Saturday, 1 August 2020

የአፍላህን ጊዜ

Please read in PDF

ወዲያ ገረገራ፣ ጥግ ላይ ያለኸው
ያለህ  የምትመስል፣  ሻግተህ  ያረጀኸው

ኃጢአት ያነቀዘህ፣ በደል ያደቀቀህ
ይህ ዓለም  መዝጊያ በር፣ ያለው የመሰለህ…
ሰርክህን  ለመርከስ፣ ማለዳህን ለነውር
ዛሬም  ለዓመፃ፣ ለግፍ ʻምትቃጠር
የጌታ  ልጅ ሆነህ፣ እንደ ሎሌ ኗሪ
ለክብር  ተፈጥረህ፣  የውርደት ቤት ሠሪ
እባክህ ልብህን፣ እንዲህ ብለህ ጠይቅ
መቼ ነው የʻኔን ቤት፣ ጨርሼ “ʻምመርቅ”?

                        ሁሌ ለኃጢአትህ፣ ሁሌ ለበደልህ
                        ነፍስ እያጎሳቆልክ፣ በሥጋ መክበርህ
                        በምድሩ  እያተረፍህ፣  በሰማይ ኪሣራ
                        ከፈጣሪ ሳትሆን፣ ከዲያብሎስ ጎራ
                        እንዲህ ተሰልፈህ፣ ለራስህ  ሳትሠራ
                        ለትልቁ ጌታ፤ ላዳነህ ፈጣሪ፤ ምንም ሳትሰጥ ሥፍራ
                        አስበኸው ይሆን  ፍፃሜና ጥጉን
                         የዘራኸውን ዘር የእርሻህ መከሩን?!

ተው ወዲህ ተመለስ፣ ቤትህን “በʻጅህ ሥራ”
ተመለስ ከልብህ፣ መንገድህን አቅና
ፊትህን ዘወር አድርግ፣ ታረቅ ከፈጣሪ
ትክ ብለህ  አድምጥ፣  የመስቀሉን ጥሪ …

                        ተሰናድቷል ላንተ፣  ወይንና ፍሪዳ
                        የውበት ልብስህም፣ ቀለበት ባርኔጣ
                        እናም ……..
                        በልብህ ሰገነት፤ የንስሐ ጎጆ፤ “በእንባህ” ልትቀልስ
                        ዛሬ ዘመንህን፤ የአፍላህን ጊዜ፤ ለአምላክህ ቀድስ።
23/3/2006 ተጻፈ።

No comments:

Post a Comment