Wednesday 22 August 2018

ከሆነኝ ኢየሱስ!

Please read in PDF

ጠዋት በማለዳ ሲመሽም በሠርኩ
በኃጢአት ወድቄ ድኼ እያለቀስኩ
መሐሪ ፍለጋ ለበደሌ ይቅርታ

ብዞር ብንከራተት አጣሁኝ አለኝታ!

የኃጢአቴ ብዛት አልፎ ልኩን ጥሶ
የተመካሁበት የራስ ጽድቄ ፈርሶ
ስመጣ ዕርቃኔን ከነከባድ ሸክሜ
አለመራራትን የማይችል ጌታዬ
እጁን ዘረጋልኝ
ዘርግቶም አቀፈኝ
ጠረኑን አሻቶ ጸጋ አለበሰኝ፡፡

ማለዳም ብመጣ በጨለማው ሌሊት
እርሱ እኔን ታቅፎ ከያዘኝ በጽናት
ለምን እመርጣለሁ? ከቶ ከርሱ ሌላ
ከሆነኝ ኢየሱስ የዘላለም ጥላ?!

1 comment: