዷል አንዳንዴ፤
የወንጌል መከራን ማለፍ ነው ኮምኮ ፣ ኮምኮ በዘዴ…
እያልክ ከመድረኩ ኃጢአትʻ ምትሞሽረው፤
ጌታ ካላለበት ከየትኛው መዝገብ ጥቅሱን አገኘኸው?!


1 comment: