Sunday 12 April 2020

ጌታ አኹን አድን

ስለ በዛው ጣዕር ስለ ሕፃናት ዋይታ
ስለ አዛውንቱ ስለ እናቶች እንባ
እንደ ቅጠል ረግፎ ቀብር በወረደው

አንጀቱ ታውኮ ልቡ በፈረሰው
ስለእነዚህ ኹሉ እኔ አልልህም
በሰው ልጅ በጎነት እኔ አልለምንህም።
ስለ ስምህ ብለህ ስለ ሁሉን ቻዩ
ስለ አንድያ ልጅህ ስለ ተሰቃዩ
ጌታ አኹን አድን ጌታ አኹን አቅና
ለግሩም ርኅራኄህ፣ ኹሌም ሆሼዕና ይገባሃልና።

No comments:

Post a Comment