Monday, 8 July 2019

ክሽክሽ አርገህ ሰብረህ

Please read in PDF
ስብእና ረከሰ
የጐጥ ቤት ነገሠ
ሰውነት ወረደ

ቋንቋ ተወደደ
ወንዝነት ገነነ
አብሮነት ተነነ …
ነገድ አቃየሰን
ብሔር አናከሰን
ቀለም ተመረጠ
ሰው መኾን ዘቀጠ …
መቅኖ አጣን ረከስን
ተባላን፣ ተናተፍን፣ ከገዛ ወገናችን
ጠባችን ከረረ
ፍቅራችን መረረ …
ባድማ ለመኾን ማለድን ቃተትን
መኖር ተመርረን መጫረስ “ጣፈጥን” …
ኤሎሂም ያህዌ አንተ ካልመለስከን
ሰብረህ በምሕረት ዳግም ካልፈወስከን
ዓመጽ የማንጠግብ የገልቱ ገልቱ ነን
የኀጢአት ጡት ጠቢ የአንቀልባ ሕጻን ነን …
ክሽክሽ አርገህ ሰብረህ እንደገና ማረን …
አሜን

No comments:

Post a Comment