Monday 29 July 2019

ወርሰህ ክበርበት

Please read in PDF
እኔ …
ኹል ጊዜ ስሑት ፍጹም የማልረባ
ዘወትር በደጄ ኃጢአት የሚያደባ

ከክፉ ማላመልጥ
የተያዝኩ በወጥመድ …፣
በሥጋ ደም ውልደት ዘመኔ የባጀ
ምግባሬ ሃሳቤ በፊትህ የጃጀ
ኢየሱስ ግን አንተ …
ነውር አልባ ፍጹም ነህ፣ ጻድቅና ቅዱስ
ዕርቃን ያለችን ነፍስ ክብርን የምታለብስ
ቁስል ለወረሰው መዓዛህ ʻሚፈውስ
ልዩ ነህ ኢየሱስ ወደር አልባ ጌታ
በጽድቅህ ደም ግባት ፍጥረት የምትገዛ …
እንኪያስ …
እርጅናዬን ዋጀው የረከሰው እኔን
ወርሰህ ክበርበት አለመታመኔን!!!


2 comments: