Saturday 18 April 2015

እንጭጭ ክርስትና!


                      Please read in PDF       

ጸሎት እወዳለሁ ባ'ምላኬ ፊት መቆም፤
ምጽዋትም ሰጣለሁ ድኀ ለመደጎም፤
አብዝቼ ጾማለሁ ከምግብ ውኃ ርቄ፤

ሕጉን ጠብቃለሁ እጅግ ተጠንቅቄ፤
ግን ፈጽሞ አልሻም በስሙ መታማት፤
የኢየሱስ ወገን በሚለው መጠራት፡፡

ንግግሬ እንደ'ርሱ ልብስ አለባበሴም፤
ጠረኑም ጠረኔን አውዶ ቢገዛም፤
አትሙኝ በስሙ መከሰስ አልወድም፡፡
ተስማምቼ ልኑር ከሰው ተዋድጄ፤
ስለምን በስሙ ልኑር ተጠምጄ?
የሚል …
… እንጭጭ ክርስትና ዛሬ ተጠናውቶን፤
ወንጌልና የሰው ፊት ተመቻመቸብን፡፡
ብናስተውል …
እርፍን የያዘና ነብርን የጨበጠ

ወደኋላ አይልም ሞትን ያመለጠ፡፡

No comments:

Post a Comment