Friday 20 August 2021

ማርያም፤ ሰባት ጊዜ ሞታ ተነሣች?

Please read in PDF

በኦርቶዶክስና በካቶሊክ ስለ ማርያም ሞት፣ “ትንሣኤና ዕርገት” የማያልቁ አእላፍ ተረቶች አሉ፡፡ ምሳሌ፦ ነገረ ማርያም በግልጥ፣ የማርያምን ስም ትርጉም ሲያብራራ እንዲህ ይላል፣ ማርያም በገሃነም ያሉ ኀጢአተኞችን ባየች ጊዜ፣ “እርሷም እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እነዚህ ነፍሳት ዘለዓለም በገሃነመ እሳት ወርደው ሲቀሩስ እንኳን አንድ ጊዜ ፯ ጊዜ ልሙት ብላ ሙታለች ኋላም ለፍጥረቱ ኹሉ መጽደቂያ ሁና ተገኝታለችና ወኀብት(ስጥውት) አላት፡፡”[1] ማርያም ለኀጢአተኞቹ ራርታ ሰባት ጊዜ ልሙትላቸው ብላ ሰባት ጊዜ ሞታላቸዋለች! ከዚህም የተነሣ መጽደቂያቸው ኾናለች! መጽሐፍ ቅዱስ ግን፣ “አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥ እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤” (ሮሜ 3፥21-22) በማለት የምንጸድቀው በክርስቶስ ብቻ እንደ ኾነ ይነግረናል!

ካቶሊካዊው፣ “ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ[2] 12ኛ የእመቤታችንን ወደ ሰማይ መውጣት አንቀጸ ሃይማኖት (ዶግማ) አወጁ፡፡”[3] ይህንም የወሰኑት መጽሐፍ ቅዱስን ሳይኾን ትውፊትን መሠረት በማድረግ ነው!

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ በግልጽ በመንቀፍ፣ ማርያም ሞታ በመነሣትዋ ለኀጢአተኞች መጽደቂያ መኾንዋን ሲናገሩ፣ ካቶሊካውያኑ ደግሞ ከ1800 ዓመታት በኋላ የማርያምን ዕርገት በዶግማነት አጸደቁ!

እኛስ!

ጌታችን ኢየሱስ፣ ደቀ መዛሙርቱን፣ “ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥ በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል። እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ።” (ማቴ. 24፥46-48) ብሎ እንደ ተናገረው እኛም፣ “መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥” (1ቆሮ. 15፥3-4) ብለን እመሰክራለን፤ ከዚህ የተለየ ምስክርነት ከእግዚአብሔር አይደለም!



[1] ነገረ ማርያም፤ ገጽ 665

[2] 1876 እስከ 1958 ዓመተ እግዚዕ በሕይወት የኖረ ነው፡፡

[3] የካቶሊክ እምነታችን ምንነት(ካቶሊክ በመኾናችን የሚሰማን ደስታ)፤ ገጽ 64

2 comments:

  1. እኛ የኢ/ኦርቶዶክስ ተ/ቤ/ክ ተከታዮች የምናመልከው ጠንቅቀን እናውቃለን። እሱም መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ነው። አምልኮን ለፍጡራን አንሰጥም። እሱ ራሱ ያከበራቸው ቅድስት ድንግል ማርያምን

    ReplyDelete
  2. እንግዴህ ምን ይደረግ???ድንግል ማርያም የምትሰጠው እንደ ቅዱስ ዮሐንስ እስከ መስቀል ድረስ ለፀና ነው።አንተ ገና ማይክ ከመጨበጥህ አዳራሽ አማረህ በአዳራሽ ደግሞ ምንም የለም ባዶ ጩኸት ብቻ። መናፍቃን ነፍስ ይማር

    ReplyDelete