Tuesday 16 June 2015

በክስ አታዳክሙኝ!


                    Please read in PDF  

ለምን እክዳለሁ ፣ አመንዝራነቴን ፤
ሌባና አመጸኛ ፣ ስግብግብነቴን ፤
አላስተባብልም ፣ ስሁት ሰው መሆኔን … ፤

ዳሩ …
በትላንቴ አፍራለሁ ፣ ዛሬ ዞሬ ሳየው ፤
ህይወቴን ያይደለ ፣ ሞቴን ነው 'ሚጮኸው!

ግና ድፍረት አለኝ ፣ በክርስቶስ በኩል ፤
ዋናው ኃጢአተኛ ፣ ምህረት በመቀበል ፤
ሞቴ ተገስጿል ፣ ቤቴ ተፈውሷል ፤
በንስሐ ልቤ ፣ ወደአባቴ አቅንቷል፡፡

የበደልኳቸውን ፣ የበደሉኝንም ፤
ይቅርታዬ ይኸው ፣ ባትቀበሉኝም፡፡

ከዚህ በዘለለ …
በክስ አታዳክሙኝ ፣ ተንትጌያለሁ በ'ርሱ ፤

መቅደሱን የመላው ፣ ጋርዶኛል ቀሚሱ፡፡

1 comment:

  1. ዎው! ጌታ ጸጋዉን ያብዛልህ!

    ReplyDelete