ከሩቅ
የሚሰማ ፣ ከአድማስ ባሻገር፤
ከምድር
ዳርቻ ፣ ከቀላያቱ ዳር፤
ሰው
ከማይኖርበት ፣ ከዚያ ምድረ በዳ፤
በረሃብና
ጥም ፣ ሥጋቸው ቢጎዳ…
አራጅ
ተስፋ ቆርጦ ፣ ስል ብረት ሲያነሳ፤
በጥይት
ደብድቦ ፣ አንገትን ሲቀላ፤
እንደሌባ
ራሱን ፣ ጋርዶና ደብቆ፤
የማይበላውን
፣ የሰው ሥጋ አርዶ …
ሥጋቸውን
ቢያፈርስ ፤
ደማቸውን
ቢያፈስ፤
ደማቸው
ድምጽ አለው ፣ ጮኾ የሚጣራ፤
ክርስቲያን
ሆይ! ጽና ፣ የሚል እንዳትፈራ፡፡
አማኙ
ሆይ! ስማ ፣ የዚህን የደም ድምጽ ፤
ስለሙሉ
ደሞ'ዝ ፣ የወንጌሉን እውነት -
በሕይወትህ ጨብጥ፡፡
No comments:
Post a Comment